አዲስ አበባ የኹላችንም/ መጠፋፊያችን እንዳትኾን !

አዲስ አበባ የኹላችንም/ መጠፋፊያችን እንዳትኾን !

ኮማንደር አሰፋ ሰይፉ

ዐቢይና ለማ በማንጅራታችን ሲያርዱን እንተባበር!?!?

የሚያስተውል ያስተውል ግዳጁንም ይወጣ! አለበለዚያ “የአረብ ጸደይ!” የሚባለውን እናመጣለን ! ! ! የኹሉም መጀመሪያ ደግሞ ‘ዋና ከተማው’ እንደነበር፡ ያስታውስ፡፡

አዲስ አበባ የኹላችንም/ መጠፋፊያችን እንዳትኾን !
የአዲስ አበባ ህዝብ ቁጣ

 አንደኛ በየትኛውም የኦሮሚኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ውስጥ የሌለውን “ ፊንፊኔ ኬኛ!” እየተባለ ሽር_ጉዱ እየተሟሟቀ ሲመጣ፦ ‘ፊንፊኔ’ ከግማሽ ጋሻ የማትበልጥ፦ አደገኛ ወባዋ አያስቀርቤ! ፍልውሃና አካባቢዋ እነበረው ጨፌ ውስጥ “ ፊን _ ፊን” የሚልበትን ቦታ እንድነበር መረዳት ሲመጣ፦ ያዋጣል ተብሎ በ ‘አዝማችነት!’ የተተካው “ ሸገር” ሲኾን የሚያሳዝነው የዚህ አቀንቃኝ ኾኖ ብቅ ማለት የጀመረው፦ ያውም በሚያሳፍር መልክ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኾኖ ተገኘ፡፡

አሳፋሪነቱ፦ ለእኔ በኹለት ምክንያቶች ነው፡፡ አንደኛ “ ኢትዮጵያ! ኢትዮጵያ!” እያለ ከነታሪኳ እያቆላምጠ፡_ ልጆችዋም በአንድነት ሳያስደፍሯት አኩሪ መኾኑን በሚጣፍጥ አንደበቱ ሲለፍፍ ቆይቶ፦ አዲስ አበባን በማስዋብ አገር_ጎብኚዎችን መሳቢያ ሊያደጋት ማሰቡን ገልጾ _ ተጨማሪ ገንዘብ ማስገኛው ደግሞ የእምዬ ምኒልክን ታሪካዊ ጊቢ ማሳደስና ለሽርሽር አጓጉዪ በማድረግ የአገር ልጅን ብቻ ሳይኾን የውጪ ጎብኚዎችንም መሳቢያ ኾኖ የገንዘብ ማስገቢያ ተጨማሪ ምንጭ እንደሚያደርገው ሲለፍፍ ያልተደስተና ያልደገፈው ያለ አይመስለኝም፡፡

ይህ በአደባባይ ይለፈፍ እንጂ ተግባሩን አከናዋኝ ሲቋቋም “ ሸገር/አዲስ አበባን!” ማስዋብ ተብሎ ትንሽ ካላመደ በኋላ “ ሸገርን ማስዋብ!” እያሰኘ በዕውቅ ተዋናዮች ተወዳጁን ደቤ እሸቱን አቀንቃኝ ዓይነት አድርጎ በቲቪ ስብከቱን ቀጥሏል!! አስተውሉ “አዲስ አበባ!” ወጥቷል፡፡ እንዲህ ነው ማላመድ!!

“ አዲስ አበባ ( ይቅርታ! ‘ ሸገር ‘ የኦሮሞ ክልል ዋና ከተማ ነች፡፡ ከተማዋን ለማስተዳደርም ኾነ የወደፊት ዕጣዋን ለመወሰን የሚችለው የኦሮሞ ክልል መንግሥትና፦ የኦሮሞ ሕዝብ እንዲሁም በክልሉ በሕጋዊነት የሚኖሩት ብቻ ናቸው!” ማብራሪያ ያሻዋል?!

“የምኒልክ ሠፋሪዎች” ዕጣ ፈንታ!? እስካሁን አዲስ አበባ ውስጥ የድሃ ቤቶቻቸውን አፍርሰውባቸው መንገድ ላይ እንድተጣሉት ሳይኾን ቤቶቻቸውን ቀምተዋቸው ሌሎች ወገኖቻቸው ላይ ደርሶባቸው እንደነበርና በምድረስም ላይ እንዳለው “ አፈናቅሎ አስወጥቶ እምትሄድበት ሂድ ነው!! መጣል! ነው፡፡

ከዚያማ ምናለ? በቀደምት የእምዬ ምኒልክን ሃውልት አፍርሶ ከዚያ ጥንታዊ የታሪክ ቅርሶች በተለይ ከእምዬ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ማውደም ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኖች ይተርፉ ይኾን?

ታዲያ ለምን ይመላችኋል ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉትን አዲስ አበባ ውስጥ የሰገሰጓቸው? ለድምጽ? አዎን፦ ይህማ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ዋናው ግን፦ ወገኖቼ የአካባቢው ኦሮሞዎች በእምዬ ምኒልክ ቀልድ አያውቁም፡፡ ይህማ ባይኾን በ83 ሲገቡ እኮ ሃውልቱ ፈርሶ ይጠብቃቸው ነበር፡፡ የስሉልታና አካባቢ ወገኖቻችን ግን፡ “ እስቲ አባትክ ትነካዋለህ!? ብለው ነው ያተረፉት እስካሁንም ያቆዩት፡፡

ታዲያ እኛ በእነሱ አርአያ ቀጥለን አዲስ አበባንና ነዋሪዎችዋን ብቻ ሳይኾን አገራችንን ለመታደግ እንተባበራለን?

ብንወስዳቸው ይጠቅማሉ ከምላቸው ውስጥ በአባሪ ከምታገኙትና ሌላ ተጨማሪዎች፦

1_ ከኦጋዴን የተፈናቀሉትንና ( 7 _ 8፣ መቶ ሺህ የሚኾኑትን )“ ልንመልሳቸው ስንችል አዲስ አበባ አካባቢና አዲስ አበባ ውስጥ

አስፍረናቸዋል!” የተባለው አገር ክህደትና “ኦብነግ የገባሁት ትግሌን በሰላማዊ መንገድ ለመቀጠል ነው!” ያለውን ለማመቻችት መኾኑ አያጠያይቅም፡፡ ይህን ያህል ሰው ኢትዮጵያዊነቱን በመምረጥ የ“ልገንጠል!” ግላጎቱን ማምከን ሲቻል ማምቻቸት ይቅርታ ይሌለው የአገር ክህደት ወንጃል አይደለም?!

ስለዚህ አገር ውስጥም ኾነን እውጪ ያለነው የኢትዮጵያ ልጆች

_ ሃላፊነትዋን በጥሩ የተያያዘችው የሰላም ምንስትር፦

_የሰላምና የዕርቅ ኮሚሽን?

_ አባገዳዎችና ያገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የሃይማኖት ተቅዋማት በአገሪቱ ም/ቤት ( ፓርላማ) እርምጃ ቢያስወስዱ?

ውጪ ያለነው ሚና ሳይጓደል

_ ጠ፡ ሚኒስትሩ የአገራችንን ዋና ከተማ ስም በማናለብኝነት “ ሸገር!” በማለቱና በዚህም ስም በመንቀሳቀሱ በፍርድ ሊጠየቅ የሚችልበትን መንገድ የሕግ ልሂቃን ቢያስቡበት

_ በአገራችን ም/ቤትም ቢወገዝና ቢታረም፡፡ በ83 ዓም የነበረው ሸንጎ በተለይም ፊታውራሪ አመዴ ለማ ‘ ከልጆቻችን ጋር ( ሽፍቶቹ) እንወያይ፦ እንነጋገር፡፡ አፄ ዮሐንስንና ንጉሥ ምኒልክን ለጦርነት ከተሳለፉ በኋላ ያገር ሽማግሌዎች “ የናንተ የወንድማማቾች መዋጋት ለጠላት በር መክፈት ነው” ብለው ኹለቱም ለአገር ክብርና ለወገን ፍቅር ብለው ልዩነታቸውን በውል እንዳስቀሩት የማያውቅ የለም፡፡ በዚህም አገራችን በነሱ ጊዜ አልተደፈርችም፡፡

ለማና ዐቢይ ለኢትዮጵያና ለልጆችዋ አኩሪዎች፡፡ ተወዳጆችና ተደናቂዎች ነበሩ፡፡ ለማ ‘ሕዝቡ እንደሚጽልይልን እናውቃለን፡፡ ይህን ለመሥራት ኅሊናችን አይፈቅድልንም!’ ማለቱን በጥሞና አስታውሳለሁ፡፡

ዐቢይ ግን ወታደሮች ግቢው ድረስ ገብተው ከከበቡት በኋላ ያለው እርሱን ሊገድል በተወረወረው የቆሰለው ወጣት ( ይሙት ይሻር አላውቅም) የከበበውን “ዐቢይ ደኅና ነው? አደራችሁን ጠብቁት!” ነበር ያለው፡፡ ታዲያስ ጠ ሚ እንዲህ ዓይነቱን የአዲስ አበቤውን፦ ከራስ በላይ ፍቅር፡ በምን እየመልስከው ነው?

“ ሲወዱት የጠላ ሲያምኑት የከዳን ሰው

ከጂን ከጂ ይክዳው ብድሩ ይድረሰው!!” የተባለውን አታውቅም?!

አይደርስስ ይመስልሃል?

በግሌ በ66 ዓ ም የቀረበውን የድኅነት ሃሳብ በጠ ሚ እምቢ ባይነት ተቀባይ ካልተገኘ አገር ወገን ላይ ይደርሳል ብዬ ከፈራሁት የባሰ ወርዶ ልጆችዋ የማያውቁትን ስደት፦ እንኳን ሊያውቁት ሊያስቡት የማይችሉትን “ መፈናቀል”ና ውርድት _ የውኅኒ ቤቶቻችሁን ሰቆቃ አላሰብህም ነበር

በ መጋቢት ’83 የጸጥታው ጉባኤና አሜሪካ ፦ አሜሪካ ፈርዲናንድ ማርቆስን ከፊሊፒን በማውጣቱ የሕይወት መጥፋትንና የንብረት ወድመትን እንዳዳነ ፦ መንግሥቱንም አውጥቶልን፦ በአገራችን ሸንጎ የሽግግርም ኾነ ጊዚያዊ መንግሥት ቢያቋቁም ተምሳሳይ ዕድል እናገኛለን፡፡ ብዬ ነበር፡፡ የጸጥታ ጉባኤን የጨመሁት ምናልባት ተስፋ ይኖረው ይኾናል በማለት ነበር፡፡

አኹን ደግሞ የጎንደር ፋኖ ያሰማውን “ የኦሮሞ ደም ደሜ ነውን!” የአዳማው ቄሮ አስተጋብቶ “ የአማራው ደም ደሜ ነው!” እንደ ሰደድ እሳት የተቀጣጠለውን ለማ መገርሳ . ብሉይ ኪዳን ውስጥ እንደተባለው “ በ. የተጻፈ አይደለምን? ‘ ብዬ ሳልፈው

እዚህ እታሪክ አተላ ውስጥ ስትገቡብኝ በግሌ እማልችለው እሚመስል በሽታ ውስጥ ጣላችሁኝ፡፡ ይቅር ባዩ ጌታ ይህን ስላልኩ እንደኹለዬውም ይምረኛል ብዬ እተማመናለሁ፡፡

ምክንያቱም ለማና ዐቢይ፡ አባቶቻችን በጀግንነት ብቻ ሳይኾን በአርቆ አስተዋይነትና የግል ጥቅምን ከወገን ሳያስቀድሙ አኩርተው ያቆዩልንን አገራችን ደግሞ፦ ከእናንተ ጋር ደግሞ

የእናት ኢትዮጵያ ልጆች አኹንም ታምር በመሥራት የዓለምን ሕዝብ ከቅኝ ገዥዎች እንዳዳኑት አባቶቻቸው በ”ሦስተኛ ዓለምነት!” ወይም ባልለሙት አረንቋ ውስጥ ከመመደብ እናውጣለን የሚል ዕቅዴንም መና አስቀራችሁብኝ፡፡ ግድ የለም ኹሉ የሱ በሱ!

በእናንተ ላይ ይህን ያህል መተማመን የጀመርሁት ከጠላት መሣሪያነት ያመለጣችሁ መስሎኝ ነበር፡፡ የጠላት መሣሪያዎቹማ

“ ኢትዮጵያ የምትባለዋን አገር ከታሪክ ማኅደር አልፎም ከመጽሐፍ ቅዱስም እንኳን ሊያጠፏት እንደሚፈልጉ ታውቃላችሁ ብዬ ነበር፡፡ ይህንንም እንዳጀማመራችሁ ትቋቋሙታላችሁ ብዬ ነበር፡፡ “ ባአጭር የተቀጨ ረጅም ጉዞ”ን የደረሰው ግሩም ወጣት፦

“ ሰኢድ ባሬ ለተቃዋሚ ኹሉ ይረዳል!” የሚባል ነገር ሰምተን ከጓደኛዬ ጋር ሄድን፦ ‘ ኢትዮጵያን እንበታትናታለን!’ ብላችሁ ቃል ግቡና የሚያስፈልጋችሁን ኹሉ እንዳርግላችኋለን፡፡” አለን ዝርዝሩ ይቅር፡ እነርሱ ግን ነገሩ ቀፍፏቸው ‘አስበን እንነግራችኋለን!’ ብለው እንደጠፉ አጫወተኝ፡፡ ከየአቅጣጫው ‘ የዚህ ነጻ አውጪ.’ ያለ ኹሉ በዚህ ዓይነት የተጠመቀና ያለ ኾኖ አገር ወገኑን ረስቶ ጥላት እንደ መብል መጠጥ የጋተውን ይዞ በስመሣሪያነት ቀጥሏል፡፡

የኢትዮጵያ ልጆች፦ እጅግ ስሜታዊ ኾኜ በችግር ነው እዚ የደረስሁት፡፡ በእናታችንና ለርሷ ተሰውተው ባቆዩልን ስም የምለምናችሁ፦ ልክ እንደ ቅንጅት ጊዜ እየተባበራችሁ ተቋቋሙ፡፡ ከቆራጡ እስክንድር ነጋና ጓደኞቹ ጋር በመመካከር እንጂ ባልደራስን መሰል ከማቋቋም እንታቀብ፡፡

እስክንድር! አንድዬ ሃሳብ ምኞታችንን አሟልቶልን አንተም እንደሌላው ሰው ከሙሽራህና ከልጅህ ጋር በጤና የምትኖርበትን ጊዜ ያፋጥናልህ፤፡

አ አ በየክፍላተ ከተማዎች ውስጥ ፓርቲ ማቋቋም ሳትጀምሩ አትቀሩም፡፡ በርቱ!

_ ሕዝቡን ማንቀሳቀሱ የሕዝቡ ፈንታ ኾኖ

2_ አዲስ አበባ

ሀ_ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ሕዝቧ በመረጠው መተዳደር ሲገባው መነፈጉ ብቻ ሳይኾን የተጫኑባትም ባለሥልጣኖች ሕግንና የሕግን መንፈስ በማፍረስ ብቻ ሳይኾን በማወረድም ስለኾነ፦ ምንም ሟቹ በግል ጠላቱ ላይ የተጠቀመበት ኢሕጋዊ መንገድ በታሪክ ሲያዝውግዘው የሚኖር ቢኾን ያኹኑ ግን ከ5 ሚሊዮን የማይንስ ሕዝብ ላይ የተደረገውና ብሕዝቡም ላይ እንደተጫነ ስለኾነ በሕግ መጠየቅ ይገባዋል፡፡ የሕግ ልሂቃን ተነቃነቁ!

ለ_ በአባሪው ውስጥ እንደምታገኙት አዲስ አበቤዎች በተንኮልና ሕገ_ወጥነት የተነፈጉትን በመረጡት የመተዳደሪያ መብት አባሪው ውስጥ በተጠቀሰው መንገድና የጊዜ ገደብ እንዲፈጸም መተባበር፦ እንደሚያስፈልግ አሻሽላችሁም

ሐ_

አኹን ማቆም ስላለብኝ፦የእምዬ ምኒልክን ታልቁን ቤተምንግሥት ማሳደስ ስለተባለው ማንሳት ያለብኝን ላንሳና ላብቃ፦

ጠሚሩ እንደሚያሳድስ ሲንግረን ያልተደስተ ያለ አይመስልኝም፡፡ ግን እንደ ‘ ሸገር/አዲስ አበባ1’ የጭቃ ጅራፍ አለው፡፡

አገራችን ኪነ ህንጻ ልሂቃን ሞልተው ተርፈዋት ከውጪ ከማስመጣቱ በላይ የአገር ልጆች በተራ ሠራተኛነት እንኳን ዝር ማለት አይፈቀድላቸውም፡፡ ለምን?

ይባስ ብሎ መንግሥት ያቋቋመው “ የቅርስ ጥበቃና. ፦ ሃላፊ “ እንኳን እንድናማክር እንድናይም አልተፈቀደልንም!” በማለቱ ከሥራው ተባረረ፡፡ ምን እንደተሠራ ማወቅ ስላለብን ም/ቤቱም ( ፓርላማው) ሳይቀር ቤተምንግሥቱን የሚያውቁ ይዞ ማፈተሽ አገራዊ ግዴታው ነው፡፡ ጨምሩበት!

እንዳልኩት _ _ ይቅርታ፦ እባካችሁ አባሪውን ሳትሰለቹ ስሙት ፡ በተቻለ መጠን በማሕበራዊ ( ሶሺአል ሚዲያም) መገናኛም አከፋፍሉ፡፡

አገር ወገናቻንን አምላክ ይጠብቅልን፡

ኮማንደር አሰፋ ሰይፉ