በጅምላ ታፍሰው የታሰሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ተጠየቀ

በጅምላ ታፍሰው የታሰሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ተጠየቀ

 በዚህ በያዝነው የአዲስ አመት መግቢያ ጀምሮ በአዲስ አበባና በአካባቢዋ በተከሰተው የጸጥታ መታወክ የተነሳ በርካታ ወግኖቻችን መገደላቸዉን መቁሰላቸዉንና መሰደዳቸዉን ሰምተናል።

በተጨማሪም በዚህ ሃላፊነት በጎደላቸው አክራሪ ስግብግብ ድርጅቶችና ግለሰቦች ቀስቃሽነት በተነሳው ሁከት ከሶስት ሺህ በላይ ንጹህ የአዲስ አበባ ወጣቶች አግባብ ባልሆነ ሁኔታ በእስር ላይ  እየተሰቃዩ እንድሚገኙ ከተለያዩ የመገናኛ አገልግሎት ሰጭ አካላት የተገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል።

የጠቅላይ ሚንስተር አቢይ መንግስት በአንድ ቀን ያለምንም ወንጀላቸዉ አፍሶ በጅምላ እያሰቃያቸዉ ያሉ ንጹሃን ወጣቶችን በአስቸኳይ ይልቀቅ ሲሉ የኢትዮጵያ የፍትህና የነጻነት ተሟጋች ሀይሎች  ጠይቀዋል :: አያይዘዉም የተቃዋሚ ድርጅቶች የአለም አቀፍ ሰበአዊ መብት ተሟጛቾች ኢትዮጵያዉያን አክቲቪስቶች እና ነጻ ሚዲያዎች በሶስት ሽህ ንጹሃን ወጣቶች ላይ የተፈጸመውን ግፍ እና ኢሰበአዊ አያያዝ በቂ ትኩረት ሰጥተዉ መረጃ በማሰባሰብ ማጋለጥ እንዳለባቸዉ አሳስበዋል።