ዓባይና የመለስ ዘናዊ (ወያኔ) መርዘኛው ተንኮል

ዓባይና የመለስ ዘናዊ (ወያኔ) መርዘኛው ተንኮል

ዓባይና የመለስ ዘናዊ (ወያኔ) መርዘኛው ተንኮል
ታላቁና ማራኪው የአባይ ፏፏቴ

በሃገራችን እንዳያማህ ጥራዉ እንዳይበላ ግፋው የሚባለው በትክክል በኢትዮጵያ ሀዝብ ላይ በመፈጸም ላይ ነዉ። ዛሬ የአለምንና የኢትጵያውያንን ሀሳብና አስተየት ለመለዎጥ ወይም ለማሳሳት ወያኔ በወኪሎቹ አማካይነት የለመደዉን የዉሸት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ላይ ይገኛል። ዓባይ እንደሚጠቅመን ሆኖ ቢገደብልን እጂግ ደስ ይለናል የወያኔ ትግሬዎች ግን ሰለአባይ ከባለቤቱ ከኢትጵይያ ህዝብ በላይ የሚያቀነቅኑበት የሚጮሁበትና ሚያስመስሉበት ምክንያቱ ሌላ ነው።  እነሱ ሃገር ወዳድ? ሌሎች ኢትዮጵዉያን ሀገራቸዉ ብታድግና ብትጠቀም የሚጠሉ ሆነው አይደለም። የኢትዮጵያም ህዝብ ይህንን በደንብ ያዉቀዋል። ከእባብ እንቁላል እርግብ ኣልጠብቅም ብሎአቸዋ። ታዲያ ይኸ ሁሉ የአዞ እንባ ማፍሰስና የኢትዮጵያን ሀዝብ ጩኸት ለመቀማት የመሞከር የሚስጥሩ ምንድነው???

ወያኔ ኢትዮጵያን ለመጉዳትና ለረጂም ጊዜ እችግር ዉስጥ ለማስገባት ካስጠናቸዉ ትልልቅ ጉዳዮች (ፕሮጀችቶች) ኣንደኛዉና ዋናው የአባይ ግድብ ነው። ለዚህም ማስረጃ የሚከተሉትን ነጥቦች ተመልከቱ:

ሀ) ግድቡ የሚሰራው በጥንቃቄ የመሀል ሀግሩን ህዝብ በተለይም አማራዉንና ኦሮሞዉን እንዳይጠቅም በጣም እርቆ በጠረፍ ላይ ነዉ። ይህም በተለይ አማራዉና ሌሎች በአካባቢው የሚኖሩ ህዝቦች በምንም አይነት ለእርሻ (ለመስኖ) ለመጠጥ ለኢንዱስትሪና ለኤሌክትሪክ ኣገልግሎት እንዳይጠቀሙ ታስቦ የተሰራ ነው።

ለ) ሁለተኛዉና የተንኮል አካል ይኽ ጥቅም የማይሰጥ ነገር ግን ሆን ተብሎ በኣካባቢዉ ግጭት እንዲነሳና በዚያ ጥቅም በሌለዉ ግደብ ክዚህ በፊት በሺራሮና በባድመ ላይ እንደተደረገዉ ሁሉ የኢትዮጵያዉያንን ደም በማፍሰስ እነሱ እየዘረፉ ለመኖር የዘረጉት ወጥመድ ነው።

ግድቡ ከፍ ብሎ ከተሰራ  ወደ ምስራቅና ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ተዘርግቶ ሌሎች የሀገሪቱ ኣካሎች ይጠቀሙ ነበር ። ነገር ግን ያ ባለመፈለጉ የግድቡ ስራ ኤሌክትሪክ ለሱዳንና ለግብጽ በማመንጨትና በመሽጥ በሞኖፖልይ ይዞ ወያኔን በዝፍፊያ ለማበልጸግ ሲሆን ያም እድንበር ላይ በመሆኑ ዉዝግብ ሲነሳ በግብጽም ሆነ በሱዳን በቀላሉ የሚመታና የሚመክን ነዉ። ይህም ልክ ወደ ትግሬ የባቡር ሃዲዱ ሲዘረጋ አማራዉንና ኦሮሞዉን አግልሎ ወይም ሳይነካ ከአዋሽ ተነስቶ ዳር ዳሩን እየዞረ በአፋር በረሀ እንደ ደጋን ጎብጦ ከተጉአዘ በሁዋላ ወደ ግራ በመታጠፍ የትግሬ ከተሞችን ኣዳርሶ እንደቆመው የባቡር መንገድ አይነት መሆኑ ነው።

ሐ) ሶስተኛዉ ትልቁ የሴራው አካል በአባይ ግድብ ስም እጂግ ግዙፍ የሆነ የኢትዮጵያን ሀዝብ ገንዘብ በህጋዊ መልክ መዝርፍና ማደህየት ነው። በዚህ ግዙፍ የዝርፊያ ስልት በኑሮ ውድነት ላይ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች አርሶ ኣደሮች ነጋዴዎችና ሌሎች የህበረተሰብ ክፍሎች ካፋቸዉ እየተነጥቁ ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማይጠቅምና በራሳቸዉ ላይ ችግር ለሚፈጥር ሰራ እየተበዘበዙ (እየገበሩ) ነው።

ዓባይና የመለስ ዘናዊ (ወያኔ) መርዘኛው ተንኮልበሌላ በኩል በጣም የሚያሳዝነዉ ወያኔዎች የዘርፉትና በግልጽ አለም ካወቀዉ ገንዘብ ዉስጥ $3.00 ቢሊዮን በመለስ ሰም የተቀመጠ ሲሆን $26.70 ቢሊዮኑ ደግሞ ከኢትዮጵያ ውስጥ በህገወጥ መንገድ ተዘርፎ የሽሸ ነው። ይህ ማለት ወያኔወች በመለስ ስም ብቻ የዘርፉት ገንዘብ ኣራት (4) የአባይ ግድቦችን ሊያሰራ የሚችል በመሆኑ ኢትዮጵያ በመድማት ላይ መሆኑዋን የዉጭ ሚዲያዎ በግልጽ ጽፈዋል።

በዚህ በኢትዮጵያ ህዝብ ላብና ደም በሚንቀሳቀስ ፕሮጀችት በአካባቢዉ የሚኖሩትን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዓማሮች በማፈናቀል ትግሬዎችን ከተከዜ ማዶ እያመጡ ለማስፈርና ከዚያም አልፎ ግብጽና የዓረቡ አለም ወያኔንና ሻቢያን በዉስጥ ስለሚረዱ የኢትጵያን በተለይም የዓማራዉን ጸጋና ሃብት ለግብጽ መደራደሪያ ገጸ በረከት ለማቅረብ ወይም ኢትዮጵያንና ግብጽን በማዋጋት እንደ ሺራሮና ባድሜ ወያኔ የኢትዮጵያዉያንን ደም እየጠጣና ስጋቸውን እየበላ እንዲኖር ታስቦ የተጀመረ ነው።

መ) ሌላዉ ኣስገራሚ ሚስጥር ኣልጃዚራ ላይ ከግብጽ ከኢትዮጵያና ከእንግሊዝ አገር ተጋብዘው በተደርገው ዉይይት ላይ ግብጻዊቱዋ እዲህ ብላለች ” ግድቡ ሀገራዊ (ናሽናል) ሳይሆን ክፍለ አሁጉራዊ (ሪጂናል) መሆኑን ሙዋቹ መለስ ዜናዊ ተስማምቶበታል” በማለት የዎያኔዉ መሪ ክህደት መፈጸሙን ኣጋልጣለች (ይህንን ታሪካዊ ቪዲዮ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማየት ኣለበት። ይህም ማለት የግደቡ ባለቤቶች ሱዳን ግብጽና ሌሎች በአካባቢዉ የሚገኙ ሀገሮች ጭምር ናቸዉው ማለት ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! ወያኔ ለአንተ በታሪክ ዉሰጥ ጥሩ አስቦም ሆነ ሰርቶ ስለማያዉቅ በምትወደዉ ወንዝሕ በአባይ ሽፋን የተጋረጠብህን ተንኮል በጣጥሰህ ወያኔን በማስወገድ በሚጠቅምህ መልኩ አባይንና ሌሎች የልማት ፕሮጀችቶችን ለመገንባት ታጥቀህ ተነስ። በወያኔ ዉሸትና ፕሮፓጋንዳ እንዳትረታ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ