አማረኛ ቋንቋና ግዕዝ

መግቢያ

ቋንቋ ሁሉ መግባቢያ ነው የሚለው ቃል ከቋንቋ ባሕሪያት አንዱ ነው:: አዎ ትክክል ነው ፡፡ የቋንቋ ምሉዕ የለመ የሚለውም ትክክል ነው፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ አልፎ አልፎ በአንዳንድ የፖለቲካ ጽንፈኞች የሐሰት ቆብ (ዘውድ) የደፉ ዲቃሎችና ከየት እንደመጡ የማይታወቁ ወፍ ዘራሽ የእፉኝት ልጆች በአማራና በአማርኛ ቁዋንቁዋ ላይ ከፍተኛ ዘመቻ እያካሄዱ ነው።

አማራን ብቻ ሳይሆን የአማርኛንም ቁዋንቁዋ ቢችሉ ለማጥፋት ካልቻሉ ታሪክን በመደለዝ አማርኛን ሳባ ወይም ግእዝ በማለት ኢትዮጵያን አበሻ የኢትዮጵያን ታሪክ ደሞ የመቶ አመት እያሉ የራሳቸውም ለማስመሰል በከንቱ ለ60 አመቶች ለፍተዋል። አሁንም በሚጽፉአቸዉና በሚናገሩዋቸው ነገሮች ዉስት ይህ የሃሰትና የጥላቻ ታሪክ እዉን እንዲሆን ህዝቡን በማደንቆር ላይ ናቸው። አማረኛ የሚባል ቋንቋን አልነበረም አማራ የሚባል ነገድም በኢትዮጵያ አልነበረም አሁንም እናጠፋዋለን ለሚሉ ወገኖቻችን ስለ አማረኛ ቋንቋ እና ሥለ ነገደ አማራ አመጣጥና ሁኔታ በዚህ ጽሑፍ ግልፅ መረጃ እንሰጣለን

አማረኛ ቋንቋና ግዕዝ
አማረኛ ቋንቋና ግዕዝ

አማርኛና ግእዝ ከጥንት ጀምረው ተያይዘው የመጡ መነጋገሪያ እና መጸለያ በመሆናቸው የተሳሰሩ የአማሮች መነጋገሪያ እና መጸለያ ቋንቋ ናቸው::  የሚጽፉትም በአንድ የፊደል ዘር በመሆኑ እና ዘመናዊ አማርኛም የሚጻፈው በራሱ በአማርኛ ፊደሎች ስለሆነ አንዱ ከአንዱ ይቀድማል ለማለት በጥልቀት መጽሃፍ ቅዱስንና ሌሎች ስለተፈጥሮና ስለ ስነፍጥረት የተጠኑ ሰነዶችን ማጥናት ይጠይቃል። ለምሳሌ እግዚአብሄር ከአብርሃምና ከሳራ ጋር የተነጋገረው በአማርኛ ስለመሆኑ ልጃቸዉን “ይሳቅ” ብለው ስም ማዉጣታቸው አንዱ ማስረጃ ነው።

ስለሆነም አማራ ነገድ ሲሆን ቋንቋውም አማረኛ ሆነ ፡፡

ከዚህ በመነሳት አማራ ማለት አመልካች ፣ቀዳሚ ፣ ምሳሌ እንዲሁም ዱካ ፈለግ ብረሃን ማለት ነው:: “አምሃራ” የሚለው ቃል በግእዝ (“አም” ህዝብ “ሃራ” ደሞ ነጻ) ማለት ሲሆን አንድ ላይ “ነጻ ህዝብ” ማለት ነው። በራሱ በአማርኛም ደሞ ቀጥተኛ ትርጉሙ “ያማረ ደስ የሚል” ማለት ነው። ይህን ስል ማንንም ለመጥቀም ማንንም ለመጉዳት ወይንም ማንንም ነገድ አሳንሶ ነገደ ኣማራን ከፍ ለማድረግ አስበን እንዳለሆነ አንባቢያን ልብ ይሉት ዘንድ እናሳስባለን፡፡ ከዚህ ጋራ ተያይዞ አማራ ማለት ለባህሉ ለወጉ ለእምነቱ ለወገኑ እና ለሀገሩ የሚጨነቅ ህዝብ ነዉ፡፡

ማስረጃ ፡–ወግዮን የኣውዳ ለኢትዮጵያ ይላል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ትረጉሙ ግዮን የተባለው አባይ አና ጣና አትዮጵያን ይዞራታል ማለት ነዉ ፡፡ ይኽም ቦታ ኖህን እና መርከቡን የሙጥኝ ብሎ የሚኖረውን ነገድ ተሸክሞ በአብዘኛው በጾሞና ጸሎት ተግቶ ለኢትጵያ ሕዝቦች የሚኖረው ነገድ እመነቱን በገንዘበና በወሬ የማይለዉጥ እንግዳ ተቀባይ ሰው አክባሪ ፈጣሪውን ፈሪ ጠለቱን ደፋሪ የሆነ ነገድ ነው ፡፡

ማስረጃ፡- ኀንብርታ ወአክሊላ ለኢትጵያ ተብሎ የተጻፈለት ፡፡ ማለት ለኢትዮጵያ እንብርትና አከሊል (ዘውድ) የተባለዉ ይህ ነገድ ነዉ፡፡ ይኽ ነገድ አባትህ የተከለዉን ድንበር አታፍርስ ተበሎ የተጻፈውን ሕግ ጠብቆ የሚኖር ነው፡

አማረኛ ቋንቋ እንግድህ ከመግባቢያነቱም በላይ የራሱ የሆነ የፊደል ገበታ ያለው የቁጥር ዐሃዝና ፊደላት ያሉት እና እያንዳንዱ ፊደላት የ የራሰ ቸዉ የሆኑ ትርጉም ያላቸው መሆኑ ነው ፡፡

ሀ፡-ይኽ ሃሌታው ሀ ይባላል ሃሌ ፣ በሀ ፣ ሁለት ሁሴን ወዘተ የመሳሰሉትን ይፅፋል

ሐ፡- ሐመሩ ሐ ሐመር ፣ሐብት፣ ሒሳብ ሕግ ፣ ፀሐይ ወዘተ

ኀ፡- በዙሃኑ ኀ ይባላል ይህም ኃይል ፣መድኅን ፣ ኃጢኣት ወዘተ. የመሳሰሉትን ይፅፋል፡፡

ሀ(ሐ ፣ ኀ) የ ሚለዉ ፊደል ትርጓሜ ፡-ሀ ብሂል ሀለወቱ ለአብ ሲል ይገኛል ማለትም የአብ አነዋወር ማለት ነው ፡፡(አባታችን እግዚአብሔር ለዘለዓለም ይኖራል ማለት ነው )

ሀ/ ሀ ብሒል ሀመ ወሞተ (እርሱ አምላካችን ለእኛ ለሰው ልጆች ሲል ታመመ ሞተም) ማለት ነው ፡፡

ሀ/ ሀ ብሒል ኃያል እግዚአብሔር (እግዚአብሔር ኃያል ነው ማለት ነው) ፡፡

2/ ለ ለ የሚለው ፊደል ትርጉም ለ ብሒል ለብሠ ሥጋ ዚኣነ ፡፡ አምላክ እንደኛ ሰው ሆነ ማለት ነው ፡፡

መ/ መ ብሒል መንክር ግበሩ ለእግዚአብሔር (የእግዚአብሔር ሥራ ድንቅ ነው ማለት ነው)

3/ ሰሠ ሁለት ሰ እሳቱ እና ንጉሡ

ሰ/ እሳት ፣ ኢየሱስ ፣ ክርስቶስ ፣ መቅደስ ፣ ሰዓት ፣ሰናይት

ሠ/ ንጉሥ ፣ ትዕግሥት ፣ ሥላሴ ወዘተ.

ሰሠ/ሰ ብሒል ሠረቀ በሥጋ እምድንግል (ከደንንግለ ማርያም አመላካች ን ሰው ሆኖ ተወለዴ ወይንም ከሥጋዋ ሥጋ ከነብሷ ነብስ ነስቶ ሰው ሆኖ ተወለዴማለት ነዉ ፡፡

4/ረ ተርጉም ረ ብሒል ረግአ ሠማይ ወምድር ፡፡ ሰማይና ምድር በቃሉ ጸና (ቆመ) ማለት ነዉ ፡፡

5/ ቀ ትርጉም ቀ ብሒል ቀዳሚሁ ቃል ወውእቱ ቃል ይላል ይኽም ቀዳሚው ቃል ነው እርሱም እግዚአብሔር ነው ማለት ነው

6/በ ትርጉም በ ብሒል በትህትና ወረደ ይላል ይኽም እግዚአብሔር አምላክ ለሰው ልጅ ፍቅር ሲል በትኅትና ከሰማየሰማያት ወረደ ማለት ነው ፡፡

8/ ተ ትርጉም ተ ብሒል ተሰብአ ወተሰግወ እማርያም እምቅድስት ድንግል ፡፡ አምላካችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነበሷ ነብስ ነስቶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ ማለት ነው ፡፡

9/ ነ ትርጉም ነ ብሂል ነስኣ ደዌነ ወፆረ ሕማመነ ይላል ፡፡ አምላካችን በፈቃዱ ጸዋትወ መከራችንን ተቀብሎ አዳነን ማለት ነዉ(በሺታችንን ያዘ ሀህማማችነንነንም ተሸከመ ማለት ነዉ)

10/አ ትርጉም አ ብሂል አእኵቶ ለእግዚአብሔር ፡፡ እግዚአብሔርን አመስግኑ ማለት ነዉ ፡

አ/ ብሒል ዓቢይ እግዚአብሔር ፡፡ እግዚአብሔር ትልቅ ነው ማለት ነው፡፡

11/ከ / ብሒል ከሀሊ እግዚአብሔር ፡፡ እግዚአብየሔርታጋሽ (ቻይ) ነዉ ማለት ነዉ

12/ወ ወ ብሒል ወረደ በትኅትና ፡፡እግዚአብኄር በትኅትና ከሰማይ ወረደ ማለት ነው ፡፡

13/ ዘ ዘ ብሒል ዘ ኩሎ ይእህዝ እግዚአብሔር ፡፡ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ይይዘል ማለት ነው (ዓለም በመዳፉ ነች ማለት ነው)

14/ የ የ ብሒል የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኃይለ ፡፡ የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን ታደርጋለች ማለት ነው፡፡

15/ ደ ደ ብሒል ደመረ ሥጋ ዚአነ ምስለ መለኮቱ ፡፡ እግዚአብሔር ሰው ሆነ ሰውም አምላክ ሖነ ፡፡

16/ ገ ገ ብሒል ገባሬ ሰማይ ወምድር ፡፡ እገዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ ማለት ነው ፡፡

17 / ጠ ጠ ብሒል ጠዐሙ ወታዕምሩ ፡፡ ታዉቁ ዘንድ ቅመሱ ማለት ነው ፡፡

18/ጰ ጰ ብሒል ጰራቅሊጦስ መንፈስቅዱስ ፡፡ ጰራቅሊጦስ ማለት የመይታይ የማይለይ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው ፡፡

19/ ጸ (ፀ) ጸ ብሒል ፀሐየ ጽድቅ ሠረቀ ለነ ፡፡ የእዉነት ፀሐይ ወጣልን ለእኛ ፡፡ ማለትም እግዚአብሔር አምላክ ሞት ሳይገባው ሞቶ እኛን ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነብስ አዳነን ማለት ነው፡፡

20/ ፈ ፈ ብሒል ፈጣሬ ሰማይ ወምድር ፡፡ የምድርና የሰማይ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው ማለት ነው ፡፡

21/ ፐ ፐ ብሒል ከተፐ ፊደላተ ፡፡ እግዚአብሔር ፊደላቶችን ጽፏል ማለት ነው ፡፡

በኣማርኛ ቁጠር የሌላቸዉ ፊደላት (ጨ ሸ ኸ ጀ ኘ ቸ ዠ) አነዚህ የገዕዝ ግስ የሌላቸው የአማረኛ ፊደላት ናቸው፡፡

ሥለዚህ አማራ የሚለው ነገድ እና አማርኛ የሚለው ቋነቋ ትክከለኛ ሃገር በቀልነታቸው አያጠራጥርም ማለት ነው ፡፡

በመሆኑም የመጀመሪያው የሰው ዘር መገኛ የስልጣኔ ፈር ቀዳጅ የእውቀት መፍለቂያ በሆነችው በአማራ ክልል የኖኅ መርከብ ከጥፋት ዉሀ በኋላ በአረፈችበት በዚህ በአራራት ተራራ ዘጌ ገዳማት በነ ልቀሊቃውተን ተዋናይ ቤት ከግዕዝ አባቱ ቤት ያደገ ብርቅየ ቋንቋ ነው ብርቅየ ነቱ ለእያነዳንዱ ጾታ እና ብዛት እንድሁም የቅርብና እሩቅ ጾታዊ አገላለጽ ፍንትው አድርጎ ሳያሻማ እና ሳያደናግር ያስቀምጣል ፡፡ ከግዕዝ ጋር የተሳሰረ ለመሆኑም በውስጡ ሰምና ወርቅ፣ ፈሊጣዊ አነጋገር ፣ዘይቤ፣ ምሣሌያዊ ንግግር ወዘተ. ይዞ ይገኛል ሥነ-ግጥምንም ያጠቃልላል እነዚህ የተባ የቋንቋ አጠቃቀም ይባላሉ ፡፡

እያንዳንዱ ፊደል ግዕዝ፣ ካእብ፣ ሳልስ ፣ራብዕ ፣ሐምስ ፣ሳድስ እና ሳብእ አለው ፡፡ ሌሎች በሀገራችን የሚገኙ ቋንቋዎች እንደምልክት እንጅ እንደቋንቋ የሚያስቆጥራቸው ምንም መረጃ የላቸውም ፡፡ ለምሳሌ ኦረምኛን ስናይ ፊደላትም ይሁን የኩጥር አሃዝ የላቸውም ፡፡ ይባስ ብለው የላቲን ፊደሎችን ደጋግሞ በመጻፍ ይጠቀማሉ ፡፡ይህ የባሰ ከንቱነት ነው ፡፡

በለማ ጠጁ