የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ

የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ 1925 በታሪካዊው አንኮበር ከተማ በሸዋ ክፍለ ሐገር ተወልደው በ2004 ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። አፈወርቅ ተክሌ በልጅነት ዘመናቸው የስእል ዝባሌያቸውን ያሳዩ ነበር። ብዙ ጊዜ በኬምስትሪ፣ ሂሳብ፣ ወይንም በታሪክ ክፍለ ጊዜዎች ይስሉ ነበር። በኋላም ወደ እንግሊዝ አገር ለማእድን ኢንጅነሪንግ ትምህርት ሲላኩ ፍላጎታቸው ስእል ስለነበረ እና የስእል ዝንባሌያቸው ስለታወቀ በለንደን ዩንቨርሲቲ Faculty of Fine Arts of the University of London ተቀባይነት አግኝተው ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።

በአውሮፓ ቆይታቸው የተላዩ የአርት ስራዎች ያሉባቸውን ከተሞች ጎብኝተዋል። አርቲስቱ በህይወት ዘመናቸው የላቁ ስራዎችን በመስራት አገራችንን ኢትዮጵያን በአለም አስተዋውቀዋል። በስራቸው በአለማችን ከተመረጡ ሁለት መቶ ሰዎች አንዱ በመሆን የህይወት ታሪካቸው እና የአገራቸው ሰንደቅ አላማ ወደ ጨረቃ በመወሰድ በክብር ለማስታወሻነት ከተቀብሮላቸው።

በህይወት ዘመናቸው ያከናወኗቸው ስራዎችን ለኢትዮጵያ ህዝብ በማበርከት እሳቸው በቀየሱትና ባሰሩት አልፋ ሙዝየም ውስጥ ይገኛሉ። እንዲሁም ድንቅ የሆኑ ስራዎቻቸው በተለያዩ ስፍራዎች በኢትዮጵያ እንዲሁም በአለም ዙርያ ይገኛሉ። እኝህ ታላቅ አርቲስት በሰማንያ አመታቸው ከዚህ አለም አልፈዋል።

Yehager Fikir  (ከፌስቡክ የተገኘ )

More About Laurate Afewerk Tekle