እጅግ አሳዛኝ ዜና!! የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ እዉቁ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ማረፉን ተረዳን

እጅግ አሳዛኝ ዜና!! የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ እዉቁ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ማረፉን ተረዳን

እጅግ አሳዛኝ ዜና!! የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ እዉቁ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ማረፉን ተረዳን
ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ

ለሚወዳት ሃገሩና ለሚሳሳለት ህዝብ ፪፯ አመት ሙሉ ሲታገልና ሲደክም ቆይቶ በቅርቡ ኢትዮጵያ ሃገራችን ወደ ሰላምና ወደ ዲሞክራ አቅንታለች በማለት እንደሌሎች በዉጭ የሚኖሩ ወገኖቹ የናፈቃትን እናት ሃገሩን ለማየት ኢትዮጵያ የገባው የቁርጥ ቀን ልጅ ደምስ በለጠ ባልታወቀ ምክንያት እቤት ዉስጥ ሞቶ እንደተገኘ ከሃገር ቤት የተገኙ መረጃዎች አስታዉቀዋል። ደምስ የኢትዮጵያዊነትን ሚስጥር በጥልቀት የተረዳና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ሲባል በወገኖቹ በአማሮች ላይ ላለፉት ፪፯ አመታት የተፈጸመዉንና ዛሬም በመፈጸም ላይ ያለዉን የዘር ማጥፋት ወንጀል ፊት ለፊት ያለማወላወል የተዋጋ ጀግና ብልህና በራሱ የሚተማመን ጋዜጠኛ ነበር።

የአማራ ህዝብ ድምጽ አልባ በነበረበትና በያለበት ግፍ በሚፈጸምበት ሰአት የደምስ ድምጽ በሞረሽ አማራ ወገኔ መሰማት ሲጀምር የጠላትን ጎራ አርበድብዶ የተጠቂዉን ሰፊ ያማራ ህዝብ ያስደሰተና ያኮራ ነበር። የደምስ ከዚህ አለም በሞት መለየት በአጠቃላይ ለሰላምና ለአንድነት ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ለሚቆረቆርለት የአማራ ህዝብ ከፍተኛ ሀዘን ነው። ለሃገርና ለህዝብ የቆሙ ጀግኖች ቢሞቱም ታሪካቸው ህያው ነው። በትዉልድ ሁሉ ሲከበሩና ሲወደሱ ይኖራሉ።

የወንድማችን የደምስ በለጠ ህይወት ከማለፉ በፊት የነበሩትን ሁኔታዎች የሚግልጸዉን ከታች ያለዉን ጽሁፍ በማንበብ በሃገርም ዉስጥ ሆነ ከሃገር ዉጭ ያለን ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን አሟሟቱ እስከሚጣራ ድረስ ሁኔታዉን በከፍተኛ ትኩረት እየተከታተልን መረጃ እንሰብስብ።

ከእዉቀት ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየቱ የተሰማንን የመረረ ሃዘን እየገለጽን የወንድማችንን ነፍስ ይማርልን ብለናል:: አሜን!!

እጅግ አሳዛኝ ዜና!! የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ እዉቁ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ማረፉን ተረዳን
አባይ ዘውዱ

ለማንኛውም የታህሳስ 12 ቀን ውሏቸውን በተመለከተ ዛሬ ያገኘሁት መረጃ ይህን ይመስላል:_
(ለምርመራው ከጠቀመ)

1_ረፋድ 4 ስዓት ላይ ፒያሳ ቀጠሮ አለኝ ብለው መነን ት/ቤት አካባቢ ካለው ከእናታቸው ቤት ወጡ፣

2_4 ስዓት ላይ ከቤት እንደወጡ ከሁለት ጓደኞቻቸው ጋር እዛው መነን አካባቢ ከሰብለ አረጋ ከተባለች ቤተሰባቸው ቤት ቡና ጠጥተው፣ለ30 ደቂቃ ያህል ከቆዩ በኃላ ስልክ ሲደወልላቸው ፒያሳ የማገኘው ሰው ስላለ በኃላ እመጣለሁ ብለው ከሰዎች ተለይተው ሄዱ።(ዘመዳቸው ሰብለ አረጋ ከተናገረችው)
(የተደወለላቸውን ስልክ ሳይ ልክ 4 ስዓት ከ28 ደቂቃ ላይ የደወለላቸው ደግሞ አንድ ጓደኛቸው ነው(ስማቸው ይቆየን)።በአካል ያግኛቸው በስልክ ብቻ ገና አልተጣራም።

3_ከቀኑ 6 ስዓት አካባቢ ስደውልላቸው ሩሲያ ኤግዚቪሽን አካባቢ እንደነበሩ ነግረውኛል።ማገኛቸው ሰዎች አሉ ብለውኛል።
(ከእህታቸው ልጅ_ከህይወት ተፈሪ ንግግር የተገኘ)

4_ከቀኑ 9 ስዓት ተኩል ወደ እናታቸው ቤት ተመለሱ፣ጥሩ የጤንነት ስሜት ላይ አልነበሩም፣የቀረበላቸውን ምግብ ቀማምሰው ነው የተውት፣የድካም ስሜት አለባቸው፣የሆኑትን ነገር ብትጠይቃቸውም ስሜታቸውን አላጋሯቸውም።
(እህታቸው ወ/ሮ አዜብ በለጠ ከተናገረችው )

5_በመሀል አቶ ወርቁ(ጓደኛቸው) እና ወ/ሮ እታፈራሁ ካሳ ወደ እናታቸው ቤት በመምጣት ጋዜጠኛ ደምስንና ቤተሰቡን ሲያጫውቱ ቆዩ፣ከተወሰነ ቆይታ በኃላ እህታቸው ወ/ሮ አዜብ በለጠ እና ልጃቸው ህይወት ተፈሪ ለስራ ጉዳይ ከቤት ወጡ።

6_ከጋዜጠኛ ደምስ በለጠ እና ከእናታቸው ጋር እነ ወ/ሮ እታፈራሁና አቶ ወርቁ ሲጫወቱ እስከ 12 ስዓት አካባቢ አብረው ቆይተዋል፣ነገር ግን በመሀል እንቅልፍ ያሸልባቸው የነበሩት ጋዜጠኛ ደምስ በግምት 11 ስዓት አካባቢ”ጠዋት ስለተነሳሁ ትንሽ ልተኛ”ብለው ወደ መኝታ ክፍላቸው ገቡ።
(ከወ/ሮ እታፈራሁ ካሳ ንግግር የተወሰደ)
7_12 ስዓት አካባቢ ከተማ ቆይተው እህታቸው ወ/ሮ አዜብ በለጠ እና የአዜብ ልጃቸው ህይወት ተፈሪ ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል።(ከህይወት ተፈሪ ንግግር የተወሰደ)

8_ከምሽቱ 1 ስዓት ተኩል ከእንቅልፋቸው ተነስተው ከክላሳቸው በመውጣት ከቤተሰብ ጋር እራት በልተዋል።
ከእራት በኃላ ከአሜሪካን አገር ከምትኖር የስራ ባልደረባቸው ጋር ስልክ ተደወለላቸው፣እያወሩ ወደ ክላሳቸው ገቡ፣ለረዥም ጊዜ አውርተዋል።ከአሜሪካን አገር ለጉብኝት አብሯቸው የመጣው የ8 ዓመት ልጃቸውም አብሯቸው ተኝቷል።

9_ዛሬ ታህሳስ 13 ቀን ከረፋዱ 3 ስዓት አካባቢ “ያለ ወትሮአቸው ተኝተው አረፈዱ”በሚል(ሁሌ ከጠዋቱ 12 ስዓት ይነሱ ነበር)እህታቸው ወ/ሮ አዜብ በለጠ ወደ ደምስ መኝታ ይገባሉ፣በሩ ክፍት ነበር፣ሲገቡ ግን ወንድማቸው በደረት ተኝተው ደም የተቀላቀለበት ትውኪያ ሲያዩ ደንግጠው ከክላሱ በመውጣት ይጮሀሉ፣ከ20 በማይበልጡ ደቂቃዎች በርካታ የጎረቤት ሰዎች ወደ ጋዜጠኛው ክፍል ይገባሉ።ከገቡት መካከል እኔ አንዱ ነኝ ያሉት ጎረቤት አቶ ሳሙኤል አብርሀ”ደምስ በጀርባቸው ተንጋለው፣ሰውነታቸው ቀዝቅዞ ነበር፣ልጃቸውም ደግሞ መሬት ላይ ቆሞ ነበር፣እኔ እጀን አሞኝ ስለነበር አልተሸከምኩም የተሸከሙት እንደነገሩኝ እጃቸው ይንቀሳቀስ ነበር”ሲሉ ተናግረዋል።
(እጃቸው ሲንቀሳቀስ ነበር ያሉትና ተሸክመው ከመኪና አስገብተው የወሰዱት ሰዎች ተፈልገው የሚጣራ ይሆናል)

10_ወደ ጴጥሮስ ሆስፒታል ስንወስደው ሀኪሞች አስታማሚዎችን አስወጥተው 30 ደቂቃ ከቆዩ በኃላ ያለምንም ህክምና አስታማሚዎችን ጠርተው “ከሞቱ እኮ ቆይተዋል”በማለት አስከሬን መለሱልን።(እህታቸው ወ/ሮ አዜብና ጎረቤት አቶ ሳሙኤል አብርሀ)

11_አስከሬናቸው ወደ እናታቸው ቤት ተመልሶ በሳጥን ገብቷል።ከጉለሌ ክ/ከተማ የመጡ የመነን አካባቢ ፖሊሶች አንዳንድ ለመረጃው ቅርበት አላቸው ብለው ያመኗቸውን ሰዎች እያነጋገሩ መረጃ ሰብስበው ለምርመራ ክፍል ሪፖርት አድርገዋል(ከተጠየቁት መካከል_አዜብ፣አቶ ሳሙኤል፣ህፃን ገላውዲዮስ•••) በሪፖርቱ መሰረት ከማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ የመጡ መርማሪዎች ከቀኑ 10 ስዓት አካባቢ የጋዜጠኛ ደምስ አስከሬን ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል እንደወሰዱ ታውቋል።አልጋቸውና ወለል ላይ ደም የተቀላቀለበት ትውኪያ ደርቋል፣ምርመራ አልተደረገበትም።

ብቻ ከአንጋፋው ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ አሟሟት ጀርባ አንዳች ሴራ ያለ ይመስላል!እንደ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ተድበስብሶ እንዳይቀር ስንል በፈጣሪ ስም ፍትህ ፍትህ ፍትህ እያልን እንለምናለን!

የሚመለከተው የህግ አካል አጣርቶ ለህዝብ እንዲያሳውቅ እንጠይቃለን!የሚዲያ ሰራተኞች ልዩ ትኩረት ሰጥታቹህ እንድትከታተሉ እንጠይቃለን!

ነፍስ ይማር!ተፅናኑ!