የኢትዮጵያ ታሪክ ባጭሩ

የኢትዮጵያ ታሪክ ባጭሩ

የኢትዮጵያ ታሪክ ባጭሩየአርኪኦሎጂና የጽሁፍ መረጃዎች እንድሚገልጹት ኢትዮጵያ የመንግስት አስተዳደር ከጀመረችበት ከአምስት ሺህ አመት በፊት የነበሩት ነገስታት ዝርዝር ታሪክ ላይ ከተጠቀሱት  4 ዉስጥ ንጉስ አሜን አንደኛው የኢትዮጵያ ንጉስ ነበር።

ይህ ታላቅ ንጉስ ግዛቱን በማስፋት ግብፅንም ያስተዳድር የነበረ ሲሆን ግብፆችም በታሪካቸው ትልቅ ቦታ ከሰጡት ነገስታቶቻቸው መካከል ዋንኛው ነው::ንጉስ አሜን ኢትዮጵያዊ ንጉስ እንደነበር የሚቀርቡ መረጃዎች የሚከተሉት ናቸው።

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን መዝግባ የያዘቻቸው የነገስታት ታሪክ እና ዝርዝር
  • የጥንታዊ ሜሮይ ፍርስራሾች በማጥናት ንጉስ አሜን ኢትዮጵያዊ መሆኑን ያረጋገጠው የታሪክ ተመራማሪ ሆስኪንስ የጥናት ውጤት
  • በኑብያ ፒራሚዶች ውስጥ ንጉስ አሜን እና ሰራዊቱ ጋር ግብፅን በኃይል በያዙበት ወቅት ስላደረጉት ጦርነት የሚያሳዩ የተቀረፁ ምስሎች።
  • የንጉስ አሜን ዝርያዎች ግብፅ በውጭ ዜጎች በመዳቀሏ አገራችን ብለው ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው
  • የሃርቫርድ ዩንቨርስቲ የቁፋሮ ተልእኮ ቡድን ግብፅን ስለገዙ ኢትዮጵያውያን ያቀረበው መረጃ

ወዘተ (ራፋቶኤል)::


በዓለም ዉስጥ ክሚገኙ ጥንታዊ አገሮች ኢትዮጵያ ቀዳሚ በመሆን ከሁሉም የበለጠ ረጅም እድሜ አስቆጥራለች፡፡ በግእዝ/ዓማርኛ እና በመጽሀፍ ቅዱስ ከተመዘገቡት ተጨባጭ መረጃዎች በተጨማሪ አምስት ሚሊዮን አመት የሚሆነውና በጣም ረጅም እድሜ ያስቆጠረው የሰው ቅሪት የተገኘው በኢትዮጵያ አዋሽ ሸለቆ አካባቢ ሲሆን ይህም፣ 3.2 ሚሊዮን አመት የሆነውን እዛው አካባቢ የተገኘውን የሉሲን (ድንቅነሽን) አጽም በእድሜ ይበልጣል፡፡

ግብጽን ሲገዛ የነበረው ሄሮደስ የሚባለው ንጉስ ከክርስቶስ ልደት በፊት በአምስተኛው ክፍለ ዘመን የነበረው ታሪክ ፀሀፊ የጥንቷን ኢትዮጵያ በጽሁፎቹ ላይ ይገልፃታል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ላይም ብዙ ግዜ የምትወሳ ስትሖን በተለይም ብሉይ ኪዳን ላይም የንግስት ሳባ (መከዳ) ኢየሩሳሌም መሄድና ለንጉስ ሰለሞን ከባድ የሆኑ ጥያቄዎች ማንሳቷ ተጽፏል፡፡ ኢትዮጵያ ዛሬ ያላትን መልክ እንድትይዝ ያደረጋት ንጉስ ሚኒሊክ የንግስት ሳባና የንጉስ ሰለሞን ዘር ናቸው::

የኢትዮጵያ ታሪክ ባጭሩ
ታላቁ ንጉስ አጼ ልብነድንግል

ንግስተ ነገስት መከዳ ወይም አዜብ (የንግስት ሳባ) ቤተ መንግስት ፍርስራሽ ሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ በጥንታዊዉ የአማራ ከተማ በአክሹም አካባቢ ይገኛል፡፡ ክርስትናን ኢትዮጵያዉያን ከመቀበላቸዉ በፊት (ኣስቅድመዉ)  የኦሪትን ህግ ሰለሚያዉቁ ኣመተ ዓለምን ወደታች እየቆጠሩ የጌታን መወለድ ይጠብቁ ሰለነበረ ክርስትናን ለመቀበል ኣላስቸገራቸዉም፡፡

በስድስተኛ ክፍለዘመን (548 ዓ/ም) ማለትም በአማራው ንጉስ በአጼ ገብረመስቀል ዘመን የነብዩ መሃመድ ተከታዮች ወደ ኢትዮጵያ ተሰደው በመጡበት ወቅት የክርስቲያን አማራ ንጉሶች ፍትህ አወቅ ስለነበሩ መጠለያ በመስጠትና ከህዝባቸው ጋር አብረው በእኩልነት እንዲኖሩ ፈቅደው እስልምና ሃይማኖት በአለም እንዲያብብ ቢያረጉም እንደ እነ ግራኝ አህመድ አይነት ከሃዲዎች ከኦቶማን ቱርኮች ጋር በማበር ከፍተና ክህደት በመፈጸም የኢትዮጵያን ህዝብ አሰቃይተዋል።

ነገር ግን በሰባተኛው ክፍለ ዘመን በእስልምና መስፋፋት ምክንያት ኢትዮጵያ ከአውሮፖውያኑ ክርስትያን ርቃ ቆይታለች፡፡ በመቀጠልም  ጎንደር ቤተመንግስት ዉስጥ ተቀጥሮ በሚሰራ ስኡል ሚካኤል በሚባል ትግሬ ተንኮል የተነሳ ኢትዮጵያ ወደ ጎጥ ወርዳ  ለብዙ ዘመናት ከሌላ አለም በመለየት በጨለማ ዉስጥ አንቀላፍታ ኖረች። ይህም ዘመነ መሳፍንት በመባል ይታወቃል።

ከዛሬ ፶00 ዓመት በፊት የሶሎሞን ስረወ መንግስት ሸዋ (መንዝንና ተጉለት) ላይ  ሆኖ ለረጅም ዘመን ኢትዮጵያን ካስተዳደረ በሁዋል  የግራኝ መሃመድ ወረራ በአጼ ልብነድንግል ዘመን ተካሄደ።  ኢትዮጵውያን በግራኝ መሃመድ ወረራ የተነሳ ከፖርቱጋሎች ጋር ግንኙነትን መሰረቱ፡ በ፩፮፴ ተጀምሮ ለረጅም ጊዜ የተካሄደው ግጭት ከውጪ የመጡትን ሚሲዮናዊያን በሙሉ ከኢትዮጵያ በማባረር ሰላም ተመልሷል፡፡ ይህ የከፋ የግጭት ጊዜ ኢትዮጵያ የውጭ ክርስትያኖች ላይ እና አውሮፖውያኖች ላይ እስከ ሀያኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ፊቷን እንድታዞር አስተዋጾ ከማድረጉም በተጨማሪ እስከ 19ኛው ክ/ዘመን አጋማሽ ድረስ ኢትዮጵያ ከመላው አለም ተገልላ እንድትቆይ አድርጓታል፡፡

አጼ ተዎድሮስ

ከ1700 ጀምሮ 100 ለሚሆኑ አመታት ኢትዮጵያ ማዕከላዊ አገዛዝ ሳይኖሯት ቆይታለች፡፡ ይህም “ዘመነ መሳፍንት”  ሲሆን በ1869 አፄ ቴዎድሮስ መሳፍንቶቹን ሁሉ አስገብረው ኢትዮጵያን አንድ አድርገዋል::

ከ1881 እስከ 1905 ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ በአፍሪካ ይዞታቸውን እያሰፉ የነበሩትን የአውሮፖ ሀይሎችን ጥቃት በመከላከል ኢትዮጵያን በስርዓት አስተዳድረዋል፡፡ በዚያን ጊዜ ጣልያን ኤርትራን በከፊል ቅኝ ገዝታ የነበረችበትና በ1880ዎቹ አጋማሽ ላይ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ቅኝ ገዝታት የነበረችበት ጊዜ ስለነበር ከሌሎች አውሮፖ አገራት በበለጠ ለኢትዮጵያ አስጊ ነበረች፡፡ በ1880 ግን እስከዛሬ ድረስ ዝነኛ በሆነው የአድዋ ጦርነት ኢትዮጵያ ጣልያንን ድል በማድረግ በአፍሪካ የባእዳን ገዥ ሀይሎችን ያሸነፈች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች፡፡

አጼ ምኒልክ

ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ የቅኝ ገዥዎችን ወረራና መስፋፋት በመመከትና ድልን በመቀዳጀት ለኢትዮጵያዉያን ብቻ ሳይሆን በባርነት ቀንበር ተጠምደዉ ለሚማቅቁ የመላዉ ዓለም ህዝቦች ከፍተኛ ክብርና ተስፋን አጎናጥፈዋል:: በ1908 የዳግማዊ ሚኒሊክ ልጅ የሆኑትን እቴጌ ዘውዲቱ ስልጣን ያዙ ፡፡ የሳቸው የቅርብ የስጋ ዘመድ የነበሩት ራስ ተፈሪ መኮንንም ሞግዚት አስተዳደርና ወራሽ ሆነው ተሹመዋል፡፡ እቴጌ ዘውዲቱ በ1922 ሲሞቱ ተተኪያቸው ዐጼ ሀይለስላሴ ስልጣን ያዙ ፡፡ ነገር ግን በ1928 ዓ.ም የጣልያን ሀይሎች ኢትዮጵያን ለአጭር ጊዜ ወረው ሲቆጣጠሩ ግዛታቸው ተቋርጦ ነበር፡፡

ፋሽስት ቅዲስቲቱዋን ኢትዮጵያን ለማዋረድ ለመዝረፍና ለመግዛት ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ ዝግጅቱን አጠናቆ በ1928 ዓም 300, 000 ሰራዊት 160 ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች 450 ታንኮች 2000 የመጉዋጉዋዣ መኪናዎችን በማሰማራት ድንበር አልፎ ጦርነት በመክፈት ከገጠር እስከ ከተማ ህዝቡን ያለ እርህራሄ ጨፈጨፈ። በዚህ የጅምላ ጭፍጨፋ ላይ የመጀመሪያውን ህይወት ያለዉን ነገር ሁሉ የሚያጠፋውን “ማስተርድ ጋዝ” የሚባል ኬሚካል መሳሪያ በመጠቀም ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል ፈጸመ።

ራስ ደስታ ዳምጠዉ በትግሬው የፋሽስት ሎሌ ተክሉ መሸሻ ጠቋሚነት ተይዘው ሊገድሉ ሲወሰዱ።

በዚያን ክፉ ቀን የነጻነትና የሀገር ትርጉም የገባቸው የቁርጥ ቀን ልጆች በየአካባቢያቸው ፋኖዎችን በመምራት የእብሪተኛዉን የፋሽ ስት ጦር መግቢያ መዉጫ በማሳጣት ኢትዮጵያ ዉስጥ በሰላም መኖር እንደማይችል ተስፋ አስቆርጠዉታል። ከነዚህ ነበልባል የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች መካከል ጠላትን በተከታታይ ዝርክርኩን አዉጥተው ከደቡብ ያሳደዱትና በመጨረሻው ዉጊያ ላይ ኢትዮጵያዊ በሚመስሉ የትግሬ ስርጎ ገብ ባንዶች ቆሰለው የተያዙትና በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉት ዉዱ የኢትዮጵያ የክፉ ቀን ልጅ ራስ ደስታ ዳምጠው ነበሩ።

ራስ ደስታ ዳምጠዉን ያስያዛቸው የባንዳ ጦር መሪ ደግሞ የትግሬው ተክሉ መሸሻ የሚባል የጣሊያን ሎሌ ሲሆን የስብሃት ነጋ አጎት የናቱ ታላቅ ወንድም መሆኑ ተረጋግጦአል:: ተክሉ መሸሻ በጣሊያን ደጃዝማችነት ተሰጥቶት በደቡብ ኢትዮጵያ የኢጣልያ ባንዳ ጦር አዛዥ ሆኖ በአካባቢው ኢትዮጵያ ጦር አዛዥ የነበሩት ራስ ደስታ ዳምጠው ከበርካታ አስደናቂ ጀብዱ በሁዋላ ቆስለው በጉራጌ አካባቢ መስቃ ከተባለው ሥፍራ ተኝተው በስቃይ ላይ እያሉ ተክሉ የስለላ መረቡን ዘርግቶ እግር በግር ተከታትሎ በመያዝ ከግንድ ጋር አስሮ በጭካኔ ደብድቦ ከገደላቸው በኋላ ራሳቸውን ረግጦ በመቆም ፎተግራፍ በመነሳት ለጣልያኑ ጌታው ግዳይ ካቀረቡት እርካሽ የትግሬ ከሃዲዎች አን

የኢትዮጵያ ታሪክ ባጭሩ
የሸንቁጥ ልጆችና ተከታዮቻቸው በሰሜን ሸዋ ዱር ገደል

ዱ ነበር። የፋሽስት ጣሊያን ጦር ኢትዮጵያን ወሮ መናገሻ ከተማዋን አዲስ አበባን ለመያዝ   ሲገሰግስ ጀምሮ ሶስቱ ቆራጥ የኢትዮጵያ ሌጆች (የሸንቁጥ) ልጆች አበበ ሸንቁጥ ተሾመ ሸንቁጥና ጥላሁን ሸንቁጥ በመርሃቤቴ በጅሩና በዠማ ወንዝ አካባቢ በመንቀሳቀስ “ዱሩ ቤቴ” በማለት ብዙ የአካባቢውን ጀግኖች አስከትለው የጣሊያንን ሀይል በመመከትና ከአገር በማባረር ከፍተኛ ገድል ፈጽመዋል።

አጼ ህይለስላሴም በዉጊያ ላይ በመሳተፍ የበኩላቸዉን ድርሻ ተወጥተዋል። ለምሳሌ አንድ የጣሊያንን የቦንብ ጣይ አዉሮፕላን በመምታት አንኮታኩተውታል። ሆኖም ግንጣሊያኖች በጀርመኖችና በአንዳንድ ሌሎች ኤሮፓዉያን በመረዳትና በሃገርም ዉስጥ እንደ ትግሬው ሀይለስላሴ ጉግሳ አይነት ባንዶች በማስከተል ባለመቻላቸው ከሃገር ዉጭ በመሆን ትግሉን ቀጠሉ። የቀዳማዊ ሃይለስላሴ በህይወት መኖር ለነጻነት ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ የመንፈስ ድጋፍ ከመሆኑም በላይ ሌሎች ሃገሮች ለጣሊያን እዉቅና እንዳይሰጡ በማድረግ ከፍተኛ የዲብሎማቲክ ስራዎችን አከናውነዋል።

አጼ ኃይለሥላሤ

አጼ ኃይለስላሴ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት እድገትና ደህንነት ብዙ ለፍተዋል። የጠላትን ወረራ በማስመልክ ሊግ ኦፍ ኔሽንስን ጠይቀው ሰሚ ስላጡ ወደ በእንግሊዝ አገር በመሰደድ ለአምስት አመታት ታግለዉ የኢትዮጵያን አርበኞች ከብሪታንያ ጋር በማስተባበር ጣልያን ተሸንፎ እንዲወጣ አድርገዋል፡፡ ፋሽስቶች በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ክፍተኛ ግፍ ከመፈጸማችዉም በላይ በኤርትራና በትግራይ ወንድሞቻችን ላይ ከፍተኛ የስነልቦና ቡርቦራ በማድረግ እስካሁን ድረስ በአካባቢዉ ሰላም እንዳይሰፍን አድርገዋል::

አፄ ሀይለ ስላሴ እስከ 1966 ድረስ ስልጣን ላይ ከቆዩ በኋላ በምትካቸው የጊዜአዊ ወታደራዊ ምክር ቤት (ደርግ ወይም ኮሚቴ) ስልጣን ይዞ ወታደራዊና ሶሻሊዝም አመራር ተመሰረተ፡፡ በዛን ጊዜ ሀምሳ ዘጠኝ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ጥረት ያፈራቻቸዉ ምሁራን፣ ሚኒስትሮች፣ ጀነራሎችና ንጉሳዊ ቤተሰቦች፣ ሲገደሉ ንጉሱም በ1967 ዓ.ም በቤተ መንግስታቸው ውስጥ ተገድልዉ ተገኙ ከመባሉ ዉጭ ጥርት ያለ መረጃ የቀረበ አልነበረም፡፡

የደርግ አባላት:- ሻለቃ መንግስቱ ኃይለማሪያም ጄነራል ተፈሪ ባንቲ እና ኮሎኔል አጥናፉ አባተ

ከዚህ ክስተት በኋላ ሻለቃ መንግስቱ ሀይለ ማሪያም እንደ ኘሬዝዳንትና እንደ ደርግ ሊቀ መንበር ስልጣን ያዙ፡፡ ስልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜም ከሶቬት ህብረትና ከኩባ ጋር ወዳጅነትና ትብብር ፈጠሩ፡፡ ለ ፩፯ አመታት የቆየው ይህ ወታደራዊ አገዛዝ በተከሰተው ድርቅና በሚከተለው የህብረተሳባዊነት ርእዮት የተነሳ በዉጭና በዉስጥ ኢትዮጵያን በሚቀናቀኑ ሃይሎች ተንኮል ያዘለ ርብርብ ሃገሪቱዋን ለወያኔ ጥሏት ሄዷዋል።፡ በ1981ዓ.ም የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (ትህነግ) ከብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን)  እና ከኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ጋር አንድ ላይ ነን ብሎ ራሱን የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ)  በማለት በሀይል ተመሰረተ::  በግንቦት 1983 ላይም ወያኔ አዲስ አበባ በመግባት ኮሎኔል መንግስቱ ወደ ዙንባቢዌ ሲሰደዱ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሽፍጥ የተሞላበት ጸረ አንድነት ፕሮፓጋንዳ ከማካሄዱም በላይ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጸመ፡፡

   በ1983 ከወያኔ እና ከሌሎች ኣሻንጉሊት የፖለቲካ ድርጅቶች የተውጣጡ 87 እዉቅና ያልተሰጣቸው ተወካዮች ሃገሪቱዋን የመሰረተዉና በቁጥርም ከፍተኛ የሆነዉን አማራ ያገለለ የኢትዮጵያ ሽግግር መንግስት በማለት ህገ ወጥ መንግስት አቋቋሙ:: በዚያው አመት በኢሳያስ አፈወርቅ መሪነት የኤርትራ ህዝቦች ነፃ አውጭ ግንባር (ኤህነግ) ከ30 አመታት የአንድነት ትግል በኋላ ኤርትራን ገንጥለዉ መንግስት መሰረቱ፡፡ ሁኔታዉን  እንዲመቻች ወያኔ በዉጭ ሃይሎች እርዳታ እስከ ግንቦት 1985 ዓ.ም ድረስም በጊዜአዊነት ስም እስልጣን ላይ እንዲቆይና በ1987 ህገ ወጥ  መንግስት እንዲመሰርት ተደርጎ ኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት የሚረገጥባትና መረጋጋት የማይታይባት ሃገር ሆናለች::

ኤርትራን ሸጦ የዘር ማጥፋት በመፈጸም ኢትዮጵያን የዘረፈው ለገሰ (መለስ) ዜናዊ

በባንዳው የዜናዊ ልጅ በለገሰ ዜናዊ (በዉንብድና ስሙ በመለስ ዜናዊ) የሚመራው የትግሬ ነጻ አዉጭ ድርጅት አዲስ አበባ ከገባ በሁዋላ በሩቅና በቅርብ ካሉ ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ አማራ ሃይሎች ጋር በማበር ኤርትራን ከማስገንጠል አልፎ በህግና በአለም አቀፍ ማህበሩ ሳይቀር የኢትዮጵያ መሆኑ የታወቀዉን የአሰብ ወደብን በመሸጥና ወደ ኢትዮጵያ እንዳይከለል በማድረግ በታሪክ በኢትዮጵያ ላይ ከተፈጸሙት ክህደቶች ሁሉ የላቀዉን የጠላትነት ድርጊት ፈጽሞአል።

የትግሬ ነጻ አዉጭ ድርጅት በኢህአድግ ስም ተሸፍኖ በአማራ በአፋር በአኙአክ በኦሮሞ በሲዳማ በሱማሌና በሌሎች ንጹሃን ብሄረሰቦችና ማህበረሰቦች ላይ የዘር ማጥፋት ማሳደድ ዘረፋና ዘግናኝ ድብደባን በማካሄድ የአለም አቀፍ ህብረተሰቡን ጭምር ያሳዘነ ዘግናኝ ወንጀል ፈጽሞአል። የአቶ መለስ ዜናዊዉን መሞት ተከሎ የደቡቡ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ እንደኤሮፓ አቆጣጠር በጁላይ ፪፩፩፪ ጠቅላይ ሚንስትር ሆኑ:: በፌብሩኣርይ ፳፩፰ ሃገራችን ዉስጥ የተከሰተውን አልገዛም ባይነት ትከትሎ በራሳቸው ፈቃድ ስልጣናቸውን ለቀቁ::

አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ

በዚህ ዘረኛና ሁዋላቀር ቡድን አሰቃቂ ግፍ የተፈጸመበት የኢትዮጵያ ህዝብ በዘር ከፋፋዩን ክልል ሰብሮ በመዉጣትና  በየአቅጣጫው ትግሉን በማፋፋም ትግሉን በ2017 ከፍተኛ ደረጃ ላይ አደረሱት።

በውጭና በሃገር ዉስጥ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ልጆች አንድነታቸውን አጠናክረው ትግሉን በ2018 ከወያኔ ቁጥጥር ዉጭ አደረጉት። የኢትዮጵያ ህዝብ ተከፋፍሎ ነጻነቱን አሳልፎ እንደማይሰጥ ያወቀው ወያኔም የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ ከፍተኛ ጭፍጨፋ ፈጸመ።

የሰሜን ሸዋ ህዝብ ጥያቄ
ከግራ ወደ ቀኝ ዶክተር አብይ አህመድ አቶ ደመቀ መኮንንና አቶ ለማ መገርሳ ተጉለትና ቡልጋ አዉራጃ ጅሩ (አነዋሪ ከተማ) ዉስጥ በጉብኝታቸው ወቅት ባህላዊ ልብስ ለብሰው የተነሱት ፎቶግራፍ።

ይሁን እንጅ በአማራ በኦሮሞና በሌሎች አካባቢዎች ወጣቶች በመደራጀት ከአቅሙ በላይ በኢትዮጵያ ስም የታጠቀዉን የወያኔ ጦር መያዣ መጨበጫ ስላሳጣው እለወጣለሁ እያለ መጮህ ጀመረ።

ህዝቡ ወያኔ ካልወረደ አርፎ እንደማይቀመጥ ስለታወቀ አቶ ደመቀ መኮንንና ዶክተር አብይ አህመድ ለጠቅላይ ሚንስትርነት ቀረቡው በመጬረሻም በ2 አፕሪል 2018 ዶክተር አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሲሆኑ አቶ ደመቀ መኮንን ደሞ ም/ጠቅላይ ሚንስቴር መሆናቸው በይፋ ተነገረ። ዶክተር አብይ አህመድም ለህዝቡ በሚያደርጉአቸው ንግግሮች ሁሉ ኢትዮጵያዊነትንና የሰዉን ልጅ መብት ከፍ አድርገው በማሰማታቸው በሃገር ፍቅር ሲቃጠል የነበረውን ሰፊዉን ህዝብ ቀልብ ከመሳብም አልፈው ከፍተኛ ሙገሳና ፍቅር ተቸራቸው።

ይሁን እንጂ እሳቸው የበፊቱ ኦህዴድ የአሁኑ ኦዴፓ አባል በመሆናቸው ለዉጡን ተከትለው ከውጭ የመጡ ጥቂት ጸረ ኢትዮጵያ የኦነግ አባላት በራሳቸው በዶክተር አብይ የተሾመዉን የአዲስ አበባን ምክትል ከንቲባ በመጠቀም ወያኔአዊ ከፋፋይ ድርጊታቸውን በማንጸባረቃቸው ህዝቡ በቁጣ ሁኔታዎቹ በስርአት እንዲታረሙ በማሳሰብ ላይ ይገኛል። አብይ አህመድ የኢትዮጵያን ህዝብ መጥቀም ከፈለጉ የሚቀጥለው ምርጫ ነጻና ሃቀኛ መሆን አለበት። ታሪክ ሰርተው በሚቀጥለው ትዉልድ ለመመስገን ከፈልጉ ሜዳዉም ፈረሱም ቀርቦላቸውል::

የሃገር ፍቅር ዘፈኖችየጸረ ኢትዮጵያዉያንና የጸረ አፍሪካዉያን የጥቃት ኢላማ የሆነችዉ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ