ጸረ-ሸዋ የጥላቻ ትርክት እና ኢትዮጵያን የማጥፋት ስልቶቹ

Asegedew Shemelis

ኖቬምበር 3 1:03 ከሰዓት  · 

የትግራይ የጥላቻ ሠይፍ በሸዋ ላይ፡ የተቃርኖ መነሻውና ውድመቱ

(አሰግደው ሽመልስ)

ከሦስተኛው ክፍለ ዘመን እስከ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ የነበረው የአክሱም ሥልጣኔ ወርቃማ ዘመናቱ ከግብጽና ከሮማ ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነት ጠንክሮ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አጋማሽ ላይ ነግሦ የነበረው ኤዛና የተቀረጸው የድንጋይ ላይ ጽሁፎች አንዳቸውም የትግሬ ስለመሆናቸው የሚመሰክሩ አልነበሩም፡፡ (Sergew Hableselassie, 1972) በድንጋይ ላይ የተቀረጹ የአክሱም ዘመንን ከግዕዝ ስልጣኔ ጋር የሚያዛምዱት እንደ ፕሮፌሰር ተሻለ ጥበቡ ያሉ የታሪክ ባለሙያዎች የግዕዝ ሥልጣኔ ሥሉስነትን በሞገቱበት ‹‹The Making of Modern Ethiopia: 1896-1974›› የታሪክ መጽሐፍ አማራ፣ አገው እና ትግሬ የስልጣኔው ተጋሪ እንደሆኑ በማስረጃ ያቀርባሉ፡፡

በአንፃሩ ዛሬም ድረስ በዝርፊያ የተለከፈው አዲስ የትግራይ ብሄርተኛ ሊሂቃንን ጨምሮ የአክሱም ሥልጣኔን በብቸኝነት ጠቅልለው ይወርሱታል፤ አማራና አገው በስለጣኔው ላይ የነበራቸውን የመሪነት አሻራ ጨርሶ ሲክዱ ይስተዋላል፡፡

እውነታው ግን የአክሱም ስልጣኔ የአማራ፣ የአገው፣ የትግሬ እና የሁሉም ኢትዮጵያዊ ስልጣኔ ውጤት መሆኑ ነው። ለአክሱም ሥልጣኔ መዳከም የንግድ መሥመሩ ላይ በተወሰደበት ብልጫና ጦርነት መሆኑ እሙን ቢሆንም፣ ከአማራ፣ አገው-ላስታ እና ትግሬ የጋራ ሥልጣኔ በተጻራሪው በመቆም፣ ትግሬዎች በሰሜን ምሥራቅ ሱዳን የሚገኙትን የቤጃ ማኅበረሰቦች አክሱም ድረስ በስውር አስርገው ማስገባታቸው ተጠቃሽ መሆኑን ኢብን ሃውከልን ጠቅሶ ስርግው አብራርቶታል፡፡

እንደ ስርግው ምልከታ እነዚህ የቤጃ ማኅበረሰቦች (ሰሞኑን የሱዳኑን የወደብ መሥመር ዘግተው የአልቡህራን እና ሃምዶክን መንግስት እያስጨነቁ የሚገኙት ነገዶች) በትግሬ መሪነት የሠረጉ ሲሆኑ ለውድመቱም እጃቸው እንዳለበት ይገልጻል፡፡

በዚህ መነሻ እና ሌሎች በርካታ ምክንያቶች አማራ እና አገው በአረቢያ፣ የመን እና አክሱም የዘረጉትን የየሃ እና የአክሱም የጋራ ሥልጣኔ ለማስቀጠልና ከከሃድያን ለለመጠበቅ ወደመሃል በመሳብ የመጨረሻውን የሠሎሞን ሥርወ-መንግስት ነጋሲ የድልነዓድን ልጅ መሶበወርቅን ለላስታው መራ ተክለኃይማኖት በመዳር አገር ማስቀጠል ተችሏል፡፡ ይህ እንግዲህ ከ1300 ዓመታት በፊት ጀምሮ የዳበረ ሥርዓት እራሱንም፣ ባህሉንና የዕውቀት ተቋማቱን ጭምር በማዳን እስከ 1970ዎቹ መዝለቅ ችሏል፡፡

የተቃርኖው መነሻዎች

የትግራይ ልሂቃን ጥላቻ መነሻው እና በየትኛውም ዘመን የሚነሳው የዚያ ግድም ችግኝ የክፋት ማጠንጠኛ አንከርት የሆነ ተቃርኖ በሁለት ዘውግ ሊታይ ይችላል፡ ባንድ በኩል የባሕልና ሥልጣኔ ሽኩቻ (War of Culture & Civilization) በተለየ መልኩ አክሱም ላይ የተመሠረተው የአማራ እና አገው ሥልጣኔ ሥርወ-መንግስቱን እያጠናከረ ከአክሱም ወደደቡብ አቅጣጫ በላስታና በሸዋ መንሠራራት ተቃርኖ (Dialectics of the Revival of the Zagwe & Solomonic Realm) ሲሆን በየሐ የመንግስት ሥርዓት የገነነው አክሱም በየመንና በቀይባህር ይዞታው ሲላላ፣ በሳባ ምድር ባሕሉ እና ጦሩ ሲጎለድፍ የመጨረሻው ንጉስ ድልነዓድ ወደሸዋ መጥቶ መሸሸጉ ቀዳሚው ተቃርኗቸው ነው፡፡

ከአክሱም ባህል፣ ኃይል እና ሥልጣኔ መሟሸሽ በኋላ፣ የሠለሞናዊው ሥርወ-መንግስት በይኩኖ አምላክ ሸዋ ላይ ወጋግራ ማቆሙ ቆጥቁጧቸዋል፡፡

ይሁን እንጂ፣ ታላቁ የጥንታዊ እና መካከለኛው ዘመን ታሪክ ሊቅ ሥርግው ሐብለሥላሴ፤ ‹‹በአክሱማውያንም፣ በዛግዌም ሆነ በኋላ በሸዋ የመንግስትነት አዝማናት የሥልጣኔ እና የመሻሻል ለውጦች ከመታየት በስተቀረ፣ የቅርጽና የጋራ ጠባያቸውን አልለወጡም›› ይሏቸዋል (Ancient and Medival Ethiopian History to 1270, ገጽ 292)፡፡ ይህን መቀበል ያቃተው የትግሬ ልሂቅ የኢትዮጵያን የዘመን ዝቅታ እየጠበቀ ማጥቃት ልማዱ ነውና ዘመነ-መሳፍንትን ጠብቆ በአጤ ዮሐንስ አማካኝነት ዙፋኑን ወደ አድዋ ለመመለስ የተንኮል ገመዱን መዘርጋት መርጦ ነበር፡፡ በዚህም እንግሊዞችን መርቶ አምጥቶ ጦር መዘዘ፣ ሸዋን ልክ የስፓርታው ንጉስ ሜነላውስ ትሮይን እንዳወደማት ሊያወድም እና ፍርስራሽ ሊያደርጋት ወሰነ፡፡

ኋላም ከታላቁ የዘመናዊነት መሐንዲስ አጤ ቴዎድሮስ ማግስት፣ አጤ ዮሐንስ ሸዋን ወግቶና አንበርክኮ፣ አጤ ምኒልክን ለመማረክና ግዞት ለማስገባት የማይተወው-የማይገድፈው ዕቅዱ እንደነበር ጸሐፌ-ታሪክ ተክለጻዲቅ መኩሪያ ‹‹አጤ ምኒልክና የኢትዮጵያ አንድነት›› መጽሐፍ ላይ ጽፈውታል፡፡ በዚሁ በተክለጻዲቅ መጽሐፍ ገጽ 32 ላይ፣ የ20ኛው ክፍለዘመን ሊቅ፣ ፖለቲከኛ፣ ደራሲና የታሪክ ተመራማሪ የሆኑት ነጋድራስ አፈወርቅ ስለ አጤ ዮሐንስ የተናገሩትን ለትውልድ አስፍረውታል፡፡ ‹‹አጼ ዮሐንስ ከንጉስ ምኒልክ ቢዋጉ እንደሚሸነፉ ስለተረዱት ፊታቸውን ወደመተማ አዞሩት..ካጤ ምኒልክ ጋር ተዋግቶ ተሸንፎ በገዙበት ሥፍራ እንዳይገዙ፣ ባስገበሩበት ፈንታ እንዳይገብሩ…ሞታቸውን መርጠው ወደመተማ ወረዱና ለመመለስ አይደለም ከዚያው ለመቅረት…›› ያሉትን እናገኛለን፡፡

አጤ ዮሐንስ የጦር አበጋዙን አሉላን አባሮ ራስ ኃለማርያምን በመሾም፣ በልቡ ኢትዮጵያን ከማዳን ይልቅ ሸዋን አንበርክኮ ለማውደም፣ ንጉስ ምኒልክን ለማክሰም ተንኮል ሸርቦ ባይዋጋ ተሸንፎ እዚያው መተማ በደርቡሽ እርሳስ ባልቀረ፡፡ በድል አድራጊነት ወደሸዋ ለመገስገስ ያደረገው ጦርነት በመምከኑ ሸዋን ሳያፈርስ ቀረ፡፡ የጆሮ ሎቲ አንጠልጣዩ፣ ‹ሴታሴት ነው› እየተባለ እረኛው ሁሉ የሚተርትበት ልዑል ዐልጋ ወራሽ መንገሻም ምኒልክን ለመግጠም ወኔ አጣ፡፡ሆኖም፣ በወቅቱ ሀሞታቸው ይፍሰስ፣ ልባቸው ይራድ እንጂ፣ የዚህ ሸዋን የማጥፋት ፕሮጀክት ተቀጥላ (Extension Project to the Destruction of Shewa) ክፋት ግን ከ200 ዓመታት በኋላ ነፍስ ዘርቶ፣ ሠይፍ አንግቶ ተነሳ፡፡

በሌላ ገጹ ከአድዋ ማግስት የጀመረ የጸረ-ምኒልክ ጥላሸት አዝሎ የመዞር የታናሽነት እብደት መረን ለቀቀ፡፡ ይህ በሽታም ሌላው ከትግራይ የሚነሳ የጸረ-ሸዋ ጥላቻ ጎጆ መቀለሻ ሆነ፡፡ በተለይ የሸዋን አገረ-መንግስት ምሥረታ ውጥን፣ ሰፊና ለአውሮፓ ገዢዎች የማይመች አገራዊ የአስተዳደር ሥነ-ውቅር የመጠየፍ ተቃርኖ (The Dialectics of Shewan-led Nation-State Fermentation, Foundation & Formation) ከዮሐንስ እስከ ደብረ-ጽዮን፣ ብሎም በ2014 ዓ.ም መስከረም ወር ‹ባይቶና› የተሰኘ ደቂቀ-ትህነግ ባወጣው መግለጫ ላይ ‹‹የምኒልክ ልጆች ደመኛ ጠላቶቻችን ናቸው›› በማለት የጥላቻ ገመድን ማርዘሙን ዛሬም ቀጥሎበታል፡፡ በርግጥ ባይቶና መላውን አማራ ቢሆንም በ‹ደመኛ ጠላትነት› አብዝቶ የፈረጀው፣ ከዳግማዊ ምኒልክ ጋር ማስተሣሠር የፈለገው የዘወትር ጥላቻ ማራገፊያ ሸዋን እና የሸዋ አማራን ነው፡፡ ለዚህ ሌላው ማሳያ የቀድሞው የትህነግ አባል የነበረው ገብረመድኅን አርአያ 2006 ዓ.ም የትግራይ ሕዝብ ትህነግ ላይ እንዲያምጽ ባቀረቡት ጥሪ፣ በጥፋት ሥራው አልተባበርም ያሉትን ትግሬዎች ሁሉ ‹‹ትግራዋይ ሸዋዊ›› (የትግራይ ሸዋ) እያለ ይፈርጅበት እንደነበር ጽፎታል፡፡ እንግዲህ ይህ ፍረጃ በዋናነት የሚያሳየው፣ የሸዋን በነዱት የማይነዳ፣ በገፉት መንገድ ሁሉ ልጓዝ የማይል ምክንያታዊነት እንደ መጥፎ ባሕል በመውሰድ ትህነግ ‹አልተባበርህም› ያሉትን ጥቂት የትግራይ ሀቀኞች የሚጠላበትን ጽንፍ ‹‹ትግራዋይ ሸዋዊ›› በማለት ይገልጣል፡፡

እጅግ አደገኛውን ክህደት ግን የኢትዮጵያን ሚሌኒየም ምክንያት በማድረግ በ2000 ዓ.ም የኢሕአዴግ ልሳን የሆነው ‹አዲስ ራዕይ› መጽሔት 2ኛ ዓመት፣ ቅጽ 2 ልዩ ዕትም ላይ የመጽሔቱ ዓምደኛ ታደሰ ገ/ወልድ (የመለስ ዜናዊ የብዕር ስም) ‹አዲሱ ሚሌኒየም፣ የኢትዮጵያ ህዳሴ› የተሰኘ ጽሁፍ አትሞ ነበር፡፡ ጸሐፊው እንደሚሉት ‹‹ያለፈውን ሁለት ሺህ አመት ባጭሩ እንቃኝ ብንል ጎልቶ የሚወጣው መሰረታዊ ሃቅ በመጀመሪያው ሺህ ዓመት አገራችን በስልጣኔ በመጀመሪያው ረድፍ ከሚገኙ የዓለም አገሮች መካከል እንደነበረች፣ በሁለተኛው ሺህ አመታት ግን በማያቋርጥ ማሽቆልቆል ሂደት›› (አዲስ ራዕይ፤ ገጽ 6) ውስጥ እንደተነከረች ያብራራል፡፡ እዚህ ጽሁፍ ውስጥ በመሠረታዊነት ማስጨበጥ የተፈለገው የኢትዮጵያ ሁኔታ በሁለት ምሕዋር ተተክሎ እንደሚኳትን የሸማኔ አንከርት ባለበት ተወስኖ መመላለሱ ሳይሆን ሌሎች ሁለት ቁልፍ ክህደቶችን ማስተዋወቅ ነበር፡፡

የመጀመሪያውና በጥንቃቄ የቀረበው ‹የአክሱም ሥልጣኔ የትግሬ ብቻ ነው፣ ይሕ የመጀመሪያው አንድ ሺህ ዓመት የትግሬ የከፍታ ዘመን ነው› የሚለው ነው፡፡እንደማሳያ፣ በዚሁ አዲስ ራዕይ መጽሔት አቶ መለስ ዜናዊ ባዘጋጁት ጽሁፍ ውስጥ፣ ከዛግዌ ሥርወ-መንግስት በቀጥታ ወደጎንደር ሥልጣኔ በመሻገር፣ ከጥሎም የዘመነ-መሳፍንትንና የ19ኛውን እና 20ኛው መቶ ክፍለ-ዘመንን ‹‹አውሮፓውያኑ የኢንዱስትሪ አብዮት ለማካሄድ የሚያስችላቸውን የተለያየ ኤኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ለውጦችን ሲያካሂዱ፣ ኢትዮጵያ ግን የኋሊት ትጓዝ ጀመረች›› በማለት ጥላሸት ለመቀባት በእንቅብ ሙሉ ይዘው ዞረዋል፡፡

እንግዲህ ብዙዎቹ የአውሮፓ አገሮች በኋላቀርነት እና በቅኝ-ግዢ ሲኳትኑ፣ ‹የኋሊተ ጉዞ›፣ ‹የማሽቆልቆል ታሪክ› እና ‹የውድቀት ክፍላተ-ዘመናት› በተባሉባቸው ጊዜያት የአጼ ቴዎድሮስ የቴክኖሎጂ አብዮት ችቦ እና የዳግማዊ አጼ ምኒልክ የዘመናዊነት እና የዘመናዊት ኢትዮጵያ ግንባታ ተግባራዊ ሥራን መካድ ሌላው የቆረቆዘ የታናናነት መነሾ ሆኖ ለታሪክ ተቀምጧል፡፡ ምክንያቱም፣ ከላስታና ላሊበላ የጀመረው የዕውቀት ሥርዓትና ፈርጅ በጣና ገዳማት ቀጥሎ፣ በጎንደር የንጉስ ፋሲለደስን ጉምቱ ዘመን ተከትሎ በሸዋ ከተሠራው ዘርፈ ብዙ ውቅር አንጻር በየትኛውም የወቅቱ የዓለም ሥልጣኔ ካለመሠረታም በላይ፣ የቀደመው ሚሌኒየምን አወድሶ፣ ይህን ለመርገም ከመነሳት በላይ መረገም አይገኝለትም፡፡

የትግራይ ወራሪ ልሒቅ ጥላቻው ኢትዮጵያን፣ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን እና ጭፍን ፀረ-አማራ ሆኖ ሳለ፣ በተለይ ሸዋ በአማራ ፖለቲካ፣ የዕውቀት ሥርዓትና የመንግስት ተረክ ውስጥ እምብርት እንደሆነ በመረዳታቸው (Core Inner Layer) ከ1983 ዓ.ም በኋላ የሸዋ የሚመስሉ ምልክቶችን ማጥፋት፣ በየሚዲያው በነጋ እና በጠባ ቁጥር ‹የሸዋ ገዢና በዝባዥ መደብ› እያሉ ህዝቡን ያስፈጁበት፣ ከኦነግ ጋር በመተባበር ንጹሃንን የፈጁበትና ኦነግን ለመነጠል ሲባል የሸዋ አማራዎች የተጨፈጨፉበት፣ እንደ ደራ ያሉ የሸዋ አካል የሆኑ ወረዳዎችን ‹ትግል የተጀመረበት ቦታ› በሚል ከባህል፣ ማንነታቸውና ቋነቋቸው እየነጠሉ ማንገላታት የ30 ዓመታት ትግሬ-ወለድ መርገምት ሽራፊዎች ናቸው፡፡

ይህ ትግራይ-በቀል ጥላቻ እስከ ዛሬ ድረስም የሸዋን ኤኮኖሚ፣ ሥልጣኔ፣ የባሕል ውቅር፣ የአርበኝነትና የማኅበረሰብ ሥሪት የመበተኛ የጥላቻ ሠይፍ ሆኖ አገልግሏል፡፡

ጸረ-ሸዋ የጥላቻ ትርክት እና የሸዋን አብርሆት የማዳከሚያ ስልቶቹ

ወራሪና አሸባሪው የትግራዩ ትህነግ ሸዋን ካወደመበት አስከፊ ገጽታው የሸዋን አብርሆት ማዳከም (The Destruction of Shewan Enlightenments) ነው፡፡ የሸዋ ሥርወ-መንግስት (ከ13 እስከ 16ተኛው ክ/ዘመን) የመካከለኛው ዘመን፣ እንዲሁም ከ17ኛው እስከ 20ኛው ክ/ዘመን አጋማሽ ድረስ የኢትዮጵያን ስልጣኔ ይወክላል፡፡ በዚህ ዘመን የክርስትና ኃይማኖት በአገሪቱ የተስፋፋበት፣ በመካከለኛው ክፍለ-ዘመንም ሆነ በዘመናዊቷ የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥም ጉልህ ሚና የነበራቸው የአፄ ዘርዓያዕቆብ፣ አፄ ሕዝብናኝ፣ መርዕድ አዝማች አመኃየስ፣ ንጉሥ አምደ-ጽዮን፣ መርዕድ አዝማች ወሠንሰገድ፣ ንጉሥ ሣህለሥላሴ ዳግማዊ አጼ ምኒልክ፣ ፊታውራሪ ገበየሁ፣ ሸዋረገድ ገድሌ፣ ተስፋ ገብረሥላሴ ዘብሔረ ቡልጋ፣ ኪዳነወልድ ክፍሌ፣ ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ በጥቂቱ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ከሸዋ የወጣውን ሁሉ ማጠልሸት፣ የዕውቀት አበርክቶውን እና ታሪኩን መቅበር የትህነግ ሕልሙ ነውና ነገሥታቱን ‹በጨቋኝነት›፣ ‹በወራሪነት›፣ ‹በጠቅላይነት› እና ‹አድኃሪነት› በመፈረጅና በማንቋሸሽ፣ የዕውቀት ቀንዲሎቹን በማንኳሰስ፣ እና ብርቱ ሥም ያላቸውን ከመደበኛው የታሪክ ማዕድ ሊያሸሻቸው ሞክሯል፡፡ በተለይ በዘመናዊ የትምሕርት ሥርዓቱ ውስጥ የጦርነት ታሪክ (Military History) ላይ ብቻ በማተኮር የአገረ-መንግሥት ምሥረታ፣ የረጅም መሥመር ዓለም-አቀፍ ንግድ፣ የአገር አንድነት ውጥኖቻቸውንና የፍትሕና ዕውቀት አበርክቷቸውን መቅበር ዋነኛው ሴራ ነበር፡፡

በመጀመሪያው እና በሁለተኛው የጣሊያን ወረራ ኢትዮጵያን ያስከበሩ፣ ጠላት በመጣ ጊዜ ሁሉ ቀድመው የተሠለፉትን የታሪክ ሕዳግ (Historical Peripheries) ላይ እንዲቀመጡ ያልሠራው ስሌትና ክፋት አልነበረም፡፡

በመረብ ወንዝ ዳርቻ ከሚኖሩት የከቤሳ ማኅበረሰቦች፣ ትግሬዎችና አማራዎችን የማንነት መመልከቻ መንገዶችን ለማጥናት ከ1986-87 ዓ.ም ዳሰሳ ያደረጉት አለምሰገድ አባይ፣ Identity or Jilted: re-imagining Identity ተብሎ በታተመው መጽሐፍ ውስጥ ‹‹ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊ ትግሬዎች አማራ ታሪካዊ ጠላታቸው እንደሆነ ጀምረው፣ በተለይ ሸዋን አምርረው እንደሚጠሉት ገልጸዋል›› (ገጽ 153-54) ይለናል፡፡ አስደናቂው የጥላቻ መገለጫ የሚሆነው ግን በዚሁ በአለማየሁ አባይ መጽሐፍ፣ ብዙኃኑ ትግሬ አማራን ሲጠላ 10 በመቶዎቹ ብቻ ናቸው ለቱርክ እና ለጣሊያን ጥላቻ እዳላቸው የተናገሩት፡፡

አለምሰገድ አባይ በጥልቅ ቃለመጠይቃቸው እና በተተኳሪ ቡድን ውይይት ውስጥ ከጥናቱ ተሳታፊ መካከል የአንድ ትግሬ አዛውንት የጥላቻውን ምክንያትን እንዲህ አቅርቦታል፡-

ሸዋ! ሸዋ! ሸዋ! ሸዋ ነው ጠላታችን፤

እነሱ ጨካኝ፣ ሰይጣን ናቸው!

በፈጣሪ የማያምኑ…ጨካኝ! ጨካኝ ናቸው፡፡ በ1970ዎቹ በደቡብ ኢትዮጵያ ጎሬ በነበርኩበት ወቅትየሸዋ አማራ ሰው ይመጣ ነበር፣ ትግሬ መሆኔን ሲያውቅ ግን

ባንዳ፣ ውሸታምና ከሃዲ አድርጎ እየቆጠረኝ አይቀርበኝም፡፡ ወደኋላ ሦስት ደረጃ ተጉዘው፣ ታሪክ አስታውሰው አይቀርቡኝም፡፡ኩራታቸው! የፈጣሪ ያለህ፣ እንዲህ ያለ ኩራት አይቼ አላውቅም፡፡

(ገጽ 154)

በዚሁ የጥናት ክፍል ሌላ አንድ የትግሬ ሽማግሌ መጠይቅ ሲመልስ፣ ‹‹ዳግማዊ ምኒልክን እና ቀዳማዊ ኃይለስላሴን አምርረው እንደሚጠሉ ገልጸዋል›› (ገጽ 154) በማለት ለሸዋ አማራ ያላቸውን የጎመዘዘ ጥላቻ መዝግቦታል፡፡

ከሥነ-ጽሑፍ፣ ሥነ-ዕውቀት፣ ፍልስፍና እና ሥነ-መለኮት ዕውቀት ባልተናነሰ መልኩ የፍትሕ ሥርዓት ምሰሶ የሆነውን አጼ ዘርዓያዕቆብን ታሪክ በማደብዘዝ፣ የዚህ ዘመን የሸዋን ኅብረተሰብ በድህነትና በማፍዘዝ ስለታሪኩና መነሻው እንዳይጠይቅ፣ ቢጠይቅም የፖለቲካ ግርፋት እንዲፈጀው አድርጎ ሠርቶታል፡፡

ሌላውና ዋነኛው የማጥቂያ ስልቱ ኢ-ፍትሐዊነትን እና በደሉን አውቀው ይገዳደሩኛል በማለት በ ‹ሽፍታ› ሰበብ የክፉ ቀን ደራሽ፣ የወገን ደምመላሽ የሆኑ የሸዋ አናብስቶችን ከ1984-2000 ዓ.ም ድረስ በየዱሩ እያሳደደ ገድሏል፤ አስገድሏል፡፡ ለዚህ የኮላሽ ሸንተረሮች፣ የመንዝ ቆላዎች፣ የጅሩ ተዳፋት፣ የይፋት ዱሮች፣ የአሳግርትና በረኸት የወንዶች መዋያ፣ የከሰም በረኃ የክፉ ቀን ምሽግ፣ የአዳባይ ወንዝ የሸዋ ግስላዎች መመኪያ ሕያው ምስክሮች ዛሬም ይናገራሉ፡፡ ልክ የራስ ብሩ ልጆችን ደርግ አፍቀራ አምባ እንዳደረጋቸው፣ ትህነግም የቁርጥቀን ልጆቿን ፈጅቶ አንገት ለማስደፋት ያልሄደበት ጥሻ የለም፡፡ መግደል ያልቻለውን እየሰበሰበ በደብረብርሃን እና ሸዋሮቢት እሥር ቤቶች ከ4000 በላይ ወጣቶችን ግዞት በማውረድ ክፋቱን አሳያቸው፡፡

#ሸዋን በአራት መዋቅር መገነጣጠልና የልዩነት አጥር መገንባት የትግራይ ደመኛነት ማሳያው ሌላው ጥግ በ1983 ዓ.ም ሥልጣን ተቆጣጥሮ ሳይውል ሳያድር ታላቁን ሸዋ ወደ ስብርባሪነት መበተን ነው፡፡ በተለይ ታሪክና ባሕሉን፣ ቋንቋውን፣ ሥነ-ሥሪቱን፣ ኤኮኖሚውን እና ለዘመናዊት ኢትዮጵያ ምሳሌ የሚሆን ሕብረ-ቀለሙን ፍቆ-ፈቅፍቆ አጠፋው፡፡ ‹ጠላቴ› ያለውን እና በተለየ ማጥቃት የፈለገውን የደጋማው ሸዋ አማራን በብጫቂ ተራራ ላይ እንዲንጠላጠል በሌለበት ወስኖ፣ ባለተገኘበት ጉባዔ አጽድቆ ቆረረው፡፡

ይህን ደመኛነት ቀድመው የተረዱ የሸዋ አርበኞችም ለትግል ቀድመው ተነሱ፣ መከራንም ቀመሱ፡፡ ወርሐ ጥር 1984 ዓ.ም የተመሠረተው መዐሕድ በመላው የሸዋ ወረዳዎች እና ከተሞች የትግል ምዕራፉን አስጀምሮ በነበረበት ወቅት ትሕነግ ልዩ ትኩረት አደረገበት፡፡ ታሕሳስ 11 ቀን 1985 ዓ.ም በደብረብርሃን አጼ ዘርዓያዕቆብ አደባባይ ላይ መዐሕድ የሸዋን ክንፍ ለመመሥረትና ጸረ-ሕወሐት ትግሉን ለማስፋት፣ እንዲሁም ብርታት ለመሆን በሥፍራው የተገኙት ፕሮፌሠር አሥራት ወልደየስ የተናገሩትን ዘመን-አይሽሬ ትንቢት ‹‹የተጋረደው ጀግንነት›› ብሎ አርበኛ ማሙሸት አማረ በ2012 ዓ.ም ባሳተመው መጽሐፍ ለታሪክ እንዲሆን መዝግቦ አስቀምጦታል፡፡ በርግጥ አርበኛ ማሙሸት በዚያው ዘመን፣ በወጣትነት፣ በመማሪያ ዕድሜው በሸዋ ላይ የሚደርሰው የትህነግ በደል አንገሽግሾት ነው ትግሉን የተቀላቀለው፡፡

በንግግራቸው፣ ፕሮፌሠሩ፣ ‹‹በሐረር፣ በአሩሲ፣ በባሌ፣ በወለጋ፣ በጋምቤላ፣ በሶማሌ፣ በአፋር፣ በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ፣ በደቡብ እና በራሱ ርስት በአማራ (በራያ እና በሁመራ) እያለቀ ላለው አማራ እየተደራጃችሁ ለምን ይፈናቀላል፣ ለምንስ ይገደላል ብላችሁ ካልተከላከላችሁለት፣ እነሱን ሲጨርሱ ነገ እናንተ ባለተራ መሆናችሁን አትዘንጉ፤ ዛሬ በሩቅ እያለ ተደራጅታችሁ መከላከል ካልቻላችሁ፣ ከፊታችሁ ሲደርስ መያዣ-መጨበጫው ይጠፋኋል›› (የተጋረደው ጀግንነት፣ ማሙሸት አማረ፣ 2012 ዓ.ም)፡፡

በፕሮፌሠር አሥራት የሸዋ ጠቅላይ ግዛት የመዐሕድ አደራጅነት፣ መሪና አስተባባሪነት እንደነ አርበኛ አንዷለም መላኩ፣ አርበኛ ማሙሸት አማረ፣ ፊታውራሪ አስማረ ዳኜ በፈታኝ የመከራ ዘመን መካከል የሚጠበቅባቸውን ሁሉ አድርገዋል፣ ወድቀዋል፣ የመከራን ጽዋ ተጎንጭተዋል፡፡

በተለይ በጅሩ ሠላድንጋይ፣ ጉዶበረት፣ አሳግርት፣ በረኸት፣ ምንጃር፣ አንኮበር፣ ደብረብርሃን፣ ጫጫ፣ መንዝ ቀያ፣ መንዝ ላሎ፣ ባሶና ወራና፣ አገረማርያም እና ሌሎች ፈታኝ ቦታዎች ላይ እንደ አብሪ እየተወረወሩ፣ እንደ መብረቅ እያጓሩ ድንገተኛ ጥቃት በመሰንዘር እና አርሶ አደሩን በማታገል ትህነግን እረፍት ነስተው ነበር፡

ሆኖም ሸዋን በመበታተን፣ በቋንቋና በባህል የማይቃረነውን በማጋጨት፣ ቁርሾና በደል በማኖር በመካከል የጥላቻ ግንብ ገነባ፡፡ ለዚህ እንደማሳያው ወያኔ የእጅ ሥራ ውጤቱ ከ2007-2013 ዓ.ም የተደረገ ሠባት ተከታታይ ትንኮሳ እና አምስት የተሳካ ሸዋን የማጥፋት ጥቃት በይፋት አጣዬና አካባው ሲካሄድ የነበረው ነው፡

ኤኮኖሚውን በመምታት አንገት ማስደፋት አንድ ወቅት 2000 ዓ.ም አካባቢ አንድ የአገር ውስጥ መጽሔት ‹‹አጼ ዘርዓያቆብ ተመልሰው ቢመጡ ቤታቸው አይጠፋባቸውም›› ማለቱ እጅግ አነጋጋሪ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይህ ጽሑፍ ዋነኛ ዓላማው ትህነግ ሥልጣን ከያዘበት ወቅት ጀምሮ ጽሑፉ እስከተዘጋጀበት ድረስ፣ ደብረብርሃን ከተማ ከአቻዎቿ ጋር ስትነጻጸር 17 ዓመታት ሙሉ ትህነግ አንድ ስንጥር እንኳ ሳያስቀምጥባት ንጉሠ-ነገሥቱ እንዳስቀመጧት መሆኗን ለማሳየት ነው፡፡ ከጥንታዊያን ከተሞች ከአዲስ አበባ ቅርቧ ደብረብርሃን ሆና ሳለ፣ በትህነግ የጥላቻ ዱላ ሆን ተብላ እንድትቀጠቀጥና የልማት ዳርቻ እንድትሆን ሆነ፡፡

ሸዋ እነ አቡዬሜዳ፣ መገዘዝና ጓሳን የመሰሉ የዓባይ እና አዋሽ ተፋሰስ የውኃ ጋን የሆኑ መጋቢዎች፣ ከሙገር እስከ ሞረት የተነጠፈ የዠማ ሸለቆ የማዕድን ኃብት፣ በርካታ የበግ ሥጋ ምርት ማዕከል፣ የቴፍ፣ ስንዴና ምስር አምራች ነው፡፡ በተፈጥሮ ኃብትና በቱሪዝምም ከፍተኛ ሃብት የሚፈጥሩ መዳረሻዎች አሉት፡፡ ነገር ግን ወያኔ በተለመው የማቆርቆዝ ስልት ኃብቱን እንዳይጠቀም፣ እንዳይጠይቅና ቀና እንዳይል ሲፈርጀው፣ ሲያሸማቅቀውና የመልማት ዕድሉን ሲዘጋበት ሦስት አሥርት ዓመታትን ዘልቋል፡፡

የዘመናዊት ኢትዮጵያ መገለጫ ሥፍራ አንኮበር ከስም በስተቀር ሁሉም ነገሯ እንዲጠፋ ተደርጓል፡፡ ከዘይላና ታጆራ በአዋሽ አድርጎ ወደምዕራብ አፍሪካ የሚደረግን ታላቅ የረጅም ጉዞ የንግድ መሥመር የምታገናኘው፣ የጥንታዊት እና ዘመናዊቷ ኢትዮጵያ መገናኛ በር ዓልዩ-አምባ ዛሬ የተረሳች ትንሽ መንደር ሆናለች፡፡ አንኮበር መሠረተ-ልማት አጥሯት፣ የታሪክ ማስታወሻዎቿ ተሰውረው፣ መልኳ ሳስቶ ከታላቁ ቤተ-መንግስት በቀር አይን የሚያርፍባት ነገር የሌላት ጎስቋላ እንድትሆን ተደርጓል፡፡ ከምንጃር ቆላማ ሜዳ እስከ መርሐቤቴ ድረስ መሐል አገር የሚመግብ ለም መሬት፣ አገላብጦ አራሽ እና ትርፍ ምርት ቢኖረውም የተበተነ አርሶ አደር (በራሱ ማኅበር የሌለውና ዋጋ የማይተምን) በመሆኑ ከድህነት ፈቀቀ አላለም፡፡ ከአገሪቱ መዲና በ150 ኪሎ ሜትር ራዲየስ የሚገኝ ቢሆንም እጅግ ኋላቀር ግብርና እና የግብርና ቴክኖሎጂ ይጠቀማል፡፡ ቢያመርት እንኳን፣ ወደገበያ የሚወስድበት መንገድ እንኳን የሌለው አርሶ አደር ማኅበረሰብ ቢኖር ሸዋ ነው፡፡

እንደ ምሳሌ መሐልሜዳ-ዓለምከተማ፣ አንኮበር-አዋሽ አርባ፣ ደብረብርሃን-አንኮበር፣ አጣዬ-መሐልሜዳ፣ ጣርማበር–መለያ-ሞላሌ-ሠፌድሜዳ፣ ዓለምከተማ-ደጎሎ እና ለሚ-ዓለም ከተማ ፕሮጀክቶች ላይ የተሰራው ደባ አብዛኛውን የሸዋን የመልማት ፍላጎት ገደል የከተተ ነው፡፡

በጥቅል ለፕሮጀክቶቹ 8.2 ቢሊዮን ብር ተመድቦ ከ2007-2013 ዓ.ም ይጠናቀቃሉ ቢባልም፣ በ2013 ዓ.ም ጥቅምት ወር በተደረገ ጥናት ፕሮጀክቶቹ በደረሰባቸው የጥቅም ትሥሥር፣ ምዝበራና የሌብነት ቅሌት ከተመደበላቸው በጀት በላይ 60% ድረስ ተጨማሪ በጀት የሚያስፈልጋቸው እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡ በአማካይ እያንዳንዳቸው ከ280 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት የማይደረግላቸው ከሆነ ለማጠናቀቅ እንደሚቸገሩ ጥናቱ አቅርቧል (Fentahun Cherie Workneh , Habtamu Washe Mite Investigation on the Causes of Cost Overrun in Federal Road Projects in North Shewa Zone, 2020)፡፡ በዚህ የተነሳ ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ መንገዶቹ እጅግ ውስብስብ ችግር ውስጥ ገብተዋል፡፡ ለዚህ ችግር መነሻው ደግሞ በዘረፋ ትሥሥር የወደቁ የመንገድ ሥራ ተቋራጮች እና የትህነግ ደመኛ ጠላትነት የሸዋን መሠረተ-ልማት በማኮሰስ ኤኮኖሚውን የማሽመድመድ ዕቅድ አካል ነው፡፡

በሌላ አስደናቂ እና የትህነግ የጥላቻ መገለጫው የወራኢሉ፣ ጃማ፣ መንዝ ግሼ፣ መንዝ ጌራ፣ መንዝ ማማ፣ መንዝ ቀያ እና መንዝ ላሎን ጨምሮ የይፋት አጎራባች ወረዳዎችን በማገናኘት ከ700 ሺህ በላይ ኅብረተሰብ ኤኮኖሚ ሊያስተሳስር የሚችልን የመንገድ ዝርጋታ በጀት በመዝረፍ የመንገዱን ጉዳይ የሕልም እንጀራ በማድረግ ዛሬም ድረስ ሳይጠናቀቅ እየተንገታገተ ይገኛል፡፡ ይህ መሥመር እየተጠቀመ የሚገኘው የመንዙ ሊቅ፣ ዲፕሎማትና አርበኛ ፊታውራሪ ገ/ሕይወት ወ/ሐዋሪያት 1922 ዓ.ም ጀምሮ የልዕልት ተናኜወርቅ ኃ/ሥላሴ እና የክቡር ራስ ደስታ ዳምጠው ወራሾች ንብረት ኃላፊ እንደራሴ ሆነው በሚሠሩበት ወቅት ንጉሠ-ነገሥቱን ደጅ በመጥናት ከ118 ኪሎ ሜትር በላይ በአካፋና ዶማ በሰው ጉልበት ያስከፈቱትን መንገድ ነው፡፡

ፊታውራሪ ገ/ሕይወት ሁኔታውን ሲገልቱጹት እንዲሕ ይላሉ፡ ‹‹ይህን እረጅምና ገደላማ መንገድ ለመክፈት ብዙ መስዋዕትነት የተከፈለ ቢሆንም፤ በመንዝ ሕዝብ መልካም ፈቃድ፣ መተባበርና በተፈጥሮ ቀያሽነት የተገኘውን ውጤት የአውራ ጎዳና ተረክቦ እያቃና ሠርቶከ 1952 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ይገለገልበታል››፡፡ ትህነግ በሥልጣን ላይ በነበረበት ሦስት ዐሥርት ዓመታት ለሸዋ ሕዝብ የሠራለት መንገድ ያለመኖሩ አስከፊ ችግር ላይ እንዲገኝ አድርጎታል፡፡

ኤኮኖሚውን በማዳከም መጉዳት ብቻም እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባዋል፡፡

በአብዛኛዎቹ የመርሐቤቴ ቀበሌያት፣ በተለይ በፌጥራ፣ ኮራ ወንጭት-ፊት፣ ሚዳ አህያፈጅ፣ እንደ አገረሰላም፣ ክምር ድንጋይ እና ዶባ ባሉ ገደላማ የመንዝ ቀያ ቀበሌያት፣ በሞረትና ጅሩ የጠንበላን ሸለቆ፣ እንሳሮ ከበልበሊት ሸለቆ እስከ እነዋሪ ደጋ፣ ተጉለት ሸሾ ቆላ፣ በላሎ ምድር ኮረብታዎችና አፍቀራ አቅራቢያ፣ አሳግርት መገዘዝ፣ አንኮበር ጎርጎ፣ እና የአንጾኪያ ገምዛ ትርፍ አምራች አርሶ አደሮችና ግብር ከፋዮች ጥርጊያ መንገድ እንኳ ሳይኖራቸው በየሥርጣሥርጡ (ሥርጥ፡ በሸዋ አስፈሪና አደገኛ ገደላማ መንገዶች፣ በተለይ በትልልቀ ቋጥኝ አለት መካከል የሚገኙ ቀጫጭን መሹለኪያ መንገዶች) እየተጠቀመ ኖሯል፡፡

ወላድ እንኳ መውሰጃ አማራጭ የሌለው በመሆኑ ከ15-40 ሜትር ቀጥ ያለ የቋጥኝ ላይ መንገድ በቃሬዛ በሸክም ይወርዳል–ይወጣል፡፡ ይህ በሥነ-ልቦናው ላይ የተደረገ የአንገት ማስደፋት ዘመቻ አካል ነው፡፡ በተለይ የሸዋን ኅብረተሰብ የኤኮኖሚና ማኅበራዊ ውቅር አፍርሶ በሌላ በመተካት (Psychological Manipulation through Social Reengineering) ደረጃ የተሳካ የጥፋት ፕሮጀክት አከናውኗል፡፡

ሰሜን ሸዋን ከአዲስ አበባ የነጠለበትና ከዋናው ሐብት ያራቀበት፣ የሸዋ ባለሀብቶችን ‹ጥገኛ ባለሀብት› እያሉ አንገት በማስደፋት በጋራ ተባብሮ እንዳይሠራና በተናጥል የማሳደድ አስከፊ ዘመን እንዲገፋ አድረገውታል፡፡ በዚህም በሸዋና አካባቢው እንዳያለማ፣ ከደብረብርሃን በመለስ ይህ ተብሎ የሚጠቀስ የከተማ ማዕከል እንዳይቆቆር፣ ያሉትም አንዱ ከሌላ እንዳይገናኝ ተደርጎ መሠረተ-ልማት አልባ ያደረጉበት ደባ ከመዝገብ የማይፋቅ፣ ከፍርድ የማያስቀር ነው፡፡

አሸባሪው ትህነግ በዚህ እና ያልተነገሩ በእያንዳንዱ ጎጆ በቀበረው ቋያ ሸዋ የድህነት ድር ወረሰው፡፡ መከራው፣ ጥላቻውና በደሉ ሲበረታበት በመላው ኢትዮጵያ እና በባህር ማዶ ተሠደደ፡፡ ትህነግ ግን በደረሰበት ቦታ ሁሉ ‹መጤ›፣ ‹የምኒልክ ሠፋሪ› እያለ ማኅበራዊ እረፍት ነሳው፣ ለእርድ አቀረበው፣ ኃብቱን አወደመበት፡፡ በውጪ አገራት የሚኖረውንም ‹አድኃሪያን› እያለ በስደት ላይ ሌላ ካንሠር ሆነበት፡፡

ከቅርብ ጊዜያት አንስቶ እንኳ በአማራ ክልል የሚገኘውን የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር ለጸረ-አማራ እና ጸረ-ኢትዮጵያውያን መሸሸጊያ፣ ሽብር ማሠልጠኛና የጥቃት መንደርደሪያ በማድረግ ትህነግ ረጅም የቤት ሥራውን ሠርቷል፡፡ ወያኔ ሂሳብ ሠርቶ በቀበረው ፈንጅ እና በተላላኪው ኦነግ በኩል ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በሸዋ የይፋት ቀጣናን በማወክ ትንኮሳዎችን እና ጥቃት ፈጽሟል፤ አስተባብሯል፡፡ በተለየ መንገድ ግን ከመንበሩ ከተገፋ በኋላ ለዐራት ኪሎው ዙፋን ይቀርበኛል ብሎ የመረጠውን ይህን አካባቢ በማተራመስ በ2008 የተጀማመረው የሽብር ሥራ፣ በ2009፣ 2010፣ 2011፣ 2012 እና 2013 ዓ.ም እጅግ አውዳሚ ጭፍጨፋ አስፈጽሟል፡፡ በተለይ በ2013 ዓ.ም በአንድ ሳምንት ልዩነት በመጋቢት ወር በተፈተጸመ ወረራና የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ 246 ንጹሐን ሲገደሉ 295 ሰዎ በተኩስና ቃጠሎ ቆስለዋል፡፡ በዚሁ ጥቃት ከ1,500 በላይ መኖሪያ ቤቶች ጋይተው 255,000 ሕጻናት፣ ሴቶችና አረጋውያን ከመኖሪያቸው ተፈናቀሉ፡፡

አጣዬ ከተማ፣ የማጀቴ መስኖ እርሻዎች፣ የቆሪሜዳ መንደር፣ አላላ፣ ይምሉዎ፣ ብርቂቶ፣ ነጌሶ፣ በርሃሥላሴ እና ጀውኃ የአርሶ አደር መንደሮች እህልና መኖሪያ ወደአመድነት ተቀየረ፡፡ በጥቃቱም ከ2 ቢሊዮን በላይ ንብረት ወደመ፡፡ ትሕነግ ዳግም ዙፋን ለመያዝ ይቀርበኛል ብሎ ባሰበው የአጣዬ ቀጣና በተሳተፈበት፣ ባስተባረውና ባሰማራው የተላላኪ ኃይሉ ብዙ አወደመ፡፡ ይሕ ተግባሩ ንጥል ዐውድ ሳይሆን ብዙ መቶ ዓመታት የተነደፈው የጸረ-አማራ እና ጸረ-ሸዋ ፕሮጀክት አካል እንደሆነ ከታሪክ አይሰወርም፡፡ እንግዲህ ትሕነግ መጥፋት ያለበት፣ አስተሳሰቡ መነቀል ያለበት ዛሬን ስለበደለ ብቻ አይደለም የሚባለው በታሪክ ፊት የማያሰልስ የጥፋትና የክፋት ምንጭ ስለሆነ ነው፡፡ ትህነግ ኢትዮጵያን የማጥፋት የ500 ዓመት ፕሮጀክት የዚህ ዘመን ዋናው መሥሪያ ቤት ስለሆነ ነው፡፡ ይህን ለረጅም ዘመን የተጣባውን የትግሬ ልኂቃን ጸረ-አማራ፣ ዝቅ ብሎ በተለየ ያነጣጠረበት ጸረ-ሸዋ እሳቤ ማፍረስ የኅብረተሰብ እረፍት ነው፡፡ ከመሠረቱ ነቅሎ ከበከለው የዘረኝነት ምሕዳር ማስወገድ በቡኖ-በዴኖ፣ በአርባጉጉ፣ በመተሃራ፣ በቲቢላ፣ በሳላይሽ፣ በጉማይዴና በባሌ ጭፍጨፋ የተፈጸመባቸውን ንጹሃን አካላት ፍትህ አካል ነው፡፡

°°°

ፈረሱንም ጋልበዉ ላቡ እስኪንቆረቆር፤

በልጅጉን ተኩሰዉ ቃታዉ እስኪሰበር፤

ጦሩንም ወርውረዉ ሰማዩ ይሰንጠር፤

አዳራሽ ሲገቡ አንገት ከማቀርቀር፡፡

°°°

እንዲል የሸዋው ነጋሲ ክርስቶስ፣ በማንነቱ፣ በስነ-ልቦናው እና በኅልውናው ምሎ የመጣበትን ጨፍጫፊ የጨበጠው ቃታ እስኪግል ደመኛ ጠላቱ ትህነግ እና የአስተሳሰቡ ተሸካሚ ፈርሶ እስኪቀበር የመታገል ታካዊ ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ ደመኛ ጠላትን እንደጓያ ሠባብሮ እንዳይነሳ ማሽመድመድ ይገባል እንጂ በየ100 ዓመቱ እየተነሳ አገር እንዲቀጣ፣ ሥልጣኔውን እንዲያፈርስ እና እንዲያንበረክከው መፍቀድ ፈጽሞ ውጉዝ ነው፡፡