የማይደክመዉ ጉልበትና የማይዝለዉ የአማራ ክንድ

የማይደክመዉ ጉልበትና የማይዝለዉ የአማራ ክንድ

ይሙት ጀግና ፈሪ ይኑር ቢሻዉ
አተላ መሸከም ይችላል ትከሻዉ
እልም ነዉ ጭልጥ ነዉ ዉሃ አይታኘክም
ጠላት ወዳጅ ላይሆን አልለማመጥም::

This image has an empty alt attribute; its file name is ለማ-ጠጁ-በቅኝት-ላይ-2-300x279.jpg

ኢትዮጵያ በዉጭና በዉስጥ ክሃዲዎች ስትጠቃ አማሮች ከሌሎች ነገዶች ጋር ደማችዉን በማፍሰስና አጥንታቸዉን በመከስከስ እራሳቸዉንም ሆነ ሌሎች ነገዶችን በመጠበቅ በነጻንት እንዲኖሩ እረድተዋል። ይሁን እንጂ ህዝባቸዉንና አገራቸዉን በመተማመን ለረጅም ጊዜ ተዘናግተዉ በዉሥጥ ቅጥረኞችና የዲሞክራሲን ጭንብል በለበሱ ዘረኞች ታሪከ ይቅር የማይለዉ ክህደትና የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመባቸዉ ነዉ፡፡ ይህም ኢትዮጵያን ለማጥፋት አማራን ኦርቶዶክስንና መሪዎቹን (ንጉሶቹን) ማጥፋት የሚለዉ እርኩስ ሃሳብ እዉን እንዲሆን ጠላት አማራ ያለበት ቦታ ሁሉ ዘምቶ ምርጥ የክፉ ቀን ለጆቹን ደም በሸዋ፣ በጎጃም፣ በጎንደርና በወሎ ያለ እርህራሄ በግፍ በመጨፍጨፍ ላይ ይገኛል። 

ይሁን እንጂ ነዉርንና ዉርደትን እንደአባቶቹ የማይቀበለዉ እንደ ጀግናዉ ለማ ጠጁ ያለዉ ትዉልድ እመንደሩ ድረስ ሊገድሉት የመጡትን ዘረኛ የታሪክ አተላወች ከነህልማቸዉ እንንዳይመለሱ አርጎ እየቀጠቀጠ ለሚወደዉ ህዝብ እየተሰዋ ነዉ። በራሱ በአማራዉና በኢትዮጵያ ህዝብ ግብር እስከ አፍ ጢሙ የታጠቀዉን ጸረ አማራና ጸረኢትዮጵያ ጦር መረሃቤቴ ላይ በማዝመት የአካባቢዉን ህዝብ ሲያሸብር ሲገል ሲዘርፍና ሲያሸማቅቅ ከነበረዉ ዘረኛ  ጋር ፊት ለፊት ገጥሞ በአድዋ እንደተሰዋዉ እንደ ፊታዉራሪ ገበየሁ ባንዶችንና ተላላኪዎቸን በማደባየት ታሪክ ሰርቶ በክብር የአረፈዉ ጀግናዉ ለማ ጠጁ ማንዉ?

ለማ ተወልዶ ያደገዉ መርሃቤቴ ከአለም ክተማ ወጣ ብላ በምትገኝ መንደር ዉሰጥ ሲሆን የአንደኛ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱንም እዚያዉ አለም ከተማ ጨረሰ። ቀጥሎም ከባህርዳር ዩኒቨርሲት የመጀመሪዉን ዲገሪ ከአገኘ በሁዋላ ሁለትኛ  ድግሪዉን ደሞ ከአዲስ አበባ ጋምቢ ቢዝነስ ኮሌጅ አግኘቶአል። ለማ ብሩህ አእመሮ ያለዉና በአካለም ጠንካራና ፈጣን በመሆኑ ብዙ ሰዎችን ያስገርም ነበር።  አማራን ለማጠፋትና ኢትጵያን ለማፍረስ ጠላት እንደሚሰራ አስቀድሞ የተረዳ ስለነበር ገና በልጅነቱ ልቦናዉን ያዘጋጀ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀንና የአማራ መከታ ነበር፡፡ ወያኔ አማራን ለሁለተኛ ጊዜ ሲወር ከሌሎች አማራ ወንድሞቹ ጋር ሆኖ ወያኔ የመርሃቤቴን ምድር እንዳትረግጥ ቀጥቶ ወደመጣችበት መልሶአታል።

ለማ ጠጁን ልዩ የሚደርገዉ ቀዳሽ፣ ጸሎተኛ፣ አራሸ፣ ተኩዋሸና በዘመናዊ ትምህርቱም የላቀና የባንከ ስራ አስኪያጅ (Manager) ሆኖ የሰራ አፍላ ወጣት ነበር። የአማራ ህዝብ በየቦታዉ ሲገደል ሲፈናቀልና ሲዋረድ ጀግናዉ ለማ ይቆጭ ነበር። በብልጽግና ስም የሚመራወ የአብይ አህመድ ከሃዲና ዘረኛ ስርአት ይህ አልበቃ ብሎት ጎንደርን፣ ጎጃምን፣ ሸዋንና ወሎን በመዉረር ጥር ወር 2016 ዓ/ም የተወለደበትና ያደገበት የነአይበገሬ ሃገር መርሃቤቴን በመዉረር ጭፍጨፋ ፈጸመ። ልበ ሙሉዉና ዉርደትን ተጠያፊዉ ለማ ጠጁ የሞቀ ቤቱንና ስራዉን አሸቀንጥሮ ጥሎ በዘረኞች የሚመራዉን ጸረአማራ ስብስብ ከክፉ ቀን ጉዋደኞቹ ጋር በመሆን መለብለብ ጀመሩ። በጀግንነቱና በማስተዳደር ችሎታዉ ቀኛዝማች ለማ ጠጁ ተብሎአል።  በዠማ ሸለቆ፣ በዞማ ተራሮች፣ በሞረትና ጅሩ ቆላዎች፣ በጃማ፣ በደራ፣ በላይ ቤትና ታችቤት መርሃቤቴ እሰክ ዘመሮ ድረስ ጠላትን አብረከረከ። ፋኖ ለማ ሁልጊዜ ለጉዋደኞቹ እሱ መሞቱ እንደማይቀር እንደሚነግራቸዉና ነገር ግን የሚያሳስበዉ የሱ መሞት ሳሆን የአማራ ትግል እንዴት እንደሚቀጥልና ግቡን አንደሚመታ ነበረ ይላሉ።

 

በኢትዮጵያ ስም የሚጠራዉ ቅጥረኛዉ ወራሪ ጦርና ፋኖ ቀኛዝማች ለማ ጠጁ ጥር 27 ቀን 2016  ሲገናኙ ልበሙሉውና ፈጣኑ ለማ ነበልባል ክነዱን ጠላት ቀመሰ። ወደሱ የመጡትን ሁሉ አልመዉ ሳይመቱ አንጠባጠባቸዉ። በሱ ኩል ያለዉን ካሰታግሰ በሁዋላ በሌላ በኩል ያሉ ጉዋድኞቹ አንድተቆረጡና አደጋላይ አንደወደቁ ሲሰማ ወደዚያ እየፎክረ ገሰገሰ። ፋኖ ቀኛዝማች ለማ ብቻዉን ቆሞ እየተኮሰ ብዙወችን አጋደመ። በመጨረሻም በአካባቢዉ ቦታ ይዞ በነበረዉ ዘረኛና ክሃዲ ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ አማራ ጦር ተመትቶ ዉድ ህይወቱን ለሚወደዉ የመርሃቤቴ ህዝብ፣ ለአማራና ለመላወ ጭቁን የኢትዮጵያ ህዝብ አሳልፎ ሰጠ። እንዲህ ነው ህዝብን መዉደድ። እንዲህ ነው ሃገርን መዉደድ። የአንበሳው ለማ ጠጁ ጀግንነትና ልበሙሉነት እጅግ አስደናቂ ነው። ታሪክና ተዉልድ እያስታወሰዉ ይኖራል። ከሃዲና ዘረኖችም ምሳቸዉን ያገኛሉ። የትግል ጉአደኞቹም በርቱ፣ የሱ መሰዋት ለናንተ ጉልበት ይሆናችሁዋል። መርሃቤቴ ብዙ ሺ ለማ ጠጁን ትወልዳለች::   

ለቤተሰቡ፣ ለቤተ ዘመዱ፣ ለመላው አማራ፣ የመርሃቤቴ ህዝብና ለፋኖ ታጋዮች ጽናቱን ይስጥልን። የወንድማችንን ነፍስ በገነት ያኑርልን።