መለስ ወያኔዎችና ቀለብ የሚሰፈርላቸው «ቋንቋ በቀል» ሆድ አደሮች

መለስ ወያኔዎችና ቀለብ የሚሰፈርላቸው «ቋንቋ በቀል» ሆድ አደሮች

ጆሮ አይሰማው የለ?!

አቻምየለህ ታምሩ
መለስ ወያኔዎችና ቀለብ የሚሰፈርላቸው «ቋንቋ በቀል» ሆድ አደሮች
ለገሰ ዜናዊ ስሙን ለውጦ መለስ ዜናዊ የሚባለው

ቀለብ የሚሰፈርላቸው «ቋንቋ በቀል» ሆድ አደሮች የመለስ ዜናዊ ሞት ዓለምን ያጎደለ፣ አፍሪካንም ተወዳዳሪ የማይገኝለት መሪ ያሳጣና ሞቱ አህጉሩን ባጠቃላ የጎዳ አድርገው ፕሮፓጋንዳ ቀለቡ ለሆነው ያገራችን ሕዝብ ይነግሩታል። ይገርማል። መለስ ዜናዊ በሕይወት ዘመኑ ትክክለኛ ውድድር ያደረገው አንዴ ብቻ ነው። ይህም በ1960ዎቹ አጋማሽ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ማህበር [University Students Union of Addis Ababa] ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሲያካሄድ ነበር።

ይህ ውድድር መለስ ዜናዊ በሕይወት ዘመኑ ለመጀመሪያም ለመጨረሻው ጊዜ ያካሄደው ሐቀኛ ውድድር ነበር። በውድድሩ መለስ ዜናዊ በአዚህ መሐመድ [አሁን ዶክተር ሆኗል] በሰፊው ተበልጦ በዝረራ ተሸንፏል። ወያኔዎችና ቀለብ የሚሰፈርላቸው «ቋንቋ በቀል» ሆድ አደሮች ዓለምን ያጎደለ ተፎካካሪ የሌለው የሌለው የሚሉት መለስ ዜናዊ በሕይወት ዘመኑ አንዴ ባካሄደው እውነተኛ ውድድር በጠባቡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማህበር ፕሬዝደንትነት ተወዳድሮ በአዚህ መሐመድ በዝረራ ተሸንፎ ከጨዋታ ውጭ የሆነውን ጉድ ነው።

በሻዕብያ አንጋሽነት የትግሬ ነጻ አውጪ ግንባር መሪ ሆኖ በዳግማዊ ምኒልክ ቤተ መንግስት ከተሰየመ በኋላ መለስ ዜናዊ ያሳየው ጠባይ ቢኖር ዓለምን ያጎደለ፣ አፍሪካንም ተወዳዳሪ የማይገኝለት መሪ ያሳጣና ሞቱ አህጉሩንም የጎዳ ሳይሆን ተሰርቶ ያላለቀ በጥላቻ የናወዙ የትግራይ ሽፍቶች አለቃ መሆኑን ነበር። ዛሬ አንድ ቅንጫቢ ነገር ካነበበና ስለአንድ ነገር ቁንጽል ወሬ ከፈረንጅ አፍ ከሰማ፤ ሌሊቱን ስለዚያ ስላነበበው ቅንጫቢ ነገር ወይንም ከፈረንጅ አፍ ስለሰማው ቁንጽል ወሬ በጉዞ በማስታወሻ ደብተሩ ሲሞነጭር ያድርና በበነጋታው ወደ አገራዊ «ፖሊሲ» ይቀይረዋል። ADLI፤ ውሀ ማቆር፤ BPR፤BSC፤ ማይክሮ ፋይናንስ፤ ውጤት ተኮር፤ ጥቃትንና አነስተኛ ተቋማት፤ልማታዊ መንግስት፤ ወዘተ የሚባሉት የወያኔ «ልማታዊ መስመሮች » ሁሉ በዚህ መልኩ «አገራዊ ፖሊሲ» የሆኑ ናቸው።

ባጭሩ መለስ ዜናዊ ማለት ያነበበውን ቅንጫቢ ነገር ወይንም የሰማውን የፈረንጅ ቁንጽል ወሬ ሁሉ ባነበባው ቅንጫቢ ነገር ላይ ተመስርቶ ወይንም የሰማውን ቁንጥል የፈረንጅ ወሬ ይዞ በማግስቱ ወደ «አገራዊ ፖሊሲ» በመለወጥ ስራ ላይ ተጠምዶ በየጊዜው እየተገለባበጠ ሲያምታታ የኖረ ለቀበሌ መሪነት እንኳ የማይበቃ የስነ መንግስት አስተሳሰብ ሲያልፍ ያለነካው ነውረኛ ግለሰብ ነበር። ቅንጫቢ «አዲስ ነገር» ባነበበ ወይንም ቁንጽል የፈረንጅ ወሬ በሰማ ቁጥር ትናንት ያወጣው «አገራዊ ፖሊሲ» ላይ የፈረመበት ቀለም ሳይደርቅ ወይንም ትናንትና ያወጣውን «አገራዊ ፖሊሲ» ፍሬ ሳያሳየን ዛሬ ባነበበው በሌላ ቁንጽል ነገር ወይንም ከፈረንጅ አፍ በሰማው ቅንጫቢ ወሬ ሲለውጥ የኖረ ባሪያ አሳዳሪና የትግራይ የአፓርታይድ አገዛዝ አምበል ነበር።

ባጠቃላይ መለስ ዜናዊ የአገር ፖሊሲ ያህልን ነገር እንደ መስሪያ ቤት ማኑዋል በየቀኑ እየቀያየረ ሲያወናብድ የኖረ፤ አይደለም በአፍሪካ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ሊሆን ቀርቶ በጠባቡ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የተማሪዎች ማህበር ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሲያካሄድ እንኳ በሰፊ ልዩነት ተበልጦ በዝረራ የተሸነፈ ጮሌ ነበር። ከምንም በላይ ደግሞ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን መለስ ዜናዊ ማለት በኢትዮጵያ ምድር ሰማያዊውን የሲዖል በር የበረገደ፤ በመሞቱና በህይወት በመኖሩ መካከል ያለው ልዩነት ሞቱ ጠቃሚ፡ ኑሮው ጎጂ የነበር ጨካኝ አውሬ ነው።