አማራና ሙዚቃ

አማራና ሙዚቃ : አሃዱ አማራ ፭
Qalkidan Gebtenal (Facebook)
አማራና ሙዚቃበስነትምህርት ሳይንስ የልኅቀት መለኪያዎች እውቀት፣ አመለካከት እና ክሂል በሚል ይታወቃሉ። እውቀት አምስት የልኅቀት እርከኖች፤ አመለካከት ስድስት የልኅቀት እርከኖች እንዲሁም ክሂል ሰባት የልኅቀት እርከኖች እንዳሏቸውና በእያንዳንዱ እርከን ያለውን ዝርዝር የመመዘኛ ነጥቦችንም የዘርፉ ሊቃውንት አስቀምጠዋል። እነዚህን ዓለምአቀፋዊ በአለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ የልኅቀት መለኪያዎች በመጠቀም ሚዛኑን አማራ ከሙዚቃ አንፃር እንቃኘዋለን።

አበክረን የሙዚቃን ጎፍላ ጥበባት እንመልከት።

ምንም እንኳን በሙዚቃ መሣሪያ የተቀነባበረ ሙዚቃ ያለግጥም እና አቀንቃኝ በራሱ ሙዚቃ የሚባል ቢሆንም አንድን ሙዚቃ «ሙዚቃ» ብለን እንጠራው ዘንድ ግጥም፣ ዜማ፣የሙዚቃ መሳሪያዎች ቅንብር እና የእነዚህ ሁሉ ውህደት ከነአቀንቃኙ መሟላት ይኖርባቸዋል። በተን አድርገን እንያቸው እስኪ።

ግጥም

ግጥም ዜማዊ በሆነና በረቀቀ ሚስጢር ቁጥብነት በተላበሰ አኳኋን ሐሳብን መግለጫ ጥበብ ነው። በአማራ ሕላዌ ውስጥ ከፍተኛ ክብር የሚሰጠው ይህ የጥበብ ዘርፍ ያናለፈን ለማሞገስና ለመውቀስ፣ ዛሬን ለማሄስና የበለጠ ብሩህ ለማድረግ፣ የነገውንም በተስፋ ለመጠበቅ እና በትንቢት ለመጠቆም ስልጡኑ የአማራ ሕዝብ በሕይወቱ ሁሉ የሚጠቀምበት ጥበብ ነው።

አማራና ሙዚቃ
ዋሽንት

የአንድ ኅብረተሰብ የስልጡንነት መገለጫ ተደርጎ ከሚወሰዱ ማኅበረሰባዊ ጉዳዮች ማኅበረሰቡ ለግጥም ያለው ቀረቤታ፣ የሚሰጠው ቦታ እንዲሁም የደረሰበት ደረጃ ተጠቃሾች ናቸው። የስነትምህርት ሊቃውንት ባስቀመጡልን ዓለማቀፋዊ መስፈሪያዎች በግጥም ረገድ አማራ ሲመዘን በሦስቱም መለኪያዎች ከሚዛን በላይ ሆኖ እናገኘዋለን። ግጥምና አማራ፤ አማራና ግጥም አንዱ ለሌላኛው ክብርና ሞገስ ሆነው ኖረዋል፤ አሉ፤ ይኖሩማል። በየዘመኑ በነበሩ የአማራ ሹማምንት እና ነገስታት ጥበብ በተለይም ግጥም በቂ ከለላና እውቅና ተሰጥቶታል።

ፅናፅል tsinatsil
ፅናፅል 

እንካችሁማ፥
«ይሰቅሉኝ እንደሆን አለሁ ከፊትዎ፣
ይገርፉኝም እንደሁ ቆምሁ ከፊትዎ፣
ያለምጣም ምንይልክ ብዬ ሰደብሁዎ።»
ግጥም በአራቱም የአማራ ግዛቶች በአማራዊ ማንነት የተዋረሰን፤ አማራነታችን ያጎናፀፈን ትልቅ ጥበባዊ ሐብት ነው። እውነት ግን ግጥምና አማራን መለያየት እንዴትስ ይቻላል?

ክራር

ዜማ

ዜማ መፍጠር ከተፈጥሮ ጋር ጥልቅ ትውውቅን የሚጠይቅ፤ ትውውቁንም በሚጣፍጥ የድምፅ ፍሰትና ቃና ለጆሮ እንዲስማማ አድርጎ መቃኜት ይጠይቃል። ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ ሥም ዓለሙ የሚያውቃቸውን አዳሜ የሚደልቅባቸውን የሙዚቃ ስልቶች አምባሰል፣ ትዝታ፣ ባቲና አንቺሆዬን ረቂቅ ፍልስፍናውን፣ እምነቱን፣ እሴቱንና የላቀ ሥነልቦናዊ እድገቱን በሚያንፀባርቅ ሁኔታ ከአማራዊ እማሬ አዛንቆ የፈጠራቸው ጠቢቡ የአማራ ሕዝብ ነው። ከአማራ ሕዝብ ታሪካዊ መነሻ ከሆነው ጥንተምድር አንጎት በአሁኑ መጠሪያው ወሎ የተበረከቱልን እነዚህ የዜማ ስልቶች/ቅኝቶች አማራ የደረሰበትን የልኅቀት ሰገነት እና በአራቱም ግዛቶች ለሚኖሩ አማራ ጥበባዊ የጋራ መግባቢያ እንዲሁም የደም ትስስራቸው አስረጂዎች ናቸው። ከዜማ አንፃር በዓለምአቀፋዊ ልኬቶች የአማራን ደረጃ ስንመዝነው ከሚዛን በላይ ይሆናል። እኛው ባበረከትናቸው የሙዚቃ ቅኝቶች ስንቶቹ ታወቅበት? ስንቶችስ ሐብት አካበቱበት? ለፈጠራ ባለቤቱ ታላቁ አማራስ ምን አደረጉለት?

አማራና ሙዚቃ
ከበሮ

ሙዚቃ መሣሪያዎች

ዋሽንት፣ ማሲንቆ፣ ክራር፣ በገና፣ ነጋሪት፣ አታሞ፣ ፅናፅል፣ ከበሮ፣ ጥሩንባና የመሳሰሉት የሙዚቃ መሣሪያዎች የአማራው የዘመናት የምርምርና ጥናት ውጤቶች ናቸው። ከሸምበቆ ዝማሜ ወረብን የፈጠረ ልሂቁ አማራ ነው ከሸንበቆ የትንፋሽ መሣሪያ የሆነውን ዋሽንትን የፈጠረው። ይኸው ልሂቅ አማራ ነው በአንድ አውታር/ገመድ ብቻ እጅግ አስደሳችና ተስረቅራቂ ሙዚቃን መጫዎቻ ማሲንቆን ከነአጨዋወቱ ለዓለሙ ያበረከተው። የበገናውን ተውት። ሰው ልዕለፍጥረት መሆኑን፤ ተፈጥሮ እርስ በርስ በልዩ ቀመር የተገናኘችና የተሳሰረች መሆኗን፤ ሊያውም በሙዚቃ መሣሪያ ከልዩ የአጨዋወት ስልት ጋር በበገና ያመለከተ ሕዝብ ነው፤ አማራ! ስለያንዳንዱ ሙዚቃ መሣሪያ ቀርቶ ስላንዱ ብቻ በጥልቅ እንፃፍ ብንል ጊዜውም ቦታውም አይበቃንምና እንዲሁ አድንቀን እንለፍ።

አማራና ሙዚቃ
ማሲንቆ

ቅንብርና ውህደት

አማራ ሙዚቃን መፍጠር፣ ለሙዚቃ የሚሆኑ ልዩ ልዩ ቅመማቅመሞችን መቀመም ብቻ አይደለም የተካነው። እነዚህን ሁሉ በምን ወቅትና ሁናቴ፤ በእንዴት አይነት ስልተምት ጭምር ተከሽነው መቅረብ እንደሚኖርባቸው ያስተማረ የጥበብ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ራሱ ጥበብ የሆነ ታላቅ ሕዝብ ነው። ከተፈጥሮ፣ ወቅትና ሁናቴ ጋር የተስማማ ሙዚቃን ማቀናበርና ለዓይንና ለጆሮ ምቹ አድርጎ ማሰናዳት ዓለም በተስማማባቸው የልኅቀት መለኪያዎች ሲሰፈሩ ‪#‎ወደርየለሽ‬የሚባሉ ናቸው።

ነጋሪት:_ ከአታሞና ከድቤ የሚለይ ሲሆን መጎሰሚያ (መምቻም) አለው። እንደ ከበሮ በእጅ ሳይሆን በመጎሰሚያ ይጎሰማል። ነጋሪት ሲጎሰም ለኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ የሆነ ትኩረትን ይቀሰቅሳል ምክንያቱም ነጋሪት የሚጎሰመው በጥንት ጊዜ ሬዲዮና ሌሎች መገናና ብዙሃን ስላልነብሩ ከማእከላዊ መንግስት(ከንጉሰ ነገስቱ)የሚተላለፍውን አዋጅ ለመስማትና ለመፈጸም ለመዘጋጀት ነው።

ነጋሪት

ነጋሪት በተለያዩ ቦታዎች በመጎሰም የንጉሰ ነገስቱ መልእክት ይተላለፋል። ለምሳሌ የአድዋ ጦርነት በእምየ ምኒልክ ጊዜ የታወጀው በነጋሪት ነበር። ህዝቡም በነጋሪት የታወጀዉን መልእክት በገጠርም ሆነ በከተማ ላልሰሙት በመንገር መረጃው ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ እንዲዳረስ በማደርግ ብቻ ሳይሆን ወደ ተግባር ለመለወጥ ይዘጋጃል።

በሚገርም ሁኔታ ከላይ በተነሱ ሙዚቃ እና ነክ ነጥቦች ላይ ያለው የፈጠራ፣ የመሰናዶና ስልተምት የምጥቀት ደረጃ በአራቱም ግዛቶች የሚኖሩ አማራ ሁሉ የታላቅነታችን ምስጢር አማራ ከሚለው መጠሪያችንና ማንነታችን የተቀዳ ስለመሆኑ ጥበባዊ ምስክር ነው።

አማራና ሙዚቃ
በገና

መውጫ

ንሳማ ድምጡን ዘለግ አርገው።
«ነይማ ላሳይሽ አገሬ ሸዋን፣
እንደእናት እንዳባት ያሳደገኝን።
ነይማ ላሳይሽ አገሬ ወሎን፣
በፍቅር ኮትኩቶ ያሳደገኝን።
ነይማ ላሳይሽ ጎንደር አገሬን፣
ሁሉን ድል አድርጌ መናገሻዬን።
ነይማ ላሳይሽ ጎጃም አገሬን፣
በማርና ወተት ያሳደገኝን።»

ከ- (Zermechit Mensholela)