ዓማርኛን መናገር መቻል

ዓማርኛን መናገር መቻልn

 

ዓማርኛን መናገር መቻል

Ethiopia
የአማርኛ ፊደሎች

ወያኔና መሰል ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ አማራ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጥቃት ኢላማ ያደረጉት ኢትዮጵያን ታሪኩዋን እና አማራዉን ብቻ ሳይሆን በአለም ላይ ቀዳሚ የሆነዉን የአማርኛን ፊደልና ቋንቋዉንም ጭምር ነው። ይህንን ከሚፈጽሙባቸው ጥቂት ኣስፋሪ መንገዶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል። አንደኛ እዉነተኛዉን የዓማራን ታሪክ ማጣመም ወይም የዉሸት ዉዥንብር በመዝራት አንዳንድ ሃላፊነት የጎደላቸው ብሄረሰቦች የነሱ ያልሆነዉን የአማራዉን ግእዝና አማርኛ ሆህያት የነሱ እንደሆኑ አርገው ማሶራት ።  ሁለተኛ የአማርኛ ቁዋንቁዋን ማሳደጊያና ማስፋፊያ ማእከሎች እንዳይፈጠሩ እንቅፋት መሆን። ሶስተኛ አማርኛ የማይችሉና ዉዥንብር ነዥ ጋዤጠኞችን አገልግሎት ሰጭወችንና ካድሬዎችን በመቅጠር የተሳሳተ አማርኛ እንዲናገሩና እንዲጽፉ በማድረግ ሌላዉ ትዉልድ ያን ተከትሎ የተበላሸ አማርኛ እንዲናገር ማድረግ ናቸው።

ከዚህ በማለፍ አንዳንድ ዓማራን የሚቀናቀኑ የዉጭና የሃገር ዉስጥ ሰዎች በአማርኛ ፊደል የሚጻፉትን ዓማርኛንና ግእዝን የተለያዩ እንደሆኑ ለማሳየት የሚነዙት ዉዥንብር ነው። ለምሳሌ እነዚህ ጸረ አማራና ጸረ ታሪክ ግለሰቦች የአማርኛን ፊደሎችን “ግእዝ” እያሉ በመጻፍና በመናገር እራሳቸዉንም ጭምር ሲያስገምቱ ይታያሉ። ግእዝም ሆነ ዓማርኛ የአማሮች መሆናቸዉን እያወቁ ታሪክን ለማጣመም የሚሞክሩት የሌላውን ታሪክ በማጥፋት ትልቅ የሆኑ ስለሚመስላቸዉም ጭምር ነው።

በጣም የሚገርመው አማሮች በግእዝ ፊደሎቻቸው ላይ እንደ ጨ፥ሸ፥ኸ፥ቸ የመሳሰሉትን ተጨማሪ ፊደሎች ቀርጸው (አዳብረው) የዛሬዉ አማርኛ ሊሰማ የሚችለውን ድምጽ ሁሉ በአጭር ፊደሎች እንዲጻፉ ማድረጋቸው እየታወቀ አማርኛን “ግእዝ” ብለው ሲጠሩ ምን ያህል አእምሮአቸው ለእዉነት እንደማይታዘዝና ደካሞች ሞሆናቸዉን ያመለክታል። ሌላ ማስረጃ “አንባሻ” ብሎ ለመጻፍ “ሸ”ን አማሮች በተጨማሪ የቀረጹት ፊደል መሆኑ እየታወቀ በግእዝ ነው የምጽፈው ብለው ለመናገር ይችላሉን??

ዓማርኛንና ግእዝን ለመለያትና ታሪክንና ማንነትን ለማዉደም በእንደነ ተስፋዬ ገብርአብ እና በመሰሎቹ የሚያደረገው መደነባበር የትም አያደርም። ምክንያቱም ሁለቱም የሚጠቀሙባቸው ፊደሎች አንድ ናቸው። ዛሬም በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚጻፈውም (እኔም አሁን የምጽፈው) በአማርኛ እንጂ በግእዝ አይደለም። ምክንያቱም አማሮች ግእዝን ስላሳደጉትና ተጨማሪ ፊደሎች ስለቀረጹላቸው ነው።

በነገራችን ላይ አንዳንድ ሰዎች “ቹ”ንና “ኣ”ን የሚጽፉት “ችሁ”ን ወይም “አ” ን መጻፍ ስለማይችሉ ነው። ማለት ኮምፑተር ገበታ (ኪቦርድ) ላይ እንዴት ‘አ’ ን ወይም “ችሁ”ን መጻፍ እንድሚቻል ስለማያዉቁና ስለማይችሉ ነው። በሌላ በኩል መቀሌን በትግርኛ ለመጻፍ አማርኛው “ቀ” ፊደል አናቱ ላይ ወደ ጎን በማስፈር የአማርኛን ፊደል የነሱ እንደሆነ አድርገው ለማሳየት ይዳዳቸዋል። እዚህ ላይ እኔ የምቃወመው የአማርኛ ፊደል ላይ ተቀጽላ አስቀምጠው መጠቀማቸዉን ሳይሆን የፊደሉ መሰረት አማርኛ መሆኑን እዉቅና አለመስጠታቸዉን ነው።

በሌላ በኩል አማርኛን አቀላጥፈው የሚናገሩ አማሮች ሳይቀሩ በሬዲዮና በቴለቪዥን የተሳሳተ አማርኛ በመሃይም የወያኔ ካድሬዎች ሲነገር እየሰሙ ያንኑ የተሳሳተ አማርኛ የሚናገሩ አሉ። ለምሳሌ አማርኛ የማይችሉ ትግሪኛ ተናጋሪዎች ብዙ ጊዜ “ምን አልክ?” ብለው ለመጠየቅ “ምን እያልክ ነው ያለኸው” ይላሉ። “እኔ የምለው!!” ለማለት “እኔ እያልኩ ያለሁትኝ” ወዘት በማለት አማርኛዉን ከማበላሸትም አልፈው ሌሎችን በማሳሳት የተበላሸ አማርኛና እንዲነገር በማድረግ ላይ ናቸው።

ለማንኛዉም “አማርኛን መናገር መቻል” የሚል ሃሳብ መለዋወጫ ብሎግ (Blog) በዚህ ባሉበት በእዉቀት ድረገጽ ላይ ከታች ስላለ አሰትዋጽኦ እንድታደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን።

ጤና ይስጥልኝ!!

8 thoughts on “ዓማርኛን መናገር መቻል

  1. ከዚህ በፊት ያለውን ኣስተያየት የፃፍኩት “ዓማርኛን መናገር መቻል” የሚለው ፅሁፍ የድረገፁ ዋና ገፅ ስለመሰለኝ ነው። ሌሎች ገፆችን ገፍቼ ስመለከት እጅግ ቀናና ርቱዕ የኾኑ መጣጥፎችን ኣግኝቼበታለሁ። እንዲህ ያሉትን በርቱ እያልኩ “ዓማርኛን መናገር መቻል” የሚለው ፅሑፍ ላይ ያለኝ አቋም ግን እንደፀና ነው። በመሠረቱ ኣመርኛ በ”ኣ” እንጂ በ “ዓ” ሊጀምር ኣይገባውም።

  2. የተመክሮንና የተሞክሮን (ሞከረ መከረ) ልዩነት እናዉቃለን ወይስ ሌላ ሰው ስላጸፈው ብቻ እንደነቅረዋለን?

  3. አንዳንድ ሰዎች ሲናገሩ “መጣሁኝ – አልኩኝ – በላሁኝ – ሄድኩኝ … በማለት “ኝ”ን እንደማሳረጊያ መጨረሻ ላይ ያስገባሉ። እንዴት ነው ነገሩ?

  4. ለምሳሌ በላህ የሚለውን በላክ በማለትና በተመሳሳይ ቋንቋችንን በሾኬ ዘርረው ሲጨፍሩበት ዝም ተብለው ነበር፤ በየአቅጣጫው ራስን ማዳን በሚለው ዘይቤ ጅምሩ ደግ ነው በርቱ

    1. እንደዚህ ከተናበብንና የምናዉቀዉን ለሌሎች ካካፈልን ቁዋንቁዋችንን (ቋንቋችንን) ባህላችንንና ታሪካችንን ከደላዥና ከበራዦች እናድናለን። ከዚያም በላይ ሃሳባችንን በጥራት ያለ ብዥታ ለሌሎች በማካፈል መማር ብቻ ሳይሆን ማስተማርም እንችላለን። ወንድም ግርማ ስላደረከው አስተዋጽኦ እናመሰግንሃለን። ይኸ “ህ”ን ወደ “ክ” መለወጥ ደሞ ከየት የመጣ ይሆን? ለማንኛዉም የዚህ ብሎግ አላማ ለመማማር እንጂ ሳያዉቁ የሚሳሳቱትን ለመዉቀስ አይደለም። እንዲያዉም ይሄ መድረክ አማርኛን በደንብ መናገርና መጻፍ ለሚፈልጉ ሁሉ ትልቅ ዋቢና መማሪያ መድረክ ሊሆናቸው ይችላል። መማር መማር መማር አሁንም መማር ያለዉ ማን ነበር? እግዜር ይስጠው።

  5. “ማሰላሰል” ነው የሚባለው ወይስ ማንሰላሰል? ትክክለኛው አማርኛ “ማሰላሰል” ነው::
    በአማርኛ እያሰበ ለማለት ከሆነ እያሰላሰለ ነው የሚባለው። ማሰላሰል ማለት ለረጂም ጊዜ አንድን ነገር በማውጣትና በማዉረድ መመዘንና ለዉሳኔ መዘጋጀት ወይም ነገርን ሳይናገሩ በሃሳብ መመርመር ማለት ነው።

    ሌላዉንም እንዳናሳስት በተመሳሳይ ቃል በመግለጽ የማናዉቀዉን ቃል ባንጠቀም ጥሩ ነው። ወያኔና የሱ ካድሬዎች አማርኛ ስለማይችሉ ብዙ ወጣቶች የነሱን የተዛነፈ አማርኛ በሚድያ እየሰሙ ሳያዉቁት እንደነሱ የተበላሸ አማርኛ ይናገራሉ። አንዳንድ አማሮችም ይህንኑ ወያኔ ያበላሸውን አማርኛ ሲሉት ሰምቻለሁ።

    እባካችሁ የአማርኛ የአነጋገር ለዛና ስርአት እንዳይበከል ሁላችሁም በመማርና በማስተማሩ (አስተያየት በመስጠት) አስተዋጽኦ አድርጉ። ወደፊት የአማርኛ ቁዋንቁዋ የምርምርና የእድገት ማእከል እስከሚፈጠር በዚህ በእጃችን ላይ ባለው የዘመኑ ዲጂታል እዉቀት ተጠቅመን አማርኛንም እናድነው።

Leave a Reply