ሻለቃ ጌትነት መሳፍንት

ለአማራ ህዝብ በህይወት መኖርና ክብር ሲሉ በዚህ ፈታኝ ወቀትት ብዙ ወጣት ፋኖዎች በለጋ እደሜአቸዉ ዉድ ሕይወታቸዉን ገብረዋል። ሰሞኑን ካጣናቸዉ ከነዚህ የቁርጥ ቀን ልጆች መካከል አንዱ የዝነኛዉ የአማራ አርበኛና ፋኖ መሳፍንት ተስፋ ልጅ ሻለቃ ጌትነት መሳፍንት ነዉ። ሀዘናችንን መራር ሚያደርገዉ ደግሞ ሻለቃ ጌትነት መሳፍንት ህይወቱ ያለፈዉ ከጠላት ጋር ፊት ለፊት ገጥሞ ሳይሆነ በዉስጥ ሰርጎ ገቦች መሆኑ ነዉ።

እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ/ም በሰሜን ጎነደር ዞን ዳባት ወረዳ፣ አጅሬ በተባለች አነስ ያለች ከተማ ለአማራ ህዝብ አርቀዉ በማያስቡና የጠላትን ፍላጎት ለማሟላት በተቀጠሩ ጥቂት ከሀዲ ግለሰቦች በተተኮሰ ጥይት ተሰዉቷል። ሻለቃ ጌትነት መሳፍንት የሰሜን አምባራስ ክ/ጦር አዛዥና የራስ አሞራዉ 3ኛ ኮር ዋና አስተዳዳሪ ነበር። የአማራ መኩሪያ፣ ቃሉን ጠባቂና ጠላትን ጨባጭ ከሆነዉ ጀግናዉ ወላጅ አባቱ ከፋኖ መሳፍንት ተሰፉ ጎን በመሆን በብዙ ዉጊዎች ላይ በመሳተፍ በጀግንነት ተፋልሞ ድል እንዳደረገ ታሪኩ መስከሯል።

ጌትነት መሳፍንት በተለያዩ ዉጊያዎች ላይ አምስት ጊዜ ተመቶ ቢቆስልም ቁስሎቹ ሳያገግሙ ወደ ሌሎች የጦር ሜዳ ዉጊያዎች ይገባ እንደነበረ ታዉቆአለ። የቁርጡ ቀን የኢትዮጵያ ጀገና የአርበኛ መሳፍነት ተሰፉ ሎጆቹ ብቻ ሳይሆኑ ወንድሞቹ፣ አጎቶቹና መላዉ ቤተሰቡ ዉርደትንና ጥቃትን ባለመሸከም ለአማራ ህዝብ በህይወት መኖርና ክብር ለአስርተ አምታት በጽናት ታግለዉና ተሰዉተዉ የአማራዉ ትገል እንዲፈረጥምና ዛሬ አለበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ ከትዉልድ ትዉልድ የሚተላለፍ አኩሪ ታሪክ ሰርተዋል።

እዉቀት ሚዲያ ለቆራጡ የጌትነት አባት ለፋኖ መሳፍንት ተስፉ፣ ለመላዉ ቤተሰብ፣ ለቤተዘመዱ በሙሉ፣ ለመላዉ የአማራ ህዝብና እንዲሁም የአማራን ህዝብ የፍትህ እንቅስቃሴ ለሚደግፉ ኢትዮጵያኖች ሁሉ እግዚአብሄር ያጽናችሁ ሲል ከፍተኛ ሀዘኑን በመግለጽ ነዉ ። የወንድማችንን ነፍስ በገነት ያኑርልን። አሜን!