የስብስብ ወይም የቡድን መሪዎች (Collective Leadership) ለአማራ ፋኖ አመርቂ የወደፊት እድገትና ስኬት

ባለንበት ዘመን ብዙ የአመራር አይነቶች ቢኖሩም ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት (ሦስቱ) ናቸዉ፡

፩/ አምባ ገነን (Authoritarian) መሪ

፪/ የስብስብ፣ የቡድን ወይም አሳታፊ (Collective/Participative Leadership or Democratic) መሪ

፫/ ያለ መሪ እንደፈለጉ እራስን መምራት (Delegative or Laissez-Faire) ናቸዉ።

የአማራ ፋኖ በአሁኑ ሰአት የሚገኝበትን የትግል እድገት ሂደት ከግምት ዉስጥ በማስገባት የስብስብ (የቡድን) ወይም አሳታፊ (Collective Leadership) አመራር ዘዴን በመጠቀም፣ እቅዶችን ስራ ላይ በማዋል፣ ፋኖንም ሆነ አጠቃላይ የአማራን ህዝብ ብሎም ሌሎች ኢትዮጵያዉያኖችን በመቀስቀስና በማበረታታት በሂደት አንድ ግዙፍ የተማከለ የአማራ መከላከያ ሃይል ፈጥሮ አማራዉን አጉልቶ ያሳተፈና መላዉን የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን ባለቤት ለማደረግ ነዉ። አሳታፊ (Participative or democratic) የአመራር ስልት ለተለያዩ ድርጅቶች፣ ለአሰትዳደርና ለወታደር የእዝ ሰንሰለቶች አመረቂ ዉጤት ያመጣል። በአሳታፊ አመራር ዉሰጥ ያሉ የአማራ ፋኖ ተወካይ አባላት ዉሳኔ ሲሰጡ እኩል ደረጃና እኩል አላፊነትን ይሸከማሉ። ማንም አባል በተናጠል በሚገኘዉ ዉጤት ለብቻዉ አይጠየቅም።

የስብስቡ ወይም የቡድኑ መሪዎች (Collective Leadership) ሃላፊነት አስራርና መርህ

  • የስብሰቡ ወይም የቡድኑ አባላት እንደ አንድ አካል ለመላዉ አማራ ፋኖ ኃይል ድርጅት ተጠሪ በመሆን በድርጅቱ ስም ዉሳኔዎችን ያሳልፋሉ።
  • የስብሰቡ ውይም የቡድኑ አባላት አንድ ወጥ ባልሆነ ወይም ባልተማክለ አመራር ኃይልንና ተጽእኖ ፈጣሪነትን የጋራ ያደርጋሉ።
  • ስብስቡ ዉሳኔ ሲያሳልፍ ሁሉም የስብስቡ አባላት በሂደቱ ዉሰጥ የየራሳቸዉን ድርሻ እንዲያበረክቱ ይደረጋል።
  • ስብስቡ በይበልጥ የሚያተኩረዉ በግንኙነት፣ በትብብር፣ በመተማመንና የጋራ ባለበቤትነት ላይ ነዉ።

የስብስብ ወይም የቡድን መሪነት ማለት፡ በአንድ ቡድን ዉሰጥ ለጋራ ግብ የሚሰሩ ሰዎች ማለት ነዉ።

የስብስብ ወይም የቡድን መሪዎች በዉሥጥም ሆነ በዉጭ ያሉ ሰዎች ለአንድ የጋራ አላማ በህብረት እንዲሰሩ ከማበረታታቸዉም በላይ ያላቸዉን የተለያዩ ተሰጥኦዎችንና ልምዶችን ለሚገኘዉ ስኬት ያበረክታሉ።

የስብስብ ወይም የቡድን መሪዎች ሰኬት ያለ ብዙ የተለያዩ የሃሳቦች፣ አቅጣጫዎችና የብዙ ሰዉ አሰተዋጽኦ ይገኛል ብለዉ አያስቡም።

በስብስብ ወይም በቡድን ተቐምን መምራት ከተለመደዉ (ከባህላዊዉ) የአስራረ ዘየቤ የተለየ ነዉ። 

በስብስብ ወይም በቡድን መሪነት ዉሥጥ የቡደኑ አባላት ሃላፊነትን፣ ዉሳኔ አሰጣጥን፣ ተጠያቂነትንና ሃቀኛ ተሳትፎን በአገባቡ ይጋራሉ። የስብስብ ወይም የቡድን መሪነት መሰረቱና እምነቱ ሑሉም አባላት መምራት እንደሚችሉና መምራትም እንዳለባቸዉ መገንዘቡ ነዉ።

ለስብስብ ወይም ለቡድን መሪነት መሳካት እጅግ በጣምአስፈላጊ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸዉ፣ እነዚህም፡-

  • ዕምነት
  • የጋራ ኃይል
  • ግልጽና አመርቂ ዉጤት የሚያመጣ የሃሳብ መገናኘትና መግባባት
  • ተጠያቂነት
  • አብሮ መማር
  • ልምድን መገብየትና የተገኘዉን ትምህርት መጋራት ናቸዉ።

ያለ መዋጮ፣ ተሰጥኦ፣ አመለካከትና የብዙዎች ጥረት እዉን የሚሆን ለዉጥን መጎናጸፍ ከባድ ነዉ። ተሰጥኦ ደሞ ሊገለጥ የሚችለዉ ሰዎች ያላቸዉን ሙሉ ችሎታና አቅም እንዲጠቀሙ ሁኔታዎች ሲፈቅዱላቸዉ ነዉ። የስብስብ ወይም የቡድን መሪነት ሲኖር ሰዎች “ይህንን አብረን ሰራነዉ” ይላሉ። የስብስቡ ወይም የቡድኑ የመሪነት ስኬት የሚወሰነዉ በመላዉ ስብስብ ወይም በቡድኑ አባላት እነጂ በአንድ ሰዉ እዉቀት ወይም ችሎታ አይደለም።

One thought on “የስብስብ ወይም የቡድን መሪዎች (Collective Leadership) ለአማራ ፋኖ አመርቂ የወደፊት እድገትና ስኬት

Leave a Reply