ለኢትዮጵያ መጭዉ ጊዜ የከፋ ነዉ

ለኢትዮጵያ መጭዉ ጊዜ የከፋ ነዉ :: የተኛህ ንቃ! በሀገር ቤትም በዉጭም ፈጥኖ ከመሰባሰብ ዉጭ ምርጫ የለም::
(ሸንቁጥ አየለ)
 
አሁን ለጊዜዉ ጋብ ያለ የሚመስለዉ የዘር ማጽዳት እና ማጥፋት ስራ ገና ጅማሮ እንጅ ማብቂያዉ አይደለም::ዉስጥ ዉስጡን በሶስት አቅጣጫ የተሰለፉ ሀይሎች ከፍተኛ ዝግጅት እያከናወኑ ነዉ::
 
1.በድፍረት እና በጭካኔ ክርስቲያን የሆኑ ኢትዮጵያዉያንን እረዱ ግደሉ: አጥፉ የሚሉ የጀሃዲስት ሀይሎች ማህበራዊ ሚዲያዉን እና
ሌሎች ሚዲያዎችን አጣበዋቸዋል::ከፍተኛ ዝግጅት እያደረጉም ነዉ::
 
2. አማራን ነፍጠኛን:ጉራጌን:ሲዳማን:ጋሞን:ዎላይታን:አገዉን:ሶማሌን እና ሌሎች ነገዶችን ከኦሮሚያ አጥፉ ከኦሮሚያ አጽዱ የሚሉ
ኦነጋዉያን ጮክ ብለዉ በመናገር ዝግጅታቸዉን እያጦፉት ነዉ
 
3.ኢትዮጵያን ለማፍረስ እድሜ ልኩን ሲሰራ የኖረዉ ህዉሃትም ኢትዮጵያን ከሚያፈርሱ ሀይሎች ጋር በመቆም ኢትዮጵያን ሲኦል
ለማድረግ ዝግጅቱን እያጧጧፈ ነዉ::
 
ይሄ ሁሉ እየተከናወነ የአቢይ መንግስት በኦህዴዳዉያን እና ኦነጋዉያን ቁጥጥር ስር ስለሆነ ነፍጠኛ አማራን እና ሌሎች ነገዶችን ማጽዳት የሚለዉ የጽንፈኞች መዝሙር ብዙም አደጋ ሆኖ አያሳስበዉም::እንዴያዉም በርካታ የአቢይ መንግስት ባለስልጣናት ለዚህ አላማ ተባባሪዎች እና ጉዳይ አስፈጻሚዎች ናቸዉ::ይሄም የመጭዉን ጊዜ የአደጋዉን ክብደት የባሰ ያደርገዋል::የአዴፓ/የአማራ ብልጽግና የሚባለዉ በሙታን ሰዎች የሚመራ የባንዳ ስብስብ ደግሞ እሬሳ ላይ ቆሞም ከሆዱ በዘለለ የማያስብ እየገደሉትም ዳቦዉን እያላመጠ የሚሞት ሀይል ነዉ::
 
የእኛ አሰላለፍስ እንዴት ነዉ?
 
1.በሀገር ዉስጥ በኢዜማ: በዉጭ በቀድሞ የግ7 የዲያስፖራ ትርፍራፊ ደጋፊዎች ብሎም በአዴፓ/የአማራ ብልጽግና ደጋፊዎች በዋናነትም በብልጽግ/ኦህዴድ/ የሚመራዉ የደነዘዘ ሀይል አሁንም ስልጣንን እንጂ የጠላትን ዝግጅት ፈጽሞ የተረዳ አይደለም::እነሱ ከላይ በሶስት አቅጣጫ የተሰለፈዉን ሀይል በመረዳት ህዝባችንን ከቀጣይ መጨፍጨፍ የሚታደግ አንዳችም አቅም የላቸዉም::የዚህ ዋና ምክንያቱ ደግሞ በዋናነት ይሄ ሀይል በኦህዴዳዉያን እና ኦነጋዉያን የተጠለፈ ሀይል ስለሆነ
“አማራን ነፍጠኛን:ጉራጌን:ሲዳማን:ጋሞን:ዎላይታን:አገዉን:ሶማሌን እና ሌሎች ነገዶችን ከኦሮሚያ አጥፉ” የሚለዉ መዝሙር ብዙም አያስጨንቀዉም::
 
ለዚህ ማሳያዉ ሰሞኑን በርካታ ዜጎች በማንነታቸዉ ተጨፍጭፈዉ ሳለ በአማራ ብልጽግና ስር የተሰለፉ በርካታ የአማራ ድርጅት ነን የሚሉ እንኳን ሳይቀር እንዲሁም ኢዜማዎች እና የአቢይ መንግስት ደጋፊዎች በጋራ በመሆን “አማራ ተጨፈጨፈ አትበሉ::ጉራጌ ተጨፈጨፈ አትበሉ::የዘር ማጥፋት በኢትዮጵያ አልተከናወነም::የአቢይን መንግስት ደግፉ” ሲሉ በአደባባይ ሰልፍ አድርገዋል::በርካታ ድንዙዝ ሰዎችም በዚህ ሰልፍ ላይ ተገኝተዉ አብረዉ ድንዛዜአቸዉን ለጠላቶቻቸዉ ነግረዋቸዋል::ጠላትም ይሄን በማዬት ከላይ እንደተባለዉ በሶስት አቅጣጫ የበለጠ ዝግጁትን እያጦፈ ነዉ::
 
2.በአማራ ተደራጅተና የሚሉ ልዩ ልዩ የሲቪክ እና የፖለቲካ ማህበራት አሁንም እንደተበታተኑ ነዉ::ተሰብሰቡ: አብራችሁ በጋራ ምከሩ ቢባሉም የናቴ ቀሚስ አደናቀፈኝ : እከሌን አልወደዉም የሚል ሰንካላ ምክንያታቸዉን እያቀረቡ ነዉ::በጣም የሚያሳፍረዉ ያለምርህ ከአዴፓ/የአማራ ብልጽግና ጋራ የተጋቡ የአማራ ሲቪክ ማህበራት እና የፖለቲካ ድርጅቶች ጉዳይ ነዉ::እራሳቸዉን አስተባብረዉ እና ህዝባቸዉን አደራጅተዉ በቀጣይ ከሚመጣዉ መከራ ህዝባቸዉን ለመታደግ ከመስራት ይልቅ በአቢይ መንግስት/በአዴፓ ደጋፊነት ተሰልፈዉ ለህዝባቸዉ መታረጃ የሚሆን ገጀራ መግዣ እያዋጡ ነዉ::
 
3.በኢትዮጵያ አንድነት ስም የተሰለፉት ወይም በኢትዮጵያ አንድነት እናምናለን የሚሉት ደግሞ ጭራሽ ከእዉነታዉ የተቆረጡ ናቸዉ::እነዚህ ወገኖች የተለያዩ የኢትዮጵያ ነገዶችን በማቀራረብ እና የመጣዉን አደጋ አማራዉ:ክርስቲያን ኢትዮጵያ እንዲሁም ሰለባ ሊሆን የሚችለዉ ሁሉ እንዲረዳዉ ከማድረግ ይልቅ “ፖለቲካ እና ሀይማኖት አይገናኝም” የሚል የማሞ ቂሎ ተረት ተረት ተሸክመዉ የሚዞሩ ናቸዉ::አሁንም አማራ አንበል የሚሉ እንዳሉም ሰሞኑን ባደረግሁት እንቅስቃሴ ማስተዋል ችያለሁ::ነገሩ እንዲህ ነዉ::አንድ ኢትዮጵያዊነትን አራምዳለሁ የሚል ድርጅት አመራር ጋር በመጭዉ አደጋ ላይ ለመምከር ሀሳብ እየተለዋወጥን “አይ እኛ እንኳን አማራ ወይም ክርስቲያን ከሚሉ ጋር ባንሰራ ጥሩ ነዉ::ምክንያቱም እኛ…”እያለ ብሉ ዝባዝንኬ ደረደረ::እንዲህ አይነት ድንዛዜ የወረረዉ ህዝብን ሊታደግ አይደለም እራሱም አንገቱን እንደ በግ ታንቆ ከመታረድ አይድንም::እንግዴህ ይሄ ሰዉ እራሱ ክርስቲያን አማራ የሆነ ሰዉ ነዉ እንዲህ የሚሉኝ::ይሄን ሰዉ ጠላቶቹ ቢያገኙት ምን ሊያደርጉት ይችሉ ነበር?መጀመሪያ ያርዱታል::ንብረቱን ያቃጥላሉ::የገደሉትን እሬሳዉን አይኑን ያወጡታል::ስጋዉን ይቆራርጡታል::ከዚያም ያቃጥሉታል::ለሚያመልኩት ርኩስ ሀይልም መስዋዕት አድርገዉ ያቀርቡታል::ይሄን ያልተረዳ ማሞ ቂሎ ክርስቲያን አማራ የሆነዉም ሰዉ እየተነባረረ “አይ እኛ እኳን አማራ :ክርስቲያን ከሚሉት ጋር አብረን ባንቆም..” እያለ ያላዝናል::
 
4.ክርስቲያን አባቶች: ሰባኪያን እና ምዕመን :- አሁንም የደጋዉን ትልቅነት አለመረዳት ብሎም ከመጭዉ አደጋ እራስን ለመከላከል አለመዘጋጀት ትልቅ ድንዛዜ አለ::እንዲያዉም ዋናዉ የመጭዉ ጊዜ ታራጆች አባቶች:ካህናት እና ምዕመናን መሆናችሁን ጥንቅቅ አድርጋችሁ እወቁት::
 
5.በዉጭ መንግስታት ላይ: በመግለጫ ላይ:በዲያስፖራ ላይ እና በፖለቲካ ድርጅቶች ላይ ታምኖ ከመጨዉ አደጋ እራሱን ለመከላከል ያልተዘጋጀዉ ሀይልም እጅግ ብዙ ነዉ::ሆኖም የዉጭ መንግስታም:ዲያስፖራም:የፖለቲካ ድርጅቶችም የመጣዉን አደጋ የሚያስቆሙት አይደሉም::
 
እናስ መፍትሄዉ ምንድን ነዉ?
 
የተኛህ ንቃ! በሀገር ቤትም በዉጭም ፈጥኖ ከመሰባሰብ ዉጭ ምርጫ የለም:: የአቢይ መንግስት ፈጽሞ የሚታደግህ አይሆንም:: የሚታደግህ በአምላክህ ታምነህ እራስህን ስታደራጅ እና በራስህ ክንድ ላይ ስትታመን ነዉ::ጠላቶችህ አንዳችም አቅም እና ወኔ የላቸዉም::ፈሪዎች ናቸዉ::አይንህን ቀና ብለዉ የማዬት ወኔም አይኖራቸዉ::እሳት እንዳዬ ጭድ የሚሟሽሹ ናቸዉ::ግን አንተ መሰባሰብ አለብህ:: ልዩነትህን ትተህ:የልብ ድንዛዜህን ትተህ: የግል እብጠትህን ትተህ ተሰባሰብ::በጉራጌ:አገዉ:ሲዳማ:ወላይታ እና ልዩ ልዩ ነገድ ያላችሁ በቅንነት እራሳችሁን ፈጥናችሁ በማሰባሰብ ከአማራ ሀይላት ጋር እና ከክርስቲያን ኢትዮጵያዉያን ጋር ለመሰለፍ እራሳችሁን አዘጋጁ::ክርስቲያን ኦሮሞዎች አደጋዉ እናንተም ላይ መጥቷል:: ወይ ክርስቶስን ትክዱታላችሁ አለዚያም በጨካኞች እጅ ትጠፋላችሁ::ስለዚህ እራሳችሁን ብትመረምሩ እና ቀኑ ሳይመሽ የክርስቲያን ኦሮሞዎች አደረጃጀት ብትፈጥሩ ይሻላችኋል::
 
የአማራ ህዝብ ታላቁ ሀላፊነት አሁን ወድቆበታል::በዋናነት እራሱን ማዳን ብቻ ሳይሆን ከላይ የተባሉ ልዩ ልዩ ሀይሎችን አስተባብሮ እና አግባብቶ መላዉ ኢትዮጵያን መታደግ ብሎም የአፍሪካን ቀንድ ሰላም የማድረግ ትልቅ እጅግ ትልቅ ሀላፊነት ወድቆበታል::
 
መጭዉ ዘመን እጅግ የከፋ ነዉ እና ሁሉም በአንድ ይምጣ::በአንድ ይቁም::ወደ አንድ ማዕቀፍ በመግባት አብሮ ይምከር::አብሮም ጉልበቱን ያስተባብር::የመጣዉ አደጋ የሚቆመዉ በዚህ መንገድ ብቻ ነዉ::ኢትዮጵያም የምትድነዉ በዚህ መልክ ብቻ ነዉ::
 
እግዚአብሄርም ህዝቡን ይመራ ዘንድ በጎ ፈቃዱ ይሁን !