የአድዋ ጦርንነትና የኢትዮጵያዉያን ድል

የአድዋ ጦርንነትና የኢትዮጵያዉያን ድል

የአድዋ ጦርንነትና የኢትዮጵያዉያን ድል :-  የካቲት 23 ቀን የቅዱስ ጊዮርጊስ  ለት 1888 .ም (እደ ኤሮፓ አቆጣጠር ማርች 1 ቀን 1896 .) የዓለምን የፖለቲካ አቅጣጭ በዘር ላይ የተመሰረተዉን ኢሰብአዊ ግንኙንት የለወጠ የፍትህና የመከላከል ጦርነት ኢትዮጵያ ዉስጥ አድዋ በሚባለው ቦታ ላይ ተካሄደ። ጦርነቱ የተካሄደው በእብሪት ከኤሮጳ ባህር ኣቁአርጦ በመጣው የኢጣሊያ ጦርና ዓለም ከተፈጠረች ጀምሮ ሀግሩ ዉስጥ በሚኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ መካከል ነበር። ኢትዮጵያዉያን  በጀግናና በብልህ ንጉሳቸው በዳግማዊ ምኒልክ ስር ተሰባስበው ዘመናዊ መሳሪያ ታጥቆ የመጣዉን ወራሪ ጦር ቅስሙን በመስበር የሃገራችውን ነጻነት አስከብረው መላው በባእድ አገዛዝ ስር ሚማቅቀው የአለም ህዝብ ተስፋ እንዲኖረው አድርገዋል:: ዳግማዊ ምኒልክ ኢትዮጵያ እንድታድግና ዜጎች እንዲጠቀሙ አስደናቂ የልማት ስራወችን በማከናወን ህዝቡ በሰላምና በስርአት እንዲኖር ኣድርገዋል።

በሌላ በኩል በጠላትና በደጋፊዎቹ ጸረ ሰላም እና ጸረ እኩልነት ሃይሎች ጎራ ከፍተኛ ድንቃጤን ከመፍጠሩም በላይ አንዳንዶቹም ቂም ከመያዝ አልፈው በረቀቀ መንገድ ሀዝቡን በመከፋፈል ለመጉዳት ከፍተኛ ተንኮል ሸረቡ::  የሁለተኛዉን የዓለም ጦርነት ኣጋጣሚ በመጠቀም በድጋሚ ወረራ አካሂደው አሰቃቂ የሆነ ኢሰብአዊ ድርጊት ፈጸሙ። ከዚያ ወዲህ ያለው ትዉልድ ታሪኩንንዳያዉቅና እንዳይጠነቀቅ የዉሸት ጽሁፎችን በሀገር ዉስጥና በዉጭ ሃገር ሰዎች በማጻፍና በመበተን እልሀቸዉን በረቀቀ ስልት መወጣት እንድሚፈልጉ አሁን ያለዉን የኢትዮጵያ ሁኔታ በጽሞና ለሚከታትል ስዉር ሊሆንበት አይችልም። እነዚህ ሁለት የእብሪት ዎረራወች “ታሪክ እራሱን ይደግማል” የሚለዉን እንዳንረሳ ማስጠንቀቂያ ናቸዉ። ለዚህ ነው ታሪክን መማርና ማወቅ ያለብን በተገኘው ድል ለመኩራራትና ለመጠቀም ብቻ ሳይሆን ታሪክ እራሱን መድገሙ ስለማይቀር ለመዘጋጀትም ጭምር ነው::

በዚህ በብዙ ሺህ የኢትዮጵያዉያን መሰዋእትነትተገኘው ድል ኢትዮጵያ አለኝታና ተስፋ ከመሆን አልፋ ለአፍሪካና ለሌሎች በባርነት ቀንበር ስር ለሚማቅቁ ህዝቦች የበኩሉዋን ድርሻ አበርክታለች። በዚህ የተንሳ ብዙ ሃገሮች ነጻ ሲወጡ የሰንደቅ አላማዋን ህብረ ቀለም ይወስዳሉ:: ጣሊያኖች በድጋሜ ኢትዮጵያን በወረሩበት ወቅት የኢትዮጵያኖችን ስነልቦናና ክብር ለመንካት ሰንደቅ አላማዋችንን ከተሰቀለበት ቦታ እያወረዱ ይረግጡት እንደነበረ በታሪክ ይታወቃል። ምንም እንኩአን የኢትዮጵያ ህዝብ ባይቀበላቸዉም ዛሬ የባንዳ ልጆች (ወያኔወች) ፋሽስቶች ካደረጉት ለወጥ አድርገው አባቶቻችን ተሰዉተው ያስረከቡንን ህጋዊና ታሪካዊ ሰንደቅ አላማችንን  ባእድ አካል እመሃል ላይ በመለጠፍ የኢትዮጵያ ህዝ እዉቅና ያልሰጠዉን ባንዲራ በመስቀል ተደብቆ የቆየዉን ጸረ ኢትዮጵያ ድርጊታቸዉን በዉስጥ አርበኝነት በመፈጸም የህዝቡን ስነ ልቦና ከመጉዳትም አልፈው የዲሞክራሲያዊ መብቱን በመንፈግና ነፍሰገዳዮችን በማሰማራት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣን በማካሀድ ላይ ናቸዉ።

በዚህ የተነሳ መልካቸዉን ቀይረዉ በመጡት የዉስጥ ከሃዲወችና በነጻነት ወዳዱ ሰፊዉ የኢትዮጵያ ህዝብ መካከል በአሁኑ ሰአት የከረረ ትግል በመካሄድ ላይ ነው።

የአድዋን ድል ኢትዮጵያዉያን ይደግሙታል:: ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!! አመሰግናለሁ!!

ከፋለ ዓለሙ