ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የተሠጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የተሠጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
 
ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የተሠጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የተሠጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
ኦነግ ሸኔ በሚል በዳቦ ስም የሚጠራውና ከኦሮሞ ሕዝብ ባህልና እምነት ፈፅሞ የተቃረነ ሰው በላ ቡድን እና ተባባሪዎቹ የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 3፡20 ድረስ በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ዞን በአቢ ዳንጎሮ ወረዳ ደቢስ በአለ እግዚአብሔር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እና ሌሎች ሦስት ቀበሌዎች ውስጥ በሚኖሩ ንፁሀን የአማራ ሕዝብ ላይ በተፈፀመ የጅምላ ግድያ እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ በተሰበሰበ መረጃ ከ70 በላይ ንፁሀን ዜጎች ሲገደሉ በርካቶች እገታና ከፍተኛ የሆነ የንብረት ዝርፊያ ተፈፅሞባቸዋል፡፡
 
ዜጎች ተወልደው ባደጉበት በገዛ ሀገራቸው መጤ እየተባሉ እየተሳደዱና እየተገደሉ ባሉበት ሁኔታ ስለምርጫ ማውራት በራሱ ቀልድ መሆኑን እያረጋገጥን፣ ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው መንግስት ዜጎችን ከአሸባሪዎች ጥቃት ከመከላከል ይልቅ የመናፈሻ፣ የመዝናኛዎችና የሪዞርቶች ግንባታ ላይ መጠመዱ አሳፋሪም አሳዛኝ ድርጊት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ሕዝባችን በኮሮና በሽታና በኑሮ ውድነት እየተሰቃዬ ባለበት ወቅት፣ ይባስ ብሎ በየአካባቢው እየተስተዋሉ ያሉትን ማንነትን መሠረት ያደረገ ዘር ማጥፋትና መፈናቀልን የሚያስቆም የመንግስት አካል መጥፋቱ ደግሞ እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው፡፡
 
እንዲህ በንፁሐን ዜጎች ላይ የሚፈፀም አይን ያወጣ የፖለቲካ ቁማርተኝነት በሰው ልጆች ታሪክ ታይቶም ሆነ ተሰምቶ አይታወቅም። በመሆኑም ሀገሪቱ ሕዝብ ያላት ሀገር መንግስት አልባ እየሆነች እንዳለች ማሳያ ነው፡፡
 
አሳዛኙ ጉዳይ ሥልጣንን አጥብቀው እየፈለጉ የስልጣናቸው ምንጭ የሆነውን የህዝቡን ደህንነት የማስጠበቅ ስራ ወደ ጎን መተው እርስ በርሱ የሚጋጭ አመለካከት እንደሆነ መኢአድ በፅኑ ያምናል። ባለፉት ሦስት ዓመታት በየቀኑ፣ በየቦታው፣ በተለይም ወያኔ በከለለው አጥር ውስጥ ኦሮሚያ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ያለማቋረጥ በበርካታ የሃገራችን ክፍሎች እየታየ ያለው በጅምላ ዘር ማጥፋት ወንጀሎችን ስናይ መንግስት ሕዝብን ለመጠበቅ ያጣው አቅም ሳይሆን ፍላጎት ማጣት እንደሆነ ያሳያል፡፡
 
ዛሬም ድረስ ወለጋ የአማራዎች መታረጃ ቀጣና ሆኖ ሲቀጥል የክልሉ መንግስት በግዴለሽነት ማየቱ ይህንን የጥፋት ቡድን እንደማይደግፈው ማረጋገጫ የለም፡፡
በመሆኑም በአጋጣሚ ሥልጣን ላይ የወጣው የፖለቲካ ቡድን የሚመራውን ሀገርና የሚያስተዳድረውን ሕዝብ ከአደጋ የመጠበቅና ደህንነቱን የማረጋገጥ ሕገ-መንግሥታዊ ግዴታና በወንጀልም እንደሚያስጠይቀው መግለፅ እንወዳለን፡፡
AEUP
 
ድርጅታችን መኢአድ በጥቃቱ ሰለባ ለሆኑት ወገኖቻችን የተሰማውን መሪር ሐዘን እየገለፅን፤ በአስቸኳይ መፍትሔ ያገኙ ዘንድ የሚከተሉትን ጥሪዎች ያቀርባል፡-
 
1ኛ.መንግስት አማራን የማጥፋት አጀንዳ በወለጋ፣ በደራ እና በደቡብ በጎራ ፈርዳ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን እንዲሁም በመላው የሀገሪቱ ክፍሎች በሚያሰኝ ደረጃ በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ተግባር ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ ወስዶ ህዝቡን ከእልቂት እንዲታደግ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡
 
2ኛ.በአራቱም የወለጋ ዞኖች የሚገኙ ወገኖቻችን ላይ በኦነግ ሸኔ አሸባሪ ቡድን አማካኝነት በደረሰው ግድያና መፈናቀል መንግሥት በአስቸኳይ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ እያሳሰብን፤ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እርዳታና ድጋፍ ለማድረግ እንዲረባረቡ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
 
3ኛ.የፌደራል መንግስትም ኦሮሚያን ጨምሮ በኦሮሚያና በሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን ሰፊ የዘር ማጥፋት ወንጀል ማስቆም ካለመቻሉም በላይ ወንጀሉን በስሙ ባለመጥራት በዜጎቻችን ላይ ለሚፈፀመው ጅምላ ፍጅት ተባባሪ በመሆኑ ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡
4ኛ.በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን የማያባራ የዘር ፍጅት መላው ኢትዮጵያውያን እንድታወግዙ እየጠየቅን፤ ለዘር ፍጅት ሰለባ ቤተሰቦችና ለመላው የአማራ ሕዝብ ፈጣሪ መፅናናትን እንዲሰጣቸው እንመኛለን፡፡
 
5ኛ.በየትኛውም ሁኔታና አካባቢ ለሚገኙ የሀገሪቱ ዜጐች መንግስት በህገ መንግስቱ መሠረት አስፈላጊውን የህግ ከለላና ጥበቃ እንዲያደርግ ዜጐች በየትኛውም የአገሪቱ ክልሎች ተዘዋውረው የመስራት ህገ-መንግስታዊ መብታቸውን እንዲያስከብርላቸው፤ አስቸኳይ ጥሪያችንን እያስተላለፍን፤ ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉትና ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን እንዲሁም ለወደመባቸው ሀብትና ንብረት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን፡፡
 
“አንዲት ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!”
መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም.አዲስ አበባ
 
 
 
 
ReplyForward