ትዕግሥትን እንደ ፍርሀት የቆጠረ ሁሉ ዕዳውን ለመክፈል በብርቱ ይቸገራል!

ትዕግሥትን እንደ ፍርሀት የቆጠረ ሁሉ ዕዳውን ለመክፈል በብርቱ ይቸገራል!
ትዕግሥትን እንደ ፍርሀት የቆጠረ ሁሉ ዕዳውን ለመክፈል በብርቱ ይቸገራል!

 

 

ላለፉት 30 ዐመታት በዐማራው ሕዝብ ላይ ሲፈጸም የቆየው ግፍና መከራ አሁንም እንደቀጠለ ነው። ዛሬም በጎጃም ክፍለ አገር በመተከል አውራጃ በትግሬ ወያኔ አጠራር ቤንሻንጉል ጉምዝ አካባቢ የዐማራ ቤቶች እየነደዱ ፤እህቶቻችን እዬተደፈሩ፤ ጡታቸው አዬተቆረጠ፤ የወንድሞቻችን ብልቶች አዬተስለቡ ሰለመሆኑ እዬተሰማ ነው ።

ወያኔ ኢህአደግ የዐማራውን ህዝብ በጠላትነት ፈርጆ የማጥቃት ተግባሩ አልበቃህ ብሎት በመላው አገሪቱ ከሚኖሩ አትዮጵያውያን ጋር እህቴና ወንድሜ ብሎ ተጎራብቶ፤ተጋብቶ፤ ተዋልዶ፤ ድሮና ተከባብሮ ይኖር ከነበረው ህዝብ ጋር ለማቃረናን ለማገዳደል፤ ያላሴረው ሴራ ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም ማለት አይቻልም።

ይህ የዘራው የጥላቻ ዘር ጎምርቶና አፍርቶ ባርባ ጉጉ፤ በቤኒሻንጉል፤ በገለምሶ፤ በቦርደዴ በወለጋ ወ.ዘ.ተ.ለብዙዎቹ የዐማራ ልጆች በሞት መቀጠፍ፤ሀብትና ንብረት መዘረፍና መፈናቀል ምክንያት ሆኖ አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ ቀጥሎ ይገኛል።

በቅርቡም የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር ነን የሚሉ የሠይጣን መልዕክተኞች ከዚህ ቀደም መሪያቸው በነበረው በሌንጮ ለታና ግብረአበሮቹ መሪነት በወገናችን በዐማራው ህዝብ ላይ የፈጸሙት ኢሠብዐዊ ተግባር ሳይፀፅታቸው፤ በድጋሚ ወደ ሰሜን ሸዋ በመምጣት በይፋት፤ አጣዬ፤ ማጀቴ፤ካራቆሬና በወሎ ቃሉ አውራጃ ከሚሴ እና አካባቢው ሠላማዊ የዐማራ ተወላጆች ላይ ግድያ ፈጽመዋል። ቤተ ዕምነቶችን አቃጥለዋል።

ፀረ አንድነትና ፀረ ኢትዮጵያ የጠባውን ጡት ነካሽ የሆነው ተስፋዬ ገብረአብ፤ ዐማራ ጡት ቆርጧል በሚል የዘራው እርኩስ ዘር እውን ሆኖ ይህንን የሰሞኑን የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር የጥፋት መልዕክት ምክንያቶች አንዱ ነው። የዐማራው ህዝብ ከዛሬ ነገ ሁኔታዎች ይሻሻሉ ይሆናል በሚል ትዕግስት ቢያደርግም የሁኔታዎች መባባስ ከዕለት ዕለት እየጨመረ መጥቷል።ሁሉም ነገር የራሱ ልክ አለው። ትዕግስትም የራሱ ልክ አለው።የዐማራው ትዕግስትም እያለቅ መምጣቱ መታወቅ ይኖርበታል። በኢትዮጵያችን ከእንግዲህ ወዲያ እርስ በእርስ ተከባብሮ ልማትን ማሰብ ድህነትን ማሸነፍ እንጂ አንዱ አጥቂ ሌላው ተጠቂ ሆኖ የሚቀጥልበት ዕድል በፍጹም ሊኖር አይችልም።

በመሆኑም የጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ መንግስትም ሆነ የሚመሩት የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ይህንን ፖለቲካዊ ሁኔታ ለመለወጥ በውስጡ ኦሮሞን ነጻ እናወጣለን በሚል ሽፋን ተሸፋፍነው የሚንቀሳቀሱ ሁሉም የኔ የሚል የግለኝነት አባዜ የተቆራኛቸው ጸረ አንድነት ሀይሎችን ከውስጡ መንጥሮ በማውጣት የፍትህ በትር የሚያገኙበትን መንገድ ካላመቻቸ፤ በሃገሪቱ ለሚፈጠሩት ቀውሶች ሁሉ በታሪክም ሆነ በሕግ ተጠያቂ መሆኑ አይቀሬ ነው። …

 

ሙሉ መልእክቱን ለማንበብ ይህንን መስመር ይጠቁሙ!