የአንኮበሩ የዳግማዊ ምኒልክ ቤተመንግስት

Emperor Menelik’s Palace at Ankober

 

የምንሊክ ሀገር አንኮበርና ታሪካዊ ቅርሶቿ

  • አንኮበር ከአዲስ አበባ በ172 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ከደብረ ብርሃን በ42 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች። በወረዳዋ ከ92 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሚኖሩ ሲገመት ከባህር ጠለል በላይ በ3700 ሜትር ላይ ትገኛለች።
  • አንኮበር በተለያዩ ወቅቶች በማዕከላዊ ከተማነት እንዳገለገለች የታሪክ ድርሳናት ይገልጻሉ።
  • ከ1262 ዓ.ም ከአጼ ይኩኖአምላክ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ አንኮበር መናገሻ ሆና መቆየቷን የታሪክ መጻህፍትን እና ከአባቶች የሰሙትን ጠቅሰው ሊቀ ካህናት ቃለህይወት ሃብተወልድ ይገልጻሉ።
  • በዚህም ከ1262 እስከ 1521 ዓ.ም ድረስ በማዕከላዊ ከተማነት አገልግላለች።
  • በመሃል ማዕከላዊነቱ ወደ ጎንደር አቅንቶ ለ200 ዓመታት ያህል አንኮበር መናገሻ መሆኗ አክትሞ ነበር።
  • መርድ አዝማች አምሃ ኢየሱስ መቀመጫቸውን ከዶቃቂት ወደ አንኮበር አዛውረው በድጋሚ አካባቢውን መናገሻ አደረጉት ይላሉ ሊቀ ካህናት ቃለህይወት።
  • ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታት የተለያዩ ነገስታት ቤተ መንግሥታቸውን በአንኮበር ገንብተዋል። የገነቡት ቤተ መንግሥት ጦርነትን ጨምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ሲፈርስ ነገስታቱም በተደጋጋሚ አሳንፀውታል፤ አድሰውታል።
  • መርድ አዝማች አምሃ ኢየሱስ ወደ አንኮበር አቅንተው መቀመጫቸውን በዚያው ካደረጉ በኋላ አምስት የተለያዩ ነገስታት መቀመጫቸው በዚያ አድርገዋል።
  • መርድ አዝማች አስፋው ወሰን፣ ወሰን ሰገድ፣ ሳህለ ስላሴ፣ ሃይለ መለኮት እና ምኒሊክ የሸዋ ንጉስ በመሆን አንኮበር ዙፋናቸውን በማድረግ መርተዋል።
  • በመሃል ለአጭር ጊዜ መቀመጫቸውን ወደ ቁንዲ ከቀየሩት ወሰን ሰገድ ውጭ፣ አንኮበር ሲሶ መንግስት እና የሸዋ ማዕከል በመሆን ከ1733 እስከ 1881 ዓ.ም አገልግላለች።
  • በዚህ ወቅትም የተለያዩ ታሪካዊ ሥራዎች በአካባቢው ተከናውነዋል።

ታሪከ ብዙዋ አንኮበር

  • ከአንኮበር 12 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው አልዩ አምባ የጉምሩክ ሥራ የተጀመረበት ሲሆን እስከ ዘይላ ወደብ ድረስ ይነገድበት እንደነበር የአንኮበር ወረዳ ባህል እና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፈለቀ ምህረት ይገልጻሉ።
  • ቢቢሲ በስፍራው በተገኘበት ወቅት “በጊዜው ይነግዱበት የነበረበት ደረሰኞች አሁንም ድረስ በማስረጃነት አሉ” ብለዋል።
  • በአንኮበር ካሲት ሰቀላ ለሶስት ዓመታት የሚሰጠውን ትምህርት የሚከታተሉ ሰዎችም በተለያዩ የአስተዳደር ቦታዎች ይመደቡ እንደነበር ይነገራል።
  • በአንድ ወቅትም ሶስት ሃገራት ኤምባሲያቸውን በአንኮበር ከፍተው እንደነበር አቶ ፈለቀ ይገልጻሉ። “የእንግሊዝ፣ የፈረንሳይ እና የጣሊያን ኤምባሲዎች በአካባቢው ነበሩ። እነዚህ አካባቢው ትልቅ ቦታ እንደነበር ያሳያሉ” ይላሉ።
  • በአካባቢው የተለያዩ ታሪካዊ ቁሳቁሶችም በስፋት የሚገኙበት ነው።
  • “በጣም ብዙ ቅርስ በአካባቢው አለ። በወረዳው ብቻ ወደ 97 የሚደርሱ አብያተ ክርስትያናት አሉ። የብራና መጽሐፍት፣ ኒሻኖች፣ የብር ከበሮ፣ የብርና የወርቅ ፀናጽል እነዚህ ሁሉ አሉ” ይላሉ።
  • በአያያዝ ጉድለት ግን የተወሰኑት ታሪካዊ ቅርሶች ተሰርቀዋል።
  • “ከአስር ዓመት በፊት የብራና መጽሐፍት፣ መስቀል፣ ስንክሳር፣ ተአምረ ማርያም እና ዳዊት ጠፍቶ ነበር” ይላሉ አቶ ፈለቀ።
  • ህብረተሰቡን በማስተማር እና ለቅርስ ጥበቃ የሚደረገውን ጥበቃ በማሻሻል ካለፉት አስር ዓመታት ወዲህ የቅርስ መጥፋት አጋጥሞ እንደማያውቅ የሚናገሩት ኃላፊው ይህንን በዘላቂነት ለማስጠበቅ 5 ሚሊዮን ብር ገደማ ተመድቦ የሙዚየም ግንባታ ተጠናቋል።
  • “የሙዚየሙ ግንባታ ተጠናቋል። የሙዚየሙ መተዳደሪያ መመሪያ እስኪጸድቅ እየጠበቅን ነው” የሚሉት የሰሜን ሸዋ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ትዕግስት መኳንንቴ ናቸው።

የጣሊያኖች ጦርና ውድመት በአንኮበር

  • አጼ ምንሊክ መቀመጫቸውን ከአንኮበር ወደ እንጦጦ ካዘዋወሩ በኋላ የነበረው ቤተመንግሥትም በጣሊያን ወረራ ወቅት እንደወደመ ይነገራል።
  • በቦታው ላይ አሁን የቀድሞውን የሚመስል ቤተ መንግሥት ተገንብቷል።
  • አንኮበር ቤተ መንግሥት አካባቢውን ለመቆጣጠር እንዲያመች እና ነገስታቱን ከጠላት ለመጠበቅ እንዲያስችል በተራራ ጫፍ ላይ ነው የተገነባው።
  • በግቢው ውስጥ ንጉስ ሳህለ ስላሴ እንደ ቢሮ ይጠቀሙበት የነበረበት እልፍኝ ፍርስራሽ ይገኛል። እልፍኙን አጼ ምንሊክም ለትንሽ ጊዜ ተጠቅመውበታል።
  • ሌላው በግቢው ውስጥ የሚገኝ ቅርስ በእንቁላል እና በኖራ የተሠራው የቤተ መንግሥቱ አጥር ነው። አጥሩንም ንጉስ ሳህለ ስላሴ እንዳስገነቡት የታሪክ ድርሳናት ይገልጻሉ።
  • “የቱሪስት ፍሰቱ የተቀዛቀዘ ነበር። ማዕከላዊነቱ ወደ አዲስ አበባ ከመዞሩም በላይ መንገዱ አመቺ አለመሆኑ ለዚህ ምክንያት ነው” ይላሉ አቶ ፈለቀ ምህረት።
  • ቤተ መንግሥቱ ቀደም ሲል የነበረውን ቅርጽ ይዞ የአካባቢው ተወላጅ በሆኑት ኢንጂነር ተረፈ አፈወርቅ በድጋሚ ተገንብቷል።
  • “ቤተመንግሥቱን ካቋቋሙት በኋላ በርካታ ጎብኚዎች ሊጎበኙ ይመጣሉ። ከአዋሽ ደብረ ብርሃን መንገድ እየተሠራ ነው። ብዙ ኢንቨስተሮችም በአካባቢው መዋለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ እየጠየቁ ነው” ይላሉ።
  • ቤተ መንግሥቱ የበፊት ቅርጹን ይዞ በአዲስ መልክ ከተገነባ በኋላ ለእንግዶች ክፍት ቢሆንም ያስገነቡት ግለሰብ ሆቴል አድርገው እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።

Background about Ankober 

The Videos above present how we drove to the Ancient & Historic City of Ankober (Ethiopia) and visited Menelik’s Palae & the Saturday Market at Gorabela. The video was recorded on 17 September 2022 when I visited this historic Site. Ankober (አንኮበር) was established by Saint & King Yikunu Amlak in the 12th Century. Sait and King Yukonu Amlak was the heir or successor of the Axumite Amhara after the destruction of Axum by Yodit Gudit and the expanssion of Ottomans in the read sea areas. The Video was recorded during my historic vist to Ankober and its surrounding areas in September 2022.

This Ancient and Historic City is found in the Amhara Administrative Region, 170 KMs away from Addis Ababa, Ethiopia and Menelik’s Palce is located at 2890 metres above sea level. The place is the origin of the Amhara Solomonic Dynasty and birth place of many Kings such as: Abiye, Amha Iyesus, Wosen Seged, Asfa Wosen, Sahile Selassie, & Haile Melekot. Emperor Menelik is the son of King Haile Melekot. In the 17, 18 & 19th Centuries Ankober was well known by Europeans, Assians, and the Middle East travlers & Deplomats.

The surrounding area is decorated by beautiful Mountains and plain agrticultural lands covered by variety of field crops. Emperor Menelik and Ankober are well known not only in Ethiopia but also globally because of Emperor Menelik’s good Governance and his victory against the Itallian colonialist invader in1896. In this Video you will See:

* The Breathtaking Mountains and plain agricultural lands covered by different field crops and Eucalyptus Trees * The Wushawushi Town

* The awful and unmaintained gravel Road

* People travelling to the Saturday Market in Gorabela

* Donkeys loaded with Teff, Wheat, Barley, Pulses, Fruits and Vegatables

* Livestocks * The forest that covers the long and extended Qundi Mountain. * The Saturday Market at Gorabela Town

* The Palace of Emperor Menelik at Ankober Historic Site

* The underconstruction of the Museum of King Menelik at Arada

* The Vantage of Emperor menelik tha shows all around Ankober as far as Awash

* A fig Tree whch was being harvested during the reign of several Kings, Juniperes Abysinica, Gesho, Kosso, Guassa, Tej Sar, Eucalyptus Tree and many other indegenious plant and grass species.

* The new Meuseum which has been designed and constructed by imitating the Palace of Ankober at Arada (Biq Inq).

* You will also see the surrounding area as far as Alyu Amba, Haramba, Awash and close to Afar Lowlands from King Menelik Palace’s Vantage.

I Thank my brother Gezahegn Birhane for travelling and supporting me during my visit to this historic site. I am also grateful for Fikirte who has given me brefiengs about Emperor Menelik & his glories inside the marvelous Palace. I woul like to extend my gratitude to the ancient people of Ankober for their Kindness and warm reception. This very educative and entertaining video. Dont miss out! Watch Enjoy and learn. Thank you for watching Kefale Alemu.