እነ ማሙሸት አማረ በእስር ቤት መከራቸውን እያዩ አረጋዊ በርሄ ዶ/ር በዛብህን ይዞ ከስብሃት ነጋ ጋር ስላንተ ሊደራደርልህ ነው

እነ ማሙሸት አማረ በእስር ቤት መከራቸውን እያዩ አረጋዊ በርሄ ዶ/ር በዛብህን ይዞ ከስብሃት ነጋ ጋር ስላንተ ሊደራደርልህ ነው
ሸንቁጥ አየለ

 

እነ ማሙሸት አማረ በእስር ቤት መከራቸውን እያዩ አረጋዊ በርሄ ዶ/ር በዛብህን ይዞ ከስብሃት ነጋ ጋር ስላንተ ሊደራደርልህ ነው
በአርጋዊ በርሄ የተጻፈው ጸረ አማራ ጸረ እምፔሪያሊዝም (አሜሪካ)ና ጸረ እስራኤል መረዘኛ ፕሮፓጋንዳ

አረጋዊ በርሄ የሚባል ተንኮለኛ ሸንጎ የሚባል ሥብሥብን ይመራል:: አረጋዊ በርሄ ልክ የኢትዮጵያ ህዝብ ድምጹን ለቅንጅት ሰጥቶ ቅንጅት በመላ አገረቱ እንዳሸነፈ ሲሰማ አንድ መግለጫ ሰጠ:: “ቅንጅት የኢትዮጵያን ህዝብ የመምራት የሞራል ብቃት የለዉም:: ምክንያቱም ቅንጅቱ የነፍጠኞች ስብስብ ነዉ” ሢል::

ወዲያዉ መለስ ዜናዊ በቅንጅት ላይ የማያዳግም እርምጃ ለመዉሰድ የአረጋዊ በርሄን መግለጫ በመከተል ተንቀሳቀሰ:: ስብሃት ነጋ የተባለዉ እባብም “ከአማራ ነፍጠኞች ጋር ድርድር እና የስልጣን ክፍፍል አያስፈልግም:: ቅንጅትን ፈጽሞ መደምሰስ ያስፈልጋል” ሲል ትንታኔ ሰጠ:: አረጋዊ በርሄ: መለስ ዜናዊ እና ስብሃት ነጋ አቋማቸዉ አንድ ነበር:: ሰላማዊ የሆነዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫ መደምሰስ እና በአማራ ህዝብ ላይ የጠላትነት ፖለቲካ ማራመድ:: ዛሬም አረጋዊ በርሄ አክራሪ የኢትዮፕያዊነት አቋም አላቸዉ የሚላቸዉን እነ ማሙሸት አማረን ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ለማዉጣት እየሰራ ነዉ::

ገንዘብ አቋም ይገዛል:: ግለሰቦችን ከእነ ስሜታቸዉ ጭምር:: ሆኖም አለም ላይ ለህሊናቸዉ እና ለአቋማቸዉ ኖረዉ የሚሞቱ ጥቂት ሃያላን ነብሶች አሉ:: ከነዚያ ሀያላን ነብሶች መሃከል ጀግናዉ ማሙሸት አማረ የሚመራው የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መኢአድ/ አናብስት ተጠቃሽ ናቸዉ:: እነዚህ ስብስቦች ሲያስተዉሏቸዉ ኮሳሳ ይመስላሉ:: ግን እጅግ ጽኑ እና ሀያላን ናቸዉ:: ስብስባቸዉ ከሰሜን ኢትዮጵያ እስከ ደቡብ ኢትዮጵያ ነዉ:: ስለ ኢትዮጵያ ሲያወሩ ዉለዉ ቢያድሩ አይሰለቻቸዉም:: የኢትዮጵያን ትንሳኤ እና መዳን ሀያ ስድስት አመታታ ሙሉ ሲያስሡ ኖረዋል:: አሁንም አልታከታቸዉም:: እየታሰሩም ስለ ኢትዮጵያ ይቃትታሉ::

አንዳንዴ ይገርማል:: ኢትዮጵያ ዉስጥ ባህል የሆነዉ የአዬር ባዬር ንግድ ነዉ:: ሁሉንም ነገር መሸጥ እና መግዛት እንደ ጀግንነት ይቆጠራል:: የተንኮል ፖለቲካ ማለት ይሄ ነዉ:: በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ሲያሳርድ የነበረ ሰዉዬን ተቃዋሚ ነኝ ያለ እንደሆነ ደጋፊ እና አብሮት የሚያናፋ አያጣም:: ትናትን አይታሰብም:: የአየር ባዬር ንግድ ወሳኝ ነዉ በሚል ስንኩል ባህል አገሪቱ ተወራለች:: በዚህም ቀመር መሰረት ምርጫ ቦርድ ሲጠራቸዉ እና ሲያዛቸዉ የሚስማሙትን ጥቂት ሰዎች ከመኢአድ ሰዎች መርጦ በመኢአድ ላይ ሾሟቸዋል::እነ ዶክተር በዛብህ: እነ አበባዉ መሃሪ: እነ ሙሉጌታ ለዚህ አላማ በወያኔ ተመርጠዉ የተንኮል ፖለቲካቸዉን ተያይዘዉታል:: ገንዘብ ይሰጣቸዋል:: እነሱ የህዝቡን ፖለቲካ ለወያኔ ይሸጡታል:: ከህዝቡ መሃል የሚታለል እና አብሯቸዉ የሚቆም አያጡም::

ወያኔ 122 (መቶ ሃያ ሁለት) የመኢአድ አመራሮችን አስሯቸዋል:: ማሰር ብቻ አይደለም እያሰቃያቸዉ ነዉ::  ያሰራቸዉ ደግሞ ህዝባዊዉን ተጋድሎ መርታችኋል በሚል ነዉ:: ኢሳት ሳይቀር: በዉጭ ሀገር ያሉ ሚዲያዎች ሲያናፉበት የነበረዉ ተጋድሎ ይሄ ተጋድሎ ነዉ:: የአማራ ተጋድሎን እነመራለን ብለዉ ብቅ ብቅ ያሉ ሰዎች ሁሉ ሲያናፉበት የነበረዉ ተጋድሎ ይሄ ነዉ:: ግን ስለ እነዚህ ስለታሰሩ 122 የመኢአድ አመራሮች አንድም ትንፍስ የሚል የለም:: የገማ ፖለቲካ እና የገማ ማህበረሰሰባዊ እሴት ይልሃል ይሄ ነዉ:: ሁሉም የሚሮጠዉ እኔ ተጋድሎዉን መራሁት ለማለት ነዉ እንጅ ስለሚጋደሉት እና ስለሚዋደቁት ሰዎች ግድም አይሰጠዉም::

አሁን በዉጭ ሃገር ያሉ ሚዲያዎች እና ባንዳዎች ግን እነበዛብህ እና እነ አረጋዊ በርሄን መርጠዋል:: አረጋዊ በርሄ በመኢአድ ጀግኖች ድርጅት ላይ እንዲያናፋ ተፈቅዶለታል:: ህሊናቢሱ የዉጭ ሀገር ሚዲያ እዉነት መመርመር አያዉቅም:: ያገነዉን ሁሉም መትፋት ልማዱ ነዉ:: መቻቻል ይልሃል ለነሱ እንዲህ ነው!! ግን መቻቻል እና ጠላትነትን አያዉቅም:: ብልታቸዉ የሚቀተቀጠዉ እና መከራ የሚቀበሉት አንዴ ዘራቸዉ እየተቆጠረ ሌላ ጊዜ ድርጅታቸዉ እየተጠራ ነዉ:: ዘራቸዉን ከሚጠላዉ እና ድርጅታቸዉን ሊያጠፋ የሚያደባዉ አረጋዊ በርሄ ግን ዛሬ በመኢአድ ወያኔ ከሰዬመቻቸዉ ሰንኮፎች እነበዛብህ ጋር በመሆን ይሳለቃል::

የመኢአድ ምክትል ፕረዝዳንት አቶ ዘመነ ምህረት በስደት በሰዉ አገር በየቀኑ በሚደርስበት የወያኔ ስለላ: የግድያ ሙከራ እና ብዙ ስቃዮች እሳት ላይ ተጥዶ ትግሉን አላቆመም:: ይሄ ሁሉ የሚደርስበት ከህዝቡ ተጋድሎ ጋር አብሮ ስለቆመ እና እዉነተኞቹ የመኢአድ አናብስት የሚያራምዱትን ትግል ስለሚመራ ነዉ:: እነ ኢሳት ይሄን ጀግና ማቅረብም ሆነ መጠዬቅ አይፈልጉም:: ኢሳት የሚመርጠዉ ማንን ነዉ? የወያኔ ተላላኪዉን ዶክር በዛብህን ነዉ:: ኢሳት የሚመርጠዉ እነ አረጋዊ በርሄን ነዉ:: ለምን? እኮ ለምን?

በታላቅ ህዝባዊ እንቅስቃሴአቸዉን እስር ቤት የተወረወሩትን ህዝባዊ ታጋዮች ለምን እስር ቤተ ገቡ ብሎ የሚጠይቅ ሀይል የለም::ሀገር በሆያሆዬ : እና ለዉጥ በባንዳ አሰራራ ይመጣል ብሎ ያመነዉ ወገን አሁን በተዘዋዋሪ ከወያኔ ጋር ተባብሮ እየሰራ ነዉ:: አረጋዊ በርሄ ለዉጥ ያመጣልኛል ብለህ የምታስብ ካለህ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ::ፕሮፌሰር መስፍን እንዳሉት አልምጥ ህዝብ የራሱን ሀገር በባለቤትነት ከመቆጣጠር እና እዉነተኛ ለዉጥ እንዲመጣ ከመስራት ይልቅ ለዉጥን ከባንዶች እና ከተንኮል ፖለቲካ አራማጆች አንጋጦ መጠበቅ ትርፉ እንዘጭ እንተፍ ነዉ::

እነ አረጋዊ በርሄ የሚመሩት ሸንጎም አሁን እነ ዶ/ር በዛብህን በመያዝ በጋራ እንሰራለን እያለ ነዉ:: ሸንጎ እና እነ ዶ/ር በዛብህም ስለ ሽግግር መንግስት ከወያኔ ጋር እየመከሩ መሆኑ ነዉ:: አስቡት ወያኔ እነ ዶ/ር በዛብህን ሾመ:: አረጋዊ በርሄ ስዉር እና ገሃድ ወያኔ ነዉ:: እናም ወያኔዉ ሸንጎ እና ዋናዉ ወያኔ አብረዉ ይደራደራሉ ማለት ነዉ:: በዉጭ ሀገር ያሉ ባንዳ ሚዲያዎች ጉዳዉን ያራግባሉ:: ሌላዉ ቀርቶ ኢሳት ይሄን የባንዳዎች ቅንጅታዊ ስብስብ ዋጋ ሰጥቶ የነዚህ ሰዎች አብሮ መስራት ለዉጥ እንደሚያመጣ በማስመሰል ህዝብ ያጃጅላል:: ጀግኖቹ ግን በእስር ቤት ይማቅቃሉ:: የኢትዮጵያ ህዝብ ከእነ አረጋዊ በርሄ ለዉጥ ይመጣልናል ብሎ አንጋጦ እንዲጠብቅ ፕሮፖጋንዳ ይቀልጣል:: ኢሳት እና እነ አባይ ሚዲያ የምንሰራው የነጻ ሚዲያ ስራ ነዉ ስለዚህ ሁሉንም አማራጮች ማቅረብ አለብን ካሉ እነ ዘመነ ምህረትን ለማቅረብ ለምን አልፈቀዱም? ለምን?

ለማንኛዉም ከበዛብህ እና ከአረጋዊ በርሄ ጋር የምትሞዳሞድ ሁሉ እራስህን መርምር:: ባንዳ እና የተንኮል ፖለቲካ ኢትዮጵያን አያድናትም ብቻ ሳይሆን እራስህንም ያጠፋሃል:: በዋናነት ለራስህ ደህንነት ስትል ከነ አረጋዊ በርሄ መረብ እራስህን አርቅ::

መደምደሚያዉ ግን አንድ ነዉ:: ድሉ የማን ነው? ህዝብንስ ከሩብ ምዕተ አመታታ በላይ ማታለል ይቻላል? መልሱ ህዝብን ምዕተ አመታት ሙሉ ማታለል አይቻልም:: ድሉ የህዝብ ነዉ:: የመኢአድ አናብስት ሀይላት የተንኮል እና የባንዳ ፖለቲካን ይጸየፋሉ:: ኢትዮጵያም ፈጽሞ ነጻ እስክትሆን ትግሉን አያቆሙም::

አንዲት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ የመኢአድ አናብስት ሀይላት ህልማቸዉ ናትና ይሄ እስኪሆን ስራዉ አይቆምም::